August 11, 2018
ከኢፌዴሪ መከላከያ ሃይል ከፌደራል ፖሊስ እና ከሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ
በዛሬው እለት የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እና ሌሎች የፀጥታ ሃይል አዛዦች በተገኙበት በጂግጂጋ ከተማ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ለክልል ሰላም በትብብር እና በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል።
ዋና አዛዡ እንደተናገሩት የፀጥታ ሃይሎቹ ክልሉን ወደ ሰላምና መረጋጋት ለመመለስ በመከላከያ ሰራዊት ዕዝ ስር ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል።
የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ለክልሉ ሰላምና ደህንነት በጋራ የሚሰራ መሆኑንም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።
Source – FBC