አያሌው መንበር

የአማራ “ክልል”መንግስት በቅማንት ኮሚቴ ሰበብ ለህዝቡ ሰላም እጦት ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የጭልጋና አካባቢው 6 አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር አውሏል።

የህወሃት አክቲቪስቶች እና የክልላቸው መንግስት ጭምር የራሳቸውን የውስጥ ችግር ችላ በማለትና ሰው እንዳይሰማ በማድረግ ስለ አማራ ክልል ግን ሌት ተቀን ሲጮሁ እንሰማለን።አንድ ትግሬ አማራ ክልል ውስጥ በመኪና አደጋ ወይም በተቅማጥ ቢሞት እንኳን ለህወሃት <<ገዱ ገደለው፣ አማራ ገደለው..>> ማለታቸው አይቀርም።በቅማንት ጉዳይ እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ደም እንዲፋሰስ ሰርተዋል።ለነጋዴ ኮሚቴዎች ቢሮ ከመክፈት እስከ በጀት መመደብ እንደሚሰሩ ይታወቃል።ይህ ተግባራቸው ዘንድሮም ቀጥሎ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የጭልጋ፣ ነጋዴ ባህርና አካባቢው በሰላም እጦት ላይ ነበር።በእነዚህ ራሳቸውን ወደ ነጋዴነት በቀየሩ የቅማንት ኮሚቴዎች ምክንያት ዜጎች መዘዋውር አልቻሉም፣ የመንግስት ስራ ቁሟል።
አማራው ግን ከዚህ በፊትም ለሰላም ሲባል በትግስት አይቷቸው የፈለጉትን ቀበሌ ሲወስዱ ክልሉም ጨምሮ ሲሰጥ ዝም ብሎ ነበር። አሁን ግን እነዚህ እኩት ሰዎች በቅማንት ማሊያ ተሸፍነው የአማራ ሆቴል ማቃጠል፣ ቤት መደብደብ፣ ቢሮ እንዲዘጋ፣ ተማሪዎች እንዳይማሩ ማድረግና ሌላ ግጭት ሲፈጥሩ አማራውም ቁጣው እያየለ ሲመጣ የአማራ “ክልል” መንግስት ወደ ሰላም ማስከበር መግባቱ ይታወሳል።በዚህ መሰረትም 1. አዛነው አደባ ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ድ.ቤት ሀላፊ
አዛነው አደባ (ም/ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ሀላፊ፣አስማረ የከተማው ፀጥታ መረጃ ሀላፊ፣ኢንስፔክተር ጥላሁን አበበ የከተማው ፓሊስ አዛዥ፣ዋና ኢንስፔክተር አስናቁ የወንጀል ምርመራ ሀላፊ፣ሳጅን እርስቴ የፓሉስ የወንጀል ክትትል ሀላፊ፣ምስጋነው ትራፊክ ፓሊስ እነዚህ አስችሏል ለጊዜው ታስረዋል።

ዋናዎቹ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያውኩ፣ሰላማዊውን የአማራ ህዝብ ውስጥ ያለውን ቅማንትን ወከልን በማለት ግጭት የሚፈጥሩትና በቅማንት ስም ነጋዴ የሆኑት እነ ከፋለ ማሞ፣ እነ ንጋቱ ፀጋ፣ ነጋ ገፀጤ፣ አምባሳደር ዘመነ የመሳሰሉት የቅማንት ኮሚቴ አባላት አልተጠየቁም።
የክልሉ መንግስት እነዚህን በአስቸኳይ መጠየቅ አለበት።

ምንም እንኳን ዋና ተጠያቂዎች ባይያዙም አሁን ከቀናት በፊት ጀምሮ ቢያንስ የትራንስፖርት አገልሎት ተከፍቷል፣ የንግስ እንቅስቀሴውም እየጀመረ ነው።ከክልል የተላኩ አመራሮች መተማ፣ ቋራ እና ጫንዳባ ላይ ነዋሪውን አወያይተዋል።ጭልጋ ላይም መግበባት ላይ ተደርሷል

ነገር ግን ከቦታው በደረሰኝ መረጃ መሰረት እነዚህ ነጋዴ ኮሜቴዎች ሌላ ተልዕኮ ይዘው ቤተሰብ የሆነው ህዝብ ለማጫረስ እየጣሩ ነውና ቤት ማቃጠልና መደብደብ፣ ስራ ማስቆምና መንገድ እንዲዘጋ ማድረጋቸውን መንግስት ይህንን ካላስቆመ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እንገባለን እያሉ ነው።ይህንን ሀሳብ ቅማንቶችም እንደተጋሩት ነው የሰማውት።እርስበርሳቸው መስማማት ያልቻሉ ኮሚቴዎች እየበጠበጡ ነው።