August 11,2018

ስሞችዎ ብዙ መሆናቸውን በአንደበትዎ ስለመስከሩ በእውነተኛው ስምዎ ሳይሆን በfake “ታምራት “ይህችን ጥያቄ ላቀርብልዎ ፈለግሁ:: አርስዎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የአማራ ዘመዶቼ በግፍ ከገደል ተወርውረዋል:: ለዚህም አርስዎ እኔ እንዲወረወሩ አላዘዝኩም :አላስጨፈጨፍኩም ብለዋል:: እኔ ግን እርስዎ አስወርውረዋል እላለሁ:: አዲስ አበባም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ላይ ቦንብ የወረወሩትን ሳይሆን የህዝቡ ጥያቄ ያስወረወሩት ላይ ነው:: ለመወርወር ብር ካለ ችግር የለም::

እርስዎ በራስዎ አንደበት የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት የአማራ ገዢ መደብ ነው ብለው አስረግጠው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ::ከእርሶ መሪነት በፊት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ( ተፈሪ መኮንን ጉዲሳ) ና ኮሎኔል  መንግስቱ ሀይለማርያም አያና በዘር ኦሮሞዎች መሆናቸውን እያወቁ ይህንንም ክደው በአማራ ላይ ልዩ ጥላቻ ለምን እንዲቀርፅብዎ ሆነ?  ከዚያም አልፈው የኢትዮጵያ መንግስት የሁሉም ብሄሮች ያውም ኤርትራውይንም ያሉበት መሆናቸውን ሳይቆጠቡ ሀቁን እያወጡ በአማራ ላይ ልዩ የሆነ የጥላቻ ቋጠሮ ለምን ያዙ? እውነት አርሶ ከአማራ አብራክ ነው የተፈጠሩት? ይህ ካለሆነ እንዴት የአማራ ብሄር ድርጅት መሪ ሆነው አቶ መለስ ዜናዊ ሲሰየምዎ እልቀፈፈዎትም ? ዛሬ “የጌታ እየሱስ ልጅ ” ስለሆኑ ሳይሆን እኔም ከንፁህ አማራዎች :የማንንም ንብረት ካልቀሙ :ሁሉንም ጎሳና እምነት ሳይለዩ በህይወት በነበሩበት ዘመን የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማኞች ሆነው የዋቀ ጉዲፈቻን እምነት ጭምር እንድናከብር እንድንወድ ቋንቋና ባህላቸውን እንድንላበስ ኮትኩተው ያሳደጉን አርስዎ ጠላት አድርገው በዘመቱባቸው አማራ ኢትዮጵያውያን ወላጆቼ ስም ይቅር ብዬዎታለሁ ::በዘመነ ዐቢይ ይቅርታና መደመር በሽ በሽ ስለሆነ ይህ ችግር የለውም::ጭራቁ የአማራም ጠላት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያምም ይቅርታ ተደርጎለታል::

ህይወቱን በሙሉ አማራን የሚጠላው መለስ ዜናዊም ሲሞት እኮ አማራው በአደባባይ ወጥቶ አልቅሶለታል::አንብቶለታል:: በክብር ከአርበኞቻችን ጎን ቅድስት ስላሴም ቀብሮ ሀውልት ሰርቶለታል:: አማራ ሁልጊዜ ይቅር ባይ ነው::ችግሩ የይቅርታ ጉዳይ አይደለም::አማራ ለኢትዮያዊነት ዘላለም ህይወቱን ስለገበረ ዛሬም ይቅር ይሎታል::ለማወቅ የምፈልገው ግን አማራ በአማራነቱ ብቻ ጨቋኝና ገዢ ይለመሆኑን ልቦ እያወቀ ለምን በአማራ ላይ የተለየ የጥላቻ ቋጥሮ ለምን ቋጠሩ? ከዚይም አልፈው ቅዱስ ፖትሪይርኩ አማራ ናቸው በሚል ጥላቻ ብቻ ለመግደልና ከመንበራቸው አስገድደው ማባረርዎን ዛሬ በፀፀት ሊተርኩልን ይፈልጋሉ::ከሞተው መለስ ላይ ሊያላክኩም ይፍጨረጨራሉ! እምነት የሌለው ኮሙኒስትና ተራማጅ ትናንት ሆነውም ዛሬ “ጌታ እየሱስ ይመስገን” እንደ ኢትዮጵያዊም ለማሰብ መመለስዎ ደስስስስ ይላል::

ከአማራ መነኩሴ የትግሬ መነኩሴ እኮ ይሻላል ብለው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሻሉን አምነውበት ከህግ ውጪ ይህንንም ተፈፃሚ አድርገዋል::በዚሁ አንደበትዎ ይዳሸን ባንክ ከህግ ውጪ በውጪ ዜግነት ባለው አላሙዲን መቋቋም የለበትም ብለው ሽንጥዎን ገትረው ለህግ በላይነት ሲከራከሩ ግን አማራ ናቸውና ይገደሉ ብለው ኢትዮጵያዊውን ቅዱስ ፖትሪያርክ አቡነ መርቆርዮስን ከህግ ውጪ ከሀገራቸው ሲያባርሩ  ኢፍትሀዊ በደል በአማራ ላይ ባሎት ልዩ ጥላቻ ብቻ ተፈፃሚ አድርገዋል::ይህ ሁሉ ፀረ አማራነት እንዴት በአእምሮዎ ላይ ሊቀረፅ ቻለ? የኮሚኒስት ርዕዮተአለም አማራን ጥሉ ከገደል አስወርውሩ ይላል? አማራን አዋርዳችሁ ግዙ የሚል አስተምሮ ይሰብካል? አማራ የሰው ሀገር ምን ይሰራል? ሀረር ሄደው የተናገሩትን ለማስታወስ ብዬ ነው! በአማራ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ አድርጉ ብሎ ያስተምራል?  የናሁ ጋዜጠኛ “ታምራት ላይኔ “እውነት ስሞ ነው? ብሎ የጅል ቢጤ በፈገግታ የተላበሰ ጥያቄ ከሚጠይቅ ፍርጥ አድርጎ “ታምራት ላይኔ ” fake name ቢሆንም የትውልድ ዘርዎ ከዬት ነው? አባትና እናትዎ ትውልዳቸው ዪት ነው? አስተዳድጎ እንዴት ነበር ? ምን ይመስላል? አማራ ኖት? ከሆኑ ለምን ጠሉ? ካልሆኑስ ለምን ለመሆን ፈለጉ? አማራን ለብቻ ለምን ጠሉ? ብሎ ቢጠይቅ ወጣቱ  ባለብዙ ስሞች “ታምራት “ላይኔ በአማራ ላይ የተለየ ጥላቻ ለምን እንደቋጠረ ትምህርት ይሰጠን ነበር::

መለስ ዜናዊ አምርሮ ለምን እንደጠላዎና ያለበቂ ምክንያት እንዳሳስርዎ በኢንተርቪው ላይ አሰምተውናል ሆኖም ለምን ልዩ ጥላቻ በእርሶ ላይ መለስ እንደቋጠሩ ስላልገለፁ በዚህም ማብራሪያ ቢሰጡን ለህዝብ አስተማሪ ይሆናል::ነገር ከመሰረቱ ውሀም ከምንጩ ነው ይላሉ አበው:: ስለዚህ እኔም ይህን ጥያቄ ለህዝብ እንዲመልሱ አፈልጋለሁ:: እውነተኛው ታምራት? ላይኔ ማን ናቸው?