туристический онлайн-справочник
Лучшие Андроид планшеты

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 42010 (ኤፍ..) በትላንትናው ዕለት አንድ የጥናት መጽሔት በቀን ሁለት ማንኪያ ከግማሽ ወይንም አምስት ግራም ያህል ጨው መጠቀም የጤና እክል እንደማያመጣ ይፋ አድርጓል፡፡

ባደጉት ሀገራት ሁለት ማንኪያ ከግማሽ ወይንም አምስት ግራም ያህል የሚጠቀሙ ሰዎች አምስት በመቶ ብቻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ በቻይና ደግሞ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ማህበረሰብ ከአምስት ግራም በላይ ይጠቀማል ተብሏል፡፡ 

ጥናቱ የተካሄደው በካናዳ ማክማስተር ዩኒቨርስቲ እና ሃሚልተን የጤና ሳይንስ ውስጥ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከሚታወቀው የጨው አወሳሰድ ልምድ የተለየ መሆኑም ተነግሮዋል፡፡

ምርምሩ በ18 የተለያዩ ሀገራት ለስምንት ዓመታት የተጠና ሲሆን ዕድሜያቸው ከ35 እስከ 70 ዓመት መካከል የሚገኙ 94 ሺህ ሰዎች ተካተውበታል፡፡

በጥናቱ የተካተቱት 94 ሺህ ሰዎችም የጨው ፍጆታቸው በቀን በአማካይ ከአምስት ግራም በላይ የሚጠቀሙ ናቸው ተብሏል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከዚህ ቀደም በቀን ከሁለት ግራም በታች የሆነ የጨው አወሳሰድ ከልብ ጋር የተገናኙ ህመሞችን ለመከላከል እንደሚረዳ አስቀምጧል፡፡

እንዲሁም የአሜሪካ የልብ ማህበር ደግሞ በልብ ህመም ለተያዙ ሰዎች ከአንድ ነጥብ አምስት ግራም በታች እንዲጠቀሙ ይመክራል፡፡

ሆኖም በዚህ ጥናት ውስጥ ከተሳተፉ ተመራማሪዎቹ መካከል የሆኑት ማርቲን የልብ ህመምንና ስትሮክን ለመከላከል በአማካይ ምንያህል የጨው አወሳሰድ መኖር እንዳለበት አሳማኝ የሆነ መረጃ ያለመኖሩንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የጨው አወሳሰድን ከልብ ህመምና ከስትሮክ ጋር የሚያያዙ ጥናቶች መውጣታቸውን ገልጸው እነዚህ ምርምሮች በግለሰቦች መረጃ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡

በጥናቱ ከተካተቱ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ እና ዚምባቡዌ ይገኙበታል፡፡


ምንጭ፦ሳይንስ ዴይሊይ


በአብርሃም ፈቀደ