ኮሎኔሌ ደመቀ ዘውዴ ንግስት ይርጋ እና ሎችም በተገኙበት በጃዋር ሙሀመድ የሚመራው የኦሮሞና የአማራ የህዝብ ለህዝብ የጋራ የውይይት መድረክ ባህር ዳር ብሉናይል አቫንቲ ሆቴል ተካሄደ ።
የኦኤምኤን ስራ አስኪያጅ ጀዋር መሀመድ በባሕር ዳር ከተማ ከወጣቶች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱም የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
ከውይይቱ ተሳታፊዎች የቀረቡ ጥያቄዎች
• አማራ ለኢትዮጵያዊነት፣ ለዳር ድንበር ሲሞት ነበር በኋላ ግን አማራ በመሆኑ እየተሰደደ እየሞተ ነው።
• የአኖሌ ሃውልትን ጨምሮ የጥላቻ ግንብ ስር እንዲሰድ መጽሃፍትን በማሳተምና ልዩ ልዩ ተረኮችን በመስበክ አማራ እና ኦሮሞን ለማጣላት የተሰሩ ሴራዎችን ለማስቀረት ለምን አልተሰራም?
• ህብረ ብሄራዊነትን ለመመስረት በምንጥርበት ጊዜ አዲስ አበባ የኛ ናት ብሎ ማሰብ ከታሪክ አንጻር ያስኪዳል ወይ?
• ለአማራ እና ኦሮሞ ወጣቶች ምከንያታዊነት መስራት ይበጃል።
• ሚዲያህ (ኦ ኤም ኤን) በኦሮሚያ ለሚኖሩ አማሮች ድመፅ አይደለም።
ከጀዋር መሃመድ የተሰጡ ምላሾች እና አስተያየቶች
• ለአማራ ብሄርተኝነት መጎልበት እና ለተጠቃሚነቱ እኔም ከእናንተ ጋር እሰራለሁ።
• ኦ ኤም ኤን ሲመሰረት የነበረው አርማ የአሁን ሳይሆን ከ1973 ዓ.ም በፊት የነበረ ነው። በወቅቱ እኔ ፈልጌ ሳይሆን ተሰርቶ የመጣ በመሆኑ በወቅቱ ተቀብየ የመሰረት ድንጋይውን አስቀምጫለሁ።
• የአርሲን ህዝብ ስለ አኖሌ ያነጋገረው ሰው የለም። እናንተም መገለጫችሁ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤ መፍትሄው ቀርቦ መነጋገር ነው።
• አዲስ አበባ የኦሮሚያ እና የአማራ ብቻ አይደለም፤ የጉራጌው፣ የሶማሌው…የሁሉም ህዝቦች መሆኑን ማወቅ ይገባል።
• የአማራን እና የኦሮሞ ህዝቦችን ለማጣላት መሞከር ኢትዮጵያን መለያየት ሳይሆን ህዝቦችን ማፋጀት ነው፤ይሄ ፖለቲካ አይደለም እውነት ነው።