(ሚኪ አማራ)
ግንቦት ሰባቶች የፌስቡክ ፕሮፖጋንዳዉን ተዉት እና ለእነዚህ ቀላል ጥያቄዎች ብቻ መልስ አምጡ እስኪ
1. ወልቃይት የትግራይ ነዉ፡፡ ትግራይ ኢትዮጵያ ዉስጥ እስከሆነች ድረስ ወልቃይት የትግራይ ነዉ አላችሁ፡፡ የ27 አመቱን እንተወዉ እና በባለፉት ሶስት አመታት ብቻ በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ብቻ 1500 ሰዉ ሞተ፡፡ እና ይሄን ሞት እንዴት ነዉ ጀስቲፋይ የምናደርገዉ ግንቦት ሰባት ወልቃይት የትግራይ ነዉ ካለ ለአማራ ህዝብ ከህወሃት በምንድን ነዉ የሚለየዉ፡፡ የሞቱት ሰወችስ ለጌጥ ነዉ እንዴ
2. የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር አዲስ አበባ ያለ አማራ መጤ ነዉ አለ፡፡ ለዛዉም በኢሳት ቴሌቪዥን ነዉ ይሄን እንደዛ ያለዉ፡፡ የአዲስ አበባ አማራ መጤ ነዉ ካለ ኦነግስ ከዚህ የተለየ ሌላ ምንድን ነዉ ያለዉ?
3. አማራ ሲገዛ ነዉ የኖረ ስለዚህም የሌላዉ ብሄር ተራ ነዉ አይነት አባባል በፕሮግራማችሁ ዉስጥ ተጽፎ አለ፡፡ ይሄስ ከህወሃት ማኒፌስቶ በምን እንደሚለይ አስረዱን እስኪ
4. ስልጣን ለመያዝ ሁለት እና ከዚያ በላይ ቋንቋ መቻል አለበት ይላል የፖለቲካ ፕሮገራማችሁ ላይ፡፡ አማራዉ በዋነኛነት ቋንቋዉ አማረኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በባለፉት 27 አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ አማራዉ ተገልሎ ነዉ የቆየዉ አሁን ደግሞ ሁለት ቋንቋ አትችልም ተብሎ ከፖለቲካዉ እንዲርቅ ነዉ፡፡ እና ከኢህአዴግ በምን ይለያል ፕሮገራማችሁ ለእኛ ለአማሮች
5. አማራ የለም እንዲሁም መደራጀት የለበትም ይላሉ የግንቦት ሰባት አፈቀላጤወች በኢሳት ቴሌቪዥን ቀርበዉ፡፡ የአማራን ህዝብ የሚመራዉ እናንት የኢትዮጵያ ለዉጥ መሪ የምትሉት አቶ ገዱ ደግሞ አማራ በአማራነቱ ባለመደራጀቱ ብዙ ችግር ደርሶበታል፡፡ ያለመደራጀቱ ለእኛም የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለመመለስ ተቸግረን ቆይተናል፡፡ እናም አማራዉ በአማራዉ መደራጀት አለበት ይላል፡፡ የአማራን ህዝብ የሚመራዉ ሰዉ ይሄን ከመከረ ግንቦት ሰባት ፌስቡክ ላይ ሁኖ አትደራጁ የሚለዉ ትናነት በህወሃት ያን ያህል ስቃይ ሲደርስበት ያልተከላከለዉ ነገ ደግሞ ስልጣን ባለዉ ቡድን እንደፈለገ ሊደረግ ነዉ የተፈለገዉ፡፡
6. ራያ መተከል የአማራ ህዝብ እና መሬቶች ናቸዉ፡፡ ዛሬ እኒህ ቦታወች ላይ የሚኖሩ አማሮች ከደርግ በባስ ጭቆና ዉስጥ ናቸዉ፡፡ ወልቃይት እና ራያ የሞተ ሰዉ እንኳን ወስዶ ለመቅበር መንግስት ነኝ ባዩ የማየፈቅድበት ቦታወች እንደሆነ የአካባበቢዉ ሰወች ነግረዉናል፡፡እና በኢትዮጵያ ዉስጥ እስካለን ድረስ እኒህ ቦታወች በትግራይ ወይም በሌላዉ ክልል ቢሆኑ ችግር የለም የምትሉት ለምን ይሆን
እና ለአማራ ህዝብ ምንድን ነዉ የያዛችሁት፡፡ ለአማራ ህዝብ የምትመልሱለት ጥያቄ ምንድን ነዉ? ነጻነት ከሆነ አሁንም በህዝቡ ብርቱ ትግል እየመጣ ነዉ ወይም መቷል፡፡ እኒህ ጥያቄወች በባህርዳር እና ሌሎች አካባቢዎች ሰልፍ የተስተጋቡ ናቸዉ እናንተ ግን ጥያቀወቹ ተገቢ እንዳልሆኑ ሰበካችሁ፡፡ እና ምን ለመመለስ ነዉ የተዘጋጃችሁት፡፡ባጭሩ ለአማራ ወጣት እና ህዝብ ምንድን ነዉ የምትመልሱለት አጀንዳ፡፡
*************