የአብዲ ኢሌ ቀኝ እጆች ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ ፤ ለቀማው ቀጥሏል።
የአብዲ ኢሌ የሚዲያ አማካሪና የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ። ከስልጣን አልወርድም በማለት ከፍተኛ የሃገር ክሕደት የፈጸመው አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ የሚዲያ አማካሪው የነበረው መሃመድ ቢሌ ድሬዳዋ ውስጥ ከተሸሸገበት በቁጥጥር ስር ውሏል።ግለሰቡ በተጨማሪ የሙያና ቴክኒክ ስልጣና ኃላፊ ሆኑ ክልሉን ያገለግላል።
በተጨማሪም የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊና በድሬዳዋ የአብዲ ኢሌ ወኪል ሞሃመድ አሕመድ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።
ግለሰቦቹ የሶማሌን የሃገር ሽማግሌዎች በመግደልና በማሰር የሚታወቁ ሲሆን የውጪ ምንዛሬም በኮንትሮባንድ በማመላለስ የ አብዲ ኢሌን ትእዛዝ የሚያስፈጽሙ ቀንደኛ ወንጀለኞች መሆናቸው ታውቋል። ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸው አፈናንና ግድያን በድሬዳዋና በ አከባቢው ማስፈጸማቸው ማስረጃ መንግስት ስላገኘባቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተጨማሪም የቀድሞ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የ አሁኑ የልማት ፕሮጄክት Pastoral Community Development Project (PCDP) ኃላፊ አብዲሃኪን ኤግል ቤቱ የተበረበረ ሲሆን እስካሁን የተሸሸገበት ባለመገኘቱ የደሕንነትች እያሰሱት ይገኛል።
RAJO NEWS
Arrests and house searches made in Dire-Dawa
– We are getting reports from reliable sources that Mohamed Bille “Miig”, head of Technical and Vocational Training (TVeT) and Media Advisor to former regional president Abdi Iley is arrested today in Dire-Dawa.
– The house of Abdihakin Egal was searched. Mr. Abdihakin was former VP and now the current head Pastoral Community Development Project (PCDP).
– Mohamed Ahmed, Diredhaba Security head, was also arrested.
These men were trouble-makers that Abdi Iley frequently dispatched with bags of money to dismantle the #Barbaarta youth in Dire-Dawa. They are also suspected of playing a role in the aborted assassination attempt of Somali elders and intellectuals who were holding a conference in Dire-Dawa.