አንዳንዶች ወገኖች የኦሮሞ ልሂቃንን ከሰፊው የኦሮሞ ህዝብ መለየት እንደተሳናችሁ ታዝቤአለሁ:: በየ አርቲክሉኦሮሞ ከማለት የተማረው ኦሮሞ ቢባል ለፍርድና ህሊናም ይቀላል:: ለምሳሌ ወንድም ስርፀ ደስታ የከተበውንእንመልከት:: እንደምሳሌ የሱን አርቲክል ልጠቀም እንጂ ብዙዋችን ይመለከታል:: ወንድሜ ሰርፀ ደስታ
በየቦታው ኦሮሞ ላልከው ባብዛኛው ተማርኩ ተብዬ የኦሮሞ ተወላጅ ብትለው ባብዛኛው ይረዳኛል ግምትህ::እኔው እራሴ ትውልደ ኦሮሞ ሆኜ እድሜልኬን ግራ ሲያጋባኝ የኖረውም ጉዳይ ብዙ ያስነበብከን እሳቤ ነው::ብዙዎች የራሴ ወገኖች “ጎበና” የሚል ስያሜ ሁሉ ይሰጡኝም ነበር በኢትዮጵያዊ አመለካከቴ በፀጋ ስያሜውንምመቀበሌን በኩራት እናገር ነበር:: የራስ ጎበናን ብልህነትና ሚና አውቄ ያደኩ በመሆኔም ጭምር ቅቅቅ:: ዋናውችግሩ እንደሚመስለኝ የጀመረው ከንጉሱ ነው:: ነፍሳቸውን ይማረውና ጃንሆይ ባደባባይ ኦሮሞነታቸውንቢያቀነቅኑ ኖሮ የተማረው ኦሮሞ ብዙም ባልተከፋ ነበር :: ሆኖም በግላቸውና በየቤተሰባቸው ጋብቻና አሰላለፍበፅኑ ኦሮሞነታቸውን ያጠናክሩ ና ይቁዋጩም ነበር:: ብዙም ያልገፉበት ኢትዮጵያዊነትን በጅጉ ከማጎልበትናከማጠናከር ፍላጎታቸው የተነሳ ነበር:: ይህንን ብዙዋች ወገናችን የንጉሱን ብልህነት አይሉት በኦሮሞነታቸው ለሀገረኢትዮጵያ ሲሉ “ደንታቢስነት” እንደየአተረጉዋገሙ ተወስዶአል:: ብዙዎች ዛሬ ድረስ የጃንሆይን ኦሮሞነት ሸምጠውይክዳሉ:: ለምን ቢባል ለሚፈለገው ብሶት መግለጫ አመቺ አይሆኑማ:: ጃንሆይ ከባድ ዩኒየኒስት እንደነበሩ ግንእኔም በቅርበት አውቅ ነበር::
ጠ ሚር አክሊሉ ነበሩ ሰርፀ ባለው የታሙት ለማለታቸው ግን ማረጋገጫ የለምከሀሜት በዘለለ:: ያን የመሰሉ ምሁር ጠ/ሚር እንድያ ወደጎሳ ንቀት ይወርዳሉ አልልም ግን አንድ ፊውዳል ራስወይም ደጃዝማች አማራ ሊሉ ይቻላቸዋል: ብለዋልም ብዙዋች ያውም ፀያፍ ቃል በመጠቀም:: በተማረውናበተራቀቀው አክሊሉ ለማላከክ: ይመችም ነበር ዘመኑ የፊውዳል ነበርና:: አክሊሉ ከበስተሁዋላቸው ብሪሊየንትአይምሮ እንጂ አጃቢ ፊውዳላዊ ደጀን አልነበራቸውምና:: በሌላ በኩል ለማፈንገጥ ይመች ዘንድ እራሳቸው ጄልታደሰስ አስነግረው እንደሆነ “ኦሮሞ ከተማረ አደጋ ያመጣልን አይነት ዘይቤ? አያችሁ በዛን ጊዜ የነበሩት የተማሩየኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ “የኔ እቀርብ አንተ አትቀርብ” ፉክክር ነበራቸው ከአማራው ፊውዳል አቻዎቻቸው ጋር ከጃንሆይ መወዳጀትን በተመለከተ:: በተለይም በግል ከጃንሆይ በኦሮሚፋ እየተቀኙ በአደባባይ ኦሮሞነታቸውን ጃንሆይ “መካዳቸው” እነ ታዴ ብሩ ያቃጥላቸው እንደነበር እኔው እራሴ ዘመዴን ዋቢ በማድረግ እመሰክራለሁ::ስለሆነም ይህ የኦሮሞን ልጅ የማስተማር “ሀጢያት” መሆን ከኦሮሞ ልጆች እንዳልመጣስ ምን መተማመኛይኖረናል ወገኖቼ?! እንደው ለማመላከት ያህል ነው ማስረጅ ስለሌለን: ብዙም አልሄድበትም::
- ወደዛሬው ተማርኩ ተብዬ ወገኖቼ ስመለስ, ያሁኖቹ በተለይም በዘመነ ወያኔ የተፈጠሩት ለየት ይሉብኛል::ጥላቻውን ወያኔ ደህና አድርጎ ከትቦአቸዋል:: ገና ከጡጦ እንደተላቀቁ አብዛኛዎቹ:: ሰርፀ እንደገመተውየተገላቢጦሽ አይመስለኝም:: ኦነግ ሲጀምር እንደዘመነ ወያኔ ባብላጫው ለአርዮስነት አልበቃም ነበር:: ለኔከኢትዮጵያ የተጣላ ማንም ጎሳ ውግዝ ከመአርዮስ ነውና:: የመንደርዮሽ ወይም የክልል አስተሳሰብ ከአገረኢትዮጵያ ውጭ የአሸዋ ላይ ካብ ነውናም:: ለዚህም ነው የጁዋር “ኢትዮጵያዊ ቅኝት” ሰውነቴ ውስጥ ቶሎያልሰረፀው:: በምንም መለኪያ እንደው የለየለት ባለ ዶቃው የወያኔ ባንዲራ ይሻል ነበር እንጂ የኦነግ ባንዲራገና ለገና ጁዋርን ወይም “በድል አድራጊነት የገባውን ኦነግን” አስደስታለሁ ተብሎ መናገሻ ከተማዋንያጥለቅልቅ? እንደው ለምልክት አንዲት አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ይጥፋ? ይህ ሁላችንንም ልብ የሰበረ ክስተትነው:: ምክንያቱም ይህ የኦነግ ባንዲራ በግድ በነዚህ ተማርኩ ተብዬ ህዝበ ኦሮሞ ላይ ተጫነ እንጂ ሰፊውየኦሮሞ ህዝብ ይህን ባንዲራ አልተዋህደውም:: አዎ በወያኔ ዘመን የተፈጠሩ ልጆች ይምሉበታል::ይገዘቱበታልም በኦሮምያ:: ለምን ቢሉ ወያኔዎች የቤት ስራቸውን በደንብ ተወተውባቸዋልና: የአማራባንዲራ ተብሎ አድጎ አማራ ደግሞ ክፉ ተናካሽ አውሬ ተብሎ ካደገስ ህፃን ምን ይጠበቃል ወገኖች? ይህአንድ ትውልድን ለመለወጥ ብዙ የቤት ስራዋች ይጠብቁናል እንደ ህዝብ:: ቄሮን ለማስደሰት ተብሎ አጋሩንፋኖን ማስቀየም ግን ተገቢ አይመስለኝም አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት መዲናን ዘልቃ የአፍሪካ መዲናበምንልበት ዘመን:: ያስተዋልነው ድርጊት ግን አዲስአበባ የሀገረ ኦሮምያ ዋና ከተማን ብሎም የኦነግ ዋናመዲናነት ፊንፊኔን እድምታን ነበር:: እውን ይህ ለዛሬው የአንድነት ድልድይ ግንብ አስፈላጊ ነበር? አላስፈላጊመልክት ያዘለ ነው:: በነገራችን ላይ ባለፈው ጎጃም ላይ ትራይከለሩ ንፁሁ ባንዲራ ሲውለበለብ የተከበሩትነጋሶ ያዙኝ ልቀቁኝ “ህገመንግስቴ ” ተደፈረ ሲሉ ምነዋ ዛሬ የኦነግ ባንዲራ ሽገርን ሲያጥለቀልቅአንደበታቸው ተዘጋ? የኦነግ ባንዲራ ባንድ ጀምበር ህገመንግስታዊ ሆኖባቸው ይሆን እንዴ?
- ወይስየልባቸው ደረሰና ነው? እንደው ብቻ ያስተዛዝባል የዚች አገረ ኢትዮጵያችን ጉዳይ :: ያሳፍራልም እንደ አንድኦሮሞ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ስቃኘው:: በእውነት:: ክቡር አቶ ለማም ሆኑ ዶር አቢይ ይህ ልጅ ውሎ አድሮ(ጁዋር) ላያቢሊቲ እንዳይሆንባቸው ከልቤ እፀልያለሁ:: ገና ለገና ቄሮን ዱካ ያስጠፋብናል ተብሎ ጁዋርንየማቀፍ የልምምጥ እስትራቴጂ ከሆነ ልጁ ብዙ ቀላምዶ ሌላ ኪሳራ ሳያመጣ በፍጥነት ቃል ገብቶ የሄደውንበተለይ ቄሮና ፋኖን በይበልጥ የሚያገናኝ ድልድይ መስራት ላይ እንዲያተኩር አቅጣጫ ማስያዝ የግድይላል:: እንጂ ስለተሰውት የኦሮሞ ልጆች ለቅሶ መድረሻ መሰረተ ድንጋይ መትከያ ጊዜም አልነበረም: ከልብእንነጋገር ከተባለ:: ያውም የኦሮሞ ልጆች ዛሬም ላይ እየታረዱ? ጅቦቹ ጎራ ለይተው በሪሞት ከርቀትአገሪቱዋን እያመሱ? ይህ ልጅ የአቶ ለማን ወይም ምራቅ የዋጡ አባገዳዋችን እገዛና መሪቃል በጅጉይፈልጋል:: እንደው የምወዳቸው አቶ ቡልቻ ደህና ይሆኑ? ምነው ድምፃቸው ጠፋ በዚህ የድምር ዘመን
- የሳቸው ምክር እጅጉን ያስፈልገን ነበር ዛሬ:: አደራ የተቀደስው የአንድነት ጉዞ እንዳይተጋጎል የሚመለከተውያስብበት :: ስለሆነም ወገኖቼ ሆይ እመኑኝ ጥላቻው የጀመረው ከሰፊው ኦሮሞ ወገን ሳይሆንከተደባለቀባቸው የኦሮሞ ልሂቃን በወያኔ አገፋሪነት በመሆኑ