የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር ሙሃመድ እና ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ያካሄዱት ውይይት(የቀጠለ)
ባሕር ዳር፡ነሀሴ 04/2010 ዓ.ም(አብመድ)
• ‹‹እውነተኛ የፖለቲካ ገበያ ለፍቅር እና ለአንድነት መሆን አለበት።›› ጀዋር ሙሃመድ
ወጣቶች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች
• የአኖሌ ታሪክ ስህተት መሆኑን በኦሮሞ ምሁራን በተደጋጋሚ ተነግሯል፤ ይህንን ለወጣቶች በማስረዳት ያንተ ሚና ምንድን ነው?

• ጃዋር ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች ጥቅም በእኩልነት ልትታገል የምትችልበት ስልት ምንድን ነው?

ጃዋር ሙሃመድ የሰጠው ምላሽ
• ጀዋር ሙሃመድ ኦ ኤም ኤን ሚዲያ ለአማራው ህዝብ መብት የሰራው አነስተኛ ነው የተባለው ትክክል ነው፤ የአማራው ጥያቄ እንዳይዳፈን ግን አድርገናል።
• እኛ ወጣቶች ላይ አተኩረን እንሰራለን፡፡
• እውነተኛ የፖለቲካ ገበያ ለፍቅር እና ለአንድነት መሆን አለበት፡፡
• መፈናቀሉ በአማራው ሲጀምር ብናስቆም አሁን ለኦሮሞ አይደርስም ነበር ለዚህም ነው ‹‹እኛ ሁላችን ነን›› ብለን ማሰብ ያለብን።
• በአማራ እና በኦሮሞ መካከል ያለው ግንኙነት ስትራቴጂካዊ እና ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን በአንድ ሰው ውስጥ ያሉ መሰረታዊ ህልውናዎች ናቸው።
• የአኖሊን ሃውልት ታሪክ የሚቀረው በዚህ ትውልድ መግባባት ነው፤አሁን ያለው ለውጥ ትልቅ እድል ነው። ሃገር በመዋደድ ላይ እንዲመሰረት፣ የጋራ ጠላት የሆነው ድህነት እንጂ የተናጠል ጠላት እንደሌለን ማሳየት ያስፈልጋል።
• ህዝብን ከህዝብ በማጣላት ትርፍ ማግበስበሰ ለሚፈልጉ ሰዎች እጅ መስጠት አያስፈልግም። ይህንን በመረዳት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡
• የአማራ ህዝብ በፌዴራል ስርዓቱ የተጠቃሚነት ጥያቄ ያነሳል እንጂ ለስርዓቱ ስጋት አይደለም። ወጣቱ አሁንም ለውጡን እንዲረዳ፣ በለውጡም ህብረ ብሄራዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ብዙ የቤት ስራ ይጠይቃል።
• ታሪክ ሳይዛነፍ ለወደፊቱ አብሮነታችን የሚጠቅመውን መስራት ከሁለቱም ክልሎች ይጠበቃል።

ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ
የአማራ መገናኛ ብዙሃን