በተግባር በመሬት ላይ እያየን ያለነው ይንን ነው።
ኦህዴድ አባላቶች እና ድፍን የኦህዴድ መዋቅር ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያለው መዋቅር ነው። የቀድሞ የፓርላማ ኣባል በአቶ ግርማ ሰይፉ የተፃፈ፦
የኦህዴድ አባላቶች እና ድፍን የኦህዴድ መዋቅር ኦነጋዊ አስተሳሰብ ያለው መዋቅር ነው። በኦህዴድና በኦነግ መካከል ወደ ታች ወዳሉት አመራሮች ከሄድን ልዩነት የለም። ታች ያሉት ከነ ለማ ይልቅ እነ ጃዋርና እነ ዳዎድ ኢብሳን ነው የሚሰሙት።
በኔ ግምት እነ ዶ/ር አብይ ስለ መደመር ሲያወሩ የራሳቸውን ድርጅት አባላት እንኳን መደመር የቻሉበት ሁኔታ ያለ አይመስልም። የተደመረነው ሌሎቻችን እንጂ ኦህዴዶች አይደሉም። የዶ/ር አብይን አመራር ሕወሃቶች ናቸው የሚቃወሙት ይባላል እንጂ ከሕወሃቶች በላይ በነ ዶር አብይ ላይ ጥርስ እየነከሱ ያሉት የኦሮሞ ብሄረተኞች ናቸው። የኦሮሞ ብሄረተኞች ዋና አጀንዳ ኢትዮጵያዉያን በሰላም፣ በፍቅር ፣ በአንድነት ተከባብረው እንዲኖሩ ማድረግ አይደለም።
አንደባበቅ ዋና አጀንዳዎቻቸው ፡
አንደኛ- አሁን ያለው የኦሮሞ ክልል ሳይነካ ፣ በተጨማሪ አዲስ አበባ፣ ድረዳዋ፣ ሃረርና ሞያሌ ….. ከተሞች ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለሉ ማድረግ
ሁለተኛ – አዲስ አበባ ወደ ኦሮሞ ክልል የማትጠቃለል ከሆነ ደግሞ በአዲስ አበባ የኦሮሞ ልዩ ጥቅም እንዲጠበቅ፣ ኦሮሞ ቅድሚያ እንዲሰጠው….ማድረግ፤
ሶስተኛ – በባእድ ፊደል በላቲን የሚጻፍ ኦሮምኛ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይወስን ፣ የፌዴራል ቋንቋ እንዲሆንና አሁንም ሕዝብ ሳይወስን በግድ በላቲን በየትምህርት ቤቱ እንዲማሩ ማድረግ፤
አራተኛ – እነርሱ ስለሚጠሉት ብቻ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ መቀየር
አምስተኛ – አማርኛንና የግእዝ ፊደልን ከኦሮሞ ክልል፣ በግድ ሁሉን ነገር በኦሮሞኛ እንዲሆን በማስገደድ አሊያም ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ አማርኛ ተናጋሪዎች በማፈናቀል ማጽዳት
ስድስተኛ – ሕወሃቶች በስልጣን ዘመናቸው የአንድ ጉሳን የበላይነት እንዳሰፈኑት፣ ተራው የኛ ነው በሚል ነው መሰለኝ የኦሮሞ የበላይነት ማስፈን
ስባተኛ – ከላይ የተዘረዘሩት ተግባራዊ ካልሆኑ ታላቂቷን ኦሮሚያ፣ ሸገርን ይዞ መገንጠል ነው። እነዚህን አጀንዳዎች ይዘው በትጋት ሌትና ቀን እየሰሩ ነው። ሌሎቻችን “ኢትዮጵያ’፣ መደመር አለብን፣ ወገኖቻችን ናቸው፣ ከነርሱ ጋር መነጋገርና መመካከር አለብን። ከነርሱ ጋር አብረን እንስራ…..” እያልን፣ እነርሱ ግን ላይ ላዩን ጥሩ ቃላት እየተናገሩ ውስጥ ውስጡን በዘረኛ አጀንዳቸው ገፍተውበታል። እስከ ታች ድረ የኦሮሞን ወጣት፣ ሕጻናትን ሳይቀር በነርሱ መልክና አስተሳሰብ እየቀረጿቸው ነው። በላቲን እርስ በርስ የሚጻጻፉትና ለኛ የሚጽፉት የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
እስቲ ተመልከቱ፣ ሌላው ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ባንዲራን ይዞ ለዶ/ር አብይ ድጋፍ ሲሰጥ፣ በኦሮሞ ክልል ከተሞች (ከአዳማና በደሌ በስተቀር) ምንም ነገር አልተሰማም። በአምቦ ዛሬ በተደረገ ሕዝባዊ ትይንት ባንዲራዎች እይተናል። ሆኖም ለምልክት እንኳ አንድም የኢትዮጵያ ሰንደቅ አናይም። በጃጋማ ኪሎ፣ በጸጋዬ ገብረ መድህን አገር ይህን ማየት ልብን በጣም ይስብራል። ብዙም ነገሮችን ማድበስበስ ማቆም አለብን።
እዉነቱን እንነጋገር ።
በሌላው የአገሩቷ ክልፍ በስፋትና በኩራት የሚውለበለብ ሰንደቅ አለመታየቱ ብዙ መራራቃችንን በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ሌሎቻችን መናደድ ሆነ መቃወም ያለብን አይመስለኝም። ዶ/ር አብይ የሚናገረው የኢትዮጵያዊነት አንድነት መንፈስ፣ የመደመር መንፈስ ፣ በአማራ ፣ በደቡብ፣ በቤኔሻጉል ከተሞች ሲንጸባረቅ በኦሮሞ ክልል ከተሞች ካልተንጸባረቀ ፣ በግድ ኢትዮጵያዊነትን ተቀበሉ ማለት አስቸጋሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት አስገድደን ተቀበሉ ልንላቸው አንችልም። ይሄ የመብት ጉዳይ ነው።
በእድሜዬ የኢትዪጵያ አንድነት አቀንቃኝ ነኝ። ግን በመደመር ዘመን፣ በአገር ደረጃ በነ ዶ/ር አብይ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነገር እያየን፣ በኦሮሞ ክልል ግን ያለው መንፈስ የመደመር መንፈስ አለመሆኑ ምን አልባት ብዙዎችን ሊያስደነግጥና ተቃዉሞ ሊያስነሳብኝ የሚችል አመለካከት እንዲኖረኝ እያደረገ ነው። ሌላው ወደ አንድነት ሲመጣ እነርሱ ግን ኦሮሞነታቸው ላይ ካከረሩ፣ እንዴት አብረን ልንቀጥል እንደምንችል ግራ እየገባኝ ነው። እንዲህ አይነት ኢትዮጵያዊነትን አሳንሶ ኦሮሞነትን ብቻ በሰፈነበት ቦታ እንዴት ዬ ነጻነት ተስምቶኝ አገሬ ነው ብዬ ልኖር የምችለው ?
ምን አልባት ወደ አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ወደፊት ከምንሄድ በሰላም ስለመፋታቱ ማሰቡ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ብዩ ማሰብ ጀምሪያለሁ። በሁሉም የኦሮሞ ወረዳዎች ሕዝብ ዉስኔ ተደርጎ ሕዝቡ እንዲመርጥ በማድረግ ኢትዮጵያን አልፈልግም የሚለውን ማሰናበቱ ሳይበጅ አይቀርም። እንደ ሸዋ፣ ጂማ ..ያሉ አካባቢዎች ሕዝቡ በኢትዮጵያ ቀልድ አያውቅም። የሸዋ ወረዳዎች ምን አልባት ከምእራብ ሸዋ ዞን በስተቀር ድምጽ ቢሰጡ ምን ሊመርጡ እንደሚችሉ ማንም መገመት ይችላል። ያለ ምንም ጥርጥር ኢትዮጵያን አንፈለግም የሚሉ ካሉም አንደኛ የተከፋፈሉ ነው የሚሆኑት። አርሲ ባሌና ሃረርጌ ያለው ለብቻው ሲሆን ምእራብ ሽዋና ወለጋ ያለውም ለብቻው ይሆናል። ሁለት አገር ይመሰርታሉ ማለት ነው። በቃ እኛም ሰላም እናገኛለን፣ እነርሱም ሰላም ያገኛሉ።
አብዛኛው ሸዋ የኢትዮጵያ ግዛት ሆኖ ስለሚቀጥል ሸገርን ጨምሮ፣ ኢትዮጵያ መልኳን ብትቀይርም ኩታ ገጠምነቷን ግን ይዛ ትቀጥላለች። እኛ አንድነት ይሻላል ፣ ሁላችንም እኩል የሆንባት የዘር ልዩነት በማይደረግባት አገር እንኑር አልናቸው።
ለመንናቸው፣ ተማጸናቸው፣ ተለማመጥናቸው። እንዳያኮርዱ፣ እንዳይናደዱ ብለን ታገስናቸው። አሁንስ የበዛ መሰለኝ። እነርሱ የኢትዮጵያብ ሰንደቅ ካልፈለጉ፣ ኢትዮጵያዊነት ካልፈለጉ፣ የፈለጉትን መሆን ይችላሉ። ኢትዮጵያ ግን የሚወዷት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች አሏት። የልጆች መካን አይደለችም።
(ከዚህ በታች የምታዩት አምቦ ነው። በነገራችን ላይ በባህር ዳሩ ሰልፍ፣ የኢትዮጳያ ባንዲራ በመያዙ ሕግ መንግስቱ ተጣሰ ብለው ሲንጨረጨሩ የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ በዚህ የኦነግ ባንዲራ ከፍ በተደረገበት ቦታ እንደነበሩ እየሰማን ነው