Somalia captured 10 ONLF fighters on their way to destabilize Somali region of Ethiopia.

በጅግጅጋ የተነሳውን ቀውስ ተከትሎ ሽብር ለመፍጠር የሞከሩ አስር የኦብነግ አባላትን ከነመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሶማሊያ ጋልሙዱግ አስተዳደር የጸጥታ ሃይሎች በጅግጅጋ የተነሳውን ቀውስ ተከትሎ ሽብር ለመፍጠር ድንበር ጥሰው ለመግባት የሞከሩ አስር የኦብነግ አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በመገስገስ ላይ እያሉ የሶማሊያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ደርሰው የጥፋት ኃይሎችን ከነመሳሪያቸው ማርገዋቸዋል።

የኦብነግ የጥፋት ሃይሎች የተያዙት ለኢትዮጵያ አቅራቢያ በሆነችው ባላንባሌ ከተማ ሲሆን ወዲያውኑ እንደተያዙ ወደ ጋልሙዱግ ዋና ከተማ ዱሳማሬብ ተዛውረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጥፋት ሃይሎቹን በድንበር ለማስገባት መሳሪያ አስታጥቆ ወደ ሱማሌ ክልል የላከው ኦብነግ የኢትዮጵያ መንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብያለሁ በሚል ልዑኩን ወደ አዲስ አበባ መላኩ ታውቋል። በዶክተር መሃመድ ኡጋስ የሚመራው የኦብነግ የልዑካን ቡድን በነገው እለት ከመንግስት ከፍተና ባለስልጣናት ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ይዟል።

ኦብነግ የጅግጅጋው ቀውስ ተከትሎ ክልሉን በጦርነት ለማመስ ተዋጊዎቹን ከመላክ ጀምሮ የ አብዲ ኢሌን ልዩ የፖሊስ ሃይልንና ሁጎ የተሰነውን ቡድን በማበረታታ በገንዘብና በመሳሪያ በመርዳት ተግባር ላይ ተሰማርቷል። ኦብነግ በዓንድ ጎን የሰላም ድርድር እያለ በሌላ ጎን ደግሞ ለጦርነት መነሳቱን በተግባር እያሳየ ስለሆነ አንዱን መምረጥ እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ ።

https://www.garoweonline.com/so/news/somalia/galmudug-oo-qabatay-xubno-ka-tirsan-onlf-fahfaahin