አሁን ማምሻውን በኢቴቪ ዜና ላይ ዐቢይና ደብረጽዮን ቅዱስ ፓትርያርኩን ለመጠየቅ ፋታ ከማይሰጥና አጣዳፊ ወቅታዊ ሥራ ላይ ተነሥተው እንደመጡ በመግለጽ የሶማሌ ክልል በሚሉት የሀገራችን ክፍል የተፈጠረውን ቀውስ ለማረጋጋት እጅግ አድካሚ በሆነ ሥራ ተጠምደው እንደሰነበቱ ዐቢይ ትንሽም ሳያፍር ሊነግረን ሞክሯል፡፡
ጉድ እኮነው እናንተየ! ወይ ዐቢይ!!!
የተከበሩ ጠ/ሚ ሆይ! ይሄ ግን ሕዝብ በደረሰበት ሰቆቃ፣ አረመኔያዊ ግፍ፣ አሳር፣ ስቃይ ማፌዝ አይሆንብዎትም ወይ??? ነው ወይስ በሕዝብ ሰቆቃ ማፌዝ፣ መቀለድ፣ መሳለቅ ፈልገው ነው እንዲህ ዓይነቱን ፌዝ የሚናገሩት???
ቀውሱን ለማረጋጋት እንዲህ አድካሚ ሥራ ስለሠራቹህ ነው እንዴ መከላከያ በቶሎ ገብቶ ዜጎችን በእምነታቸውና በማንነታቸው ከመታረድ፣ ከመቃጠል፣ ከመፈናቀል፣ ከመሰደድ የታደገው??? አብያተክርስቲያናትን፣ ቤት ንብረቶችን ከመቃጠል፣ ከመዘረፍና ከመውደም የታደገው??? ለዛ ነው እንዴ ሕዝቡ በየተጠለለበት ስፍራ ለ6 ቀናት የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ በረሃብና በጥም ሲቆላ የሰነበተው??? ምን ማለት ነው የፈለጋቹህት??? ከተጠያቂነት መሸሻቹህ መሆኑ ነው???
ሕዝብ አሳሩን እየበላ፣ ኢሰብአዊና አረመኔያዊ ግፍ እየተፈጸመበት እያለ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ማዕከላዊ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ሁኔታውን ለመቆጣጠር የሚከለክለው ሕግ በሌለበትና ግዴታና ኃላፊነት ያለበት በሆነበት ሁኔታ መብት የሚሰጡት የሕገመንግሥትና የአዋጅ አንቀጾች ባሉበት ሁኔታ “ክልሉ ጥያቄ ሳያቀርብ ሠራዊት ማስገባት ሕገ መንግሥቱን ይጻረራል!” እያላቹህ እያላገጣቹህ አይደለም እንዴ በሠራቹህት ጭካኔ የተሞላበት ሸፍጥ ስታስፈጁት የሰነበታቹህት??? ይሄ ግፍ በሕዝብ ላይ እንዲከሰት ለማድረግ ስታሴሩ የሰነበታቹህትን ነው እንዴ “አድካሚ ሥራ ላይ ነው የሰነበትነው!” የሚሉን???
ዐቢይ ምን ሊለን እንደፈለገ ገብቷቹሃል ወይ ወገኖቸ??? ተያይዞ በቀረበው ዜና ላይ “”መከላከያ ሠራዊት ይሄንን ሁሉ ጥፋትና ውድመት ካደረሰው ከአብዲ ኢሌ ልዩ ኃይል ጋር “ሊዋጋ ነው!” እየተባለ የሚወራው ወሬ ሐሰት ነው በአሁኑ ሰዓት የአብዲ ኢሌ ልዩ ኃይል፣ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ መረጋጋትን ለማምጣት አብረው እየሠሩ ነው!”” የሚል ዜና አብሮ ተዘግቧል፡፡
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ገብቷቹሃል??? አረመኔው አብዲ ኢሌና አረመኔ ልዩ ኃይሉ እንዲሁም ሌሎች አጋሮቹ ሕዝብ ላይ ለፈጸሙት አረመኔያዊ ግፍና ወንጀል “አይጠየቁም!” ነው ሊሉን የፈለጉት፡፡ “በዐቢይ ዘመን ማንም የፈለገውን ቢያደርግ አይጠየቅም!” ነው ማለት የፈለጉት፡፡ “ለምን?” ተብሎ ሲጠየቅ ደግሞ መልሱ “ዘመኑ የመደመር እንጅ የመቀነስ አይደለማ!” ነው፡፡ አያቹህ አይደል የዐቢይን የመደመር ፍልስፍናን አደጋ???
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! እባክህን አትጃጃል??? ይሄ ዐቢይ መደመር መደመር የሚለው ፍልስፍና የወያኔ/ኢሕአዴግን ወንጀለኛ ባለሥልጣናትን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ የተዘየደ ዘዴ እንጅ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እንደሚጠቅም ታምኖበት የተያዘ ሁነኛ መላ እንዳልሆነ ዕወቅ???
የዐቢይ የመደመር ፍልስፍናና የዜሮ ብዜት ስሌት ውጤት አንድ ነው ምንም ልዩነት የላቸውም፡፡ የሁለቱም ውጤት ዜሮ ወይም ምንም ነው፡፡ ምክንያቱም ተኩላን ከበግ ጋር የመደመር፣ ምግብን ከመርዝ ጋር የመደመር፣ ወተትን ከሐሞት ጋር የመደመር፣ እሳትን ከጭድ ጋር የመደመር ወዘተረፈ. ውጤቱ ባዶ ወይም አደገኛ ኪሳራ ብቻ ነውና፡፡ እናም እባክህ ወገኔ ሆይ ንቃ???
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com