August 11, 2018

 

ሰሞኑን በከፍተኛ ስለአብይ እየተሰራጨ ያለው ወሬ  አሳዛኘነቱ የወሬው መነገር ብቻ ሳይሆን በአለፉት 27 ዓመታት  ወደ አውሬነት የተቀየሩ የሰዎች ሠላመና ደስታ ለእነሱ ሲዖል የሆነባቸውን ምን ያህል በርክተው እንደነበርና አገራችንን የእርግማን ምድር እንዳደረጓት እንረዳለን፡፡

በምህረቱ አይቶ ከእነዚህ አውሬዎች ያዳነን ኃያል አምላክ እያመሰገን አሁንም እጆቻችን ወደሱ ይዘረጋሉ፡፡  ልብ በሉ በሰሞኑ የአውሮፕላን ውስጥ አብይን የመግደል ሙከራ ወሬ ለዘመናት ሕዝብና አገርን ወዳጅ መስለው በሕቡዕ መርዝ ከሚረጩትም እንዳንዶችን ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አለምነህ ዋሴ አንዱ ነው፡፡

አለምነህን በምናባዊ ዜና አውሪነት ከኦራቅ ጦርነት ጀምሮ እናውቀዋለን፡፡  ምናባዊ ያልኩት የሚያነበው ዜና ሳይሆን እራሱ ከዋናው ዜና ጋር እያቀነባበረ የሚፈጥረው ልብ ወለድ ስለነበር ነው፡፡ ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ ባይገባኝም ከቅርብ አመታት በኋላ  አንዳንድ መልዕክቶቹን ስከታተል ይህ ሰው ማን ነው የስባሉኝ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ ግን ብዙም አልገረመኝም፡፡ ብዙ እንደሱ መሰል ስላሉ በአፋቸው አብዝተው ኢትዮጵያዊ ሆነው እያሳዩን ውስጣቸው ሌላ የሆኑ አሉ፡፡ የወያኔ ውድቀት ከአስደነገጠውና የአሁኑ የአብይ ቡድን እንዲህ በሕዝብ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት ማግኘት ጸጉር ከአስነጫቸው አንዱ አለምነህ አንደሆነ ማሰብ ከጀመርኩ ሰንብቻለሁ፡፡ ሁላችሁም እስኪ በአለፉት ጥቂት የወሳኝ ትግል አመታት የለቀቃቸውን ወሬና ቪዲዮዎች አስተውሉ፡፡ በቃ ውስጡን የሚያሳብቁ ብዙ ነገር ታያላችሁ፡፡

ሰሞኑን አንድ ሴት ላከችልኝ እና እንዳቀርበው እባክህ አለችኝ ነገሩ እውነት ባይሆንም ግን 20 በመቶ የመሆን እድል አለውና ብዬ ነው ያቀረብኩት ብሎ ስለ አብይ የአውሮፕላን ውስጥ ግድያ ሙከራ ያወራው እንዲሆን የሚፈልገውን ማሟረት እንደሆነ ነው ለእኔ የገባኝ፡፡ የወሬው መሠረት አንዲት ሟርተኛ ሴት ነች፡፡ እንደተረዳሁት ነብይ ነኝ ስላለች ስለአብይ በመርዝ የመገደል ሙከራ ታሟርታለች፡፡ ከዚያ የዚች ሟርተኛ ተከታዮችና አጫፋሪዎች የዚህች ሟርተኛ ሟርት መፈጸም አለበት ብለው ስለሚያምኑ የአብይን በመርዝ የመገደል ወሬን አዛመቱት፡፡ አለምነህ የባለሟርቷ ተከታይ መሆን አለመሆኑ ባይገባኝም ወሬው ግን እሱ የሚፈልገው ስለሆነ ነበር ውሸት ነው ግን 20 በመቶ የመሆን እድል አለው እያለ ሲያሟርት የነበረው፡፡ ጻፈችልኝ ያላት ምን አልባት የባለሟርቷ ተከታይ ትሆናለች፡፡

ሹክሹክታ የተባለ ሌላው የዚህ ወሬ አዛማች የባለሟርቷ ተከታይ እንደሆነ ራሱ ተናግሯል፡፡ወሬውንም እያዛመተ ያለው የዚያች የሴትዮዋ ትንቢት ትክክል ነው በሚል ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ የዚህ ወሬ ተሳታፊዎች ለገንዘብ ሲሉ ሕሊናቸውን የሸጡ ናቸው፡፡ ሟርተኛዋ ብዙ ተከታይ እንዲኖራት፣ አሰራጮቹ የሴትዮዋ አማኝ መሆናቸውና ወሬው ምን አልባትም በዩቲዮብ ብዙ ሰው ስለሚያይልን ገንዘብ ያስገኝልናል በሚል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ አሁን ያለው ለውጥ እብድ ያረጋቸውና እንዲሆን የሚፈልጉትን በሰፊው ማውራት ነበር፡፡

ስለዚህ ቢያንስ በታወቁት በተወሰኑት ላይ እርምጃ መውሰድ ይቻለል፡፡ ሹክሹክታና አለምነህን የሚለቁትን በአለመመለከት፣ የዚህ ወሬ ምንጭ የሆነችውን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት ሕብረተሰባችንን ከስርዓትና እምነት እያወጡ የሰይጣን መንፈስ ተከታይ እያደረጉ ያሉትን ብዙ ነብይ ነን እያሉ የሚንቀሳቀሱትን ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡   ልብ በሉ ወሮበሎች እንኳን ነበይ አምላከም ነን ማለትን ይደፍራሉ፡፡ ሕዝብን እሴትና እምነቱን ማስጣል ተቀዳሚ አላማቸው ነው፡፡ ከሌሎች ሴራዎች በአልተናነሰ በእምነት በኩል ሕዝብን ከስርዓት የወጣ ማድረግና መበዝበዝ አገሪቱ ውስጥ ሥር እየሰደደ የመጣ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ቀጥሎ ትንቢት እንንናገራለን በሚል ትንቢታቸው እንዲፈጸም ታላላቅ ወንጀሎችን ጭምር ሊሰሩ እንደሚችሉ ማሰብ መልካም ነው፡፡ የአሁኑ የወሬ ሙከራም የዚሁ ወንጀል አካል ነው፡፡ አሁን በወሬ ነው፡፡ ቀጥሎ ግን ወንጀል የሚሠራ የተጠናከረ ቡድን ሰርተው ትንቢት ብለው የተናገሩትን በወንጀለኞቹ እንደሚያስፈጽሙ አስቡ፡፡ የእነዚህ ወሮበሎች ጉዳይ እንደዋዛ ባይታይ እላለሁ፡፡

ለዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

ከዛጎል የተወስደ