1) ይህን ነገር የተቆረጠ፣ የተቀጠለ ከሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህን እየቆረጣችሁ እየቀጠላችሁ የለቀቃችሁ ካላችሁ ማፈር ይገባችኋል!

2) የተቆረጠ፣ የተቀጠለ ካልሆነ፣ ትክክለኛው የድርጅቱ ሰነድ ከሆነ አርበኞች ግንቦት 7 በዚህ ዘመን በሰነድ ይህን የመሰለ ጥላቻ በማስፈር የታወቀ “የአንድነት ሀይል” ይሆናል። ይህ እውነት ከሆነ የማዝነው ለዚህ ድርጅት ለተሰውት የአማራ ልጆች ብቻ ነው!

3) ይህ ሰነድ የተሰረዘ የተደለዘ ከሆነ ድርጅቱ ማሳወቅ ይገባዋል። የእኔ አይደለም ብሎ! የእኔ ነው ካለ ግን በግልፅ ትግል የሚያስፈልገው ድርጅት ይሆናል። ይህን ሰነድ ስህተት ነበር ብሎ እስከሚያምን ድረስ!

4) ይህ ሰነድ በርካታ የአማራ ልጆች መስዋዕት የከፈሉበት የአርበኞች ግንቦት 7 ሰነድ ባይሆን እመኛለሁ። ከሆነ ግን እንደሚባለው ፀረ አማራ ነው። ደማቸውም ደመ ከልብ ሆኗል ማለት ነው!

አደራ የምታውቁ አጣሩልኝ!