በጉባኤው ላይም ዑላማዎች፣ምሁራንና የዕምነቱ ተወካዮች መሳተፋቸው ነው የተገለጸው።

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሙስሊሞች የገጠማቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ዘጠኝ አባላት ያሉት የጋራ ኮሚቴ ማቋቋማቸው የሚታወስ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለት ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የእስልምና ሊቃውንት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ሁለተናዊ ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ ጉባኤ ማካሄዳቸው ተገልጿል።

በዚህም ኮሚቴው በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ አሁን ላይ ያሉ ልዩነቶች እንዴት ይፈቱ?፣ በቀጣይ ምን መደረግ አለበት? በሚሉት ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት ማድረጉ ነው የተመላከተው።

የእስልምና አስተምህሮ ትኩረት የሚያደርገው አንድነትን፣ወንድማማችነትን መተባበርና መከባበርን አንጂ መለያየትን እንዳልሆነ የጋራ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ አንድነት ለመምጣት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል” ያሉት ሀጂ ዑመር ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁን ሚና ተጫውተዋል ልናመሰግናቸው ይገባል ብለዋል።

ስለ ሠላም በቁርዓን ላይ በግልጽ የተቀመጠውን ጉዳይ በተግባር መቀየር የሁላችን ኃላፊነት መሆኑንም ነው ሙፍቲ ሀጂ ዑመር የተናአገሩት።

በተለይ ወላጆች ልጆቻቸውና ወጣቶች በመልካም ስብዕናና በአንድነት መንፈስ እንዲታነጹ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።

የእምነቱ ምሁራን፣ አባቶች በተፈጠሩ ስህተቶች የታየውን መከፋፋል ከመሰረቱ እንዲፈታ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሀጂ ሙሀመድ አሚን ጀማል ጥሪ አቅርበዋል።

የጋራ ኮሚቴው ጸሀፊ ዶክተር እድሪስ መሐመድ በበኩላቸው ኮሚቴው ለሙስሊሙ ማህበረሰቡ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት፣ መጅሊሱ የሚቋቋምበት የህግ ማዕቀፍ

ለማዘጋጀትና የመጅሊስ አወቃቀርና አደረጃጀት ሰርቶ ለማቅረብ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነት እንዲጠበቅ የማድረግ ኃላፊነትን ተቀብሎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመላክተዋል።

ኮሚቴው ከእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴና ከገለልተኛ አካል የተወጣጣ መሆኑም ታውቋል።