አሁን አሁን ሁኔታዎች ስመለከታቸው አደገኛ ሆኖ እየመጣ ያለው እና እንደ ሰደድ እሳት ጥቃቱ በሕዝብ እና በቤተክርትያኖች መቃጠል እና ዝርፍያ እየበረታ በመጣበት በኦሮሞዎቹ አስተዳዳር (የጃዋርን ቃል ልጠቀም) በዛሬው ጊዜ ጥቃቱ እንዳይደመጥ እና ሉአላዊ ሰንደቃላማችን እየተዋረደ ባለበት ባዲስ አባባ እና በውጭ አገር ተከላካይ ሽፋን ለኦሮሞዎቹ አስተዳዳር እየሰጡ ያሉት በምርቃና የነፈዙ ነፈዞች ምክንያት እንደሆነ ኮለል ያለ ሃቅ ነው። አሮሞዎቹ ማስተዳደር ስላለቻሉ፤ ሰላምን ማስከበር ያቃተው የኦሮሞዎቹ አስተዳዳር ባስቸኳይ ስልጣኑን ለደነዙ ለተቃዋሚም ቢሆን ያስረክብ። ያው አገሪቱ የበተ-ሙከራ መለማመጃ ከሆነች ዘመን አልፏታል። አስቸኳይ እርማት ካለደረጉ ካልሆነ አገሪቱ እንደገና ወደ ባሰ ማጥ ሊያስገቡዋት ነው። በሦስት ወር የኦሮሞዎቹ አስተዳዳር ውስጥ በጣሊያን ጊዜም ሆነ በሶማሌ ወረራም ሆነ በማንኛውም ወቅት (ምናልባት የግራኝን ወደ ጎን አስቀምጠን) እንዲህ ያለ ውርደት እና ጸጥታን ማስከበር የማይችል ሰነፍ አስተዳዳር አላየሁም። በኦነግ ባንዴራ ብቻ ማውለብለብ የሰለጠኑ የመድረክ ምላሰኞች ሥልጣን ላይ ሲወጡ ጸጥታን ማስፈን ያልቻሉ ጉዶች እንዴት ወደ ሠልጣን መጡ? መልሱ እንከታተል።

አስተዳዳር በተደጋጋሚ ሳይሰለቸን ጥቂት እጅግ በጣም በጣት የምንቆጠር ሰዎች የኦሮሞ ቄሮዎች በኢትዮጵያዊነት ሽፋን ወደ አደገኛ የአገሪቱ ብጥብጥ ሊያመርዋት እንደሚችሉ ተንብየናል።አሁንም አቁዋሜ ያ ነው። ምክንያቱም ካሁን በፊት ደጋግሜ እንደገለጽኩት፤ የኔ አቁዋም ታምር ካልመጣ “ተጨባጩ ፍልሚያ” (ሪል ዲል) ብየ በምጠራው ምዕራፍ ሲደረስ ፖለቲከኞች ጠረፔዛ ላይ ይዘውት ለድርድር ሲመጡ አሁን ያለው “በባንዳው ብአዴን” እና “በጠባብ” ኦሮሞ ብሔረተኞች እንዲሁም “በተገንጣዮቹ” ኦጋዴን ነፃ አውጪ እንዲሁም በጠባቡ ህወሓት ትግሬዎች እና የመሳሰሉ ዛሬ እየታየ ያለው በተለይ በብአዴን እና ኦሮሞ ኦሆዴድ እየታየ ያለው ጊዜአዊ መተቃቀፍ፤ እንደሚደፈርስ ቃሌ እንደ ማስረጃ ያዙልኝ።

አይደፈርስም ከተባለ “አንድነት ሃይል” እያለ እራሱን እና አገሪቱን ለአደጋ እየተወ በስመ አንድነት፤ዲሞክራሲ እና ፍቅር በሉአላዊነት የሚደራደር (የሚሞዳሞደው ልበለው በጥሩ አማርኛ) አድርባዩ አቁዋመ ቢሱ ወለዋዩ የአማራው ምሁር (ፕሮፌሰር አስራት አባባል ሆዳም አማራው) እና ከሌላ ጎሳ የተሰባሰበ ጠባብነትን የሚያወግዝ የነፈዘ ሃይል፤- ጮሌዎቹ “የጎሳ አቀንቃኞቹ እነ ጃዋር እነ ለማ እና የመሳሰሉ” በሚጠይቁት የዞር አሉ አልሸሹም “ብሔር ብሔረሰብ ሕዝቦች ራስን የማስተዳደር መብት እስከ……የተፈጥሮ ሓብት ለክልሉ ጎሳ በባለቤትነት እና በልዩ ጠቀሜታ በ “ዴሞክራቲክ ፌደራሊዝም” ሽፋን ስም ተስማምቶ እንደነበረው ይቀጥል ብሎ ካልተስማማ፤ የአንድነት እና የፍትሕ አቀንቃኙ ክፍል አጀንዳውን
ይዞ ከጸና እና አጅሬ ሜንጫዎች ከሦስት ቀን በፊት በጃዋር መሪነት በመሰረተ ድንጋይ ያስቀመጡት 3/4ኛው የመላው ኢትዮጵያ ዜጎች ምድር የሆነው በሕገ ወጥ እና በጡንቻ ወረራ የከለሉት ኢትዮጵያዊ ሉአላዊነትን የሚዳፈር “የኦሮሚያ ካርታቸው” (ሦስተኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም) በይዞታችን ካልጸናልን ‘አገር ካላፈረስን’ እንደሚሉ የተዋቀ ነው። ይህ ደግሞ የምናየው ይሆናል። አይጠይቁም የምትል አሽቃባጭ ሁሉ ያኔ ብትፈርጥ ብትዘል ጌታቸው ረዳ “አይበልናን/ዶ/” የሚለውን የወያኔ ትግሬዎች ሙዚቃ ብቻ ነው መርጬ የማስዘፍንልህ።

ኢሳት የሚባለው የፖለቲካ ተቺዎች ስብስብ ዛሬ ሳደምጥ “የተቦርኖ’ (የታማኝ ወንድም) በስተቀር (ምናላቸው ስማቸው የተባለው ተብታኝ ለጊዜው ከተቦርኖ ጋር ልደምራው) በስተቀር ያ ለወያኔ ያገለገለበትን ባንዳዊ አግልገሎቱን እራሱ ይቅርታ ሳይጠይቅ ለእኩያዎቹ ባንዳዎች “ይቀርታ ጠይቁ” ሲላቸው የየነበረው የወያኔው ሚኒሰቴር ኤረሚያስ እማ ጭራሽኑ ጃዋርን ሊሸጥልን ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ጥሩ ተንታኝ የነበረው ሰውየ የጎሳ ነገር ሆናበታለች መሰለኝ ጃዋር ከልቡ ተለውጧል እያለ ሲያሽቃብጥለት ነበር። ያውም እኮ አዘጋጆቹ እንጂ ጃዋር ሓላፊነት መውሰድ የለበትም ሲል እኮ ነው ደግሞ በሚያስቅ እና በጮሌ ስለት ጃዋርን ሊከላከል የሞከረው! እንዲህ ያሉ አደገኛ ነፈዝ ምሁራኖች አንደበት መስማት ይሄ የምሁር መንጋ ሁላ ምን ጉድ ነው ት/ቤት ውስጥ የተማረው እያልኩ ሁሌም ይደንቀኛል።
እንዴት ሰው በሦስት ቀን ልዩነት አዲስ አበባ ውስጥ ያሳየው ጸረ ኢትዮጵያ ድርጊት ባሕር ዳር ሲሄድ ከልቡ ተለውጧል ማለት የሚቻለው? በሦስት ቀን ልዩነት ውስጥ ጃዋር ተለውጧል1? አረ እባካችሁ ምርቃናችሁን ቀንሱት? ምርቃናውን ትቼ ‘ድንቁርናችሁን’ ልለበል?
እንዴ ያለፈው አልፏል፤ የጃዋርን ፤ የመለስ ዜናዊን፤ ሌንጮን፤ የጃራን ……..ማሕደሩን አታውጡ አትናገሩ እኮ ነው እያሉ መሪቃኒዎቹ በየ ዩቱቡ ነፈዞቹ እየቃዡ በሚያስገርም ደደብነት እኛን ለማስተማር እየጣሩት እያሉን ያሉት። አሁን የምድረ ዩ ቱብ ነፈዝ እና ተቺው ጋዜጠኛም ምሁሩም የተያያዘው አዲስ ባሕሪ ደግሞ ሌሎቹን አትንኩ ፤ የገደሉን፥ የቀጠቀጡን ፥ ሴቶቻችን የዘረፉብንም ፥ ባሰንደቃላማችንችን ያዋረዱብንን ሁሉ ስለ እነሱ አታውሩ ጊዜው “የመደመር ወቅት ነው” ፥ ስለ እነሱ አትናገሩ ፥ “ስለ የ ሶማሌ ኦጋዴኑ የአብዲ ኢሌን ወንጀል ብቻ ነው የምናወራው እኮ ነው እያሉን ያሉት”። እንዴ? ጃዋር እንኳ ባቅሙ ያ ሁሉ ጉድ በለፈለፈበት የወንጅል እና የከፋፋይ ምላሱ ላደረገው ድርጊቱ ይቅርታ መጠየቅ ከብዶት “ያለፈው አልፏል” እያለ ጅሉን ማሕበረሰብ ሲያጃጅል “አውራምባ በተባለው” ዩ ቱብ ድረገጽ ያደረገው ቃለ መጠይቅ መስማት እውነት ብዙ ጅል እንዳለ አስተውሏል። ኦሮሞ ከጀርባየ አለ በሚል ኩራት እጅግ እንደ ቤኒቶ-ሙሶሎኒ የተለጠጠው ትዕቢቱ እንደተማመነ ማወቅ አያስቸግርም። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ “እምባየ መስፍን” የነ አብይ አማካሪ እንዲሆን ጥሪ ሲያቀርብ ይህ የሰማችሁ ምን እንደምትሉ እየጠበቅኩ ነው።
የመደመር መርቃኝ ሁሉ እስኪ ልጠይቃችሁ፡
የሜንጫው አብዮተኛ ጃዋር መሃመድ ፍንፍኔ ብሎ በሚጠራት አዲስ አበባ የተውለበለበለት የኢትዮጵያ ሉአላዊነት የሚዳፈር “የገንጣዮች ባንዴራ” እና እንዲሁም አስሬ ቄሮ እያለ ስማቸውን እየጠራ ሲያሞግሳቸው የነበሩትን ሲጮኹለት የነበሩት መንጋዎቹ የታዘብንበት ምን ክስተት ልትሉት ነው? መደመር? እውነት አዲስ አባባ ኢትዮጵያ ነው ወይስ ሜኔሶታ ከተማ አማሪካ ነው? ይህ ሁሉ አገርን የሚዳፈር ድፍረት ልናይ የቻልነው? ብላችሁ እስኪ ጠይቁ? ያየነው ክስተት እኮ ቀደም ብለው “በኦሮሚያ ኬኛ” ሲውለበለብ የነበረ እና ሲነገር የነበረ የተንጸባረቀበት ክስተት እና መፈክር እኮ ነው እያሳዩን ያለው። ያውም ዛሬ እማ ይባስ ብሎ የኦሮሚያ ካርታ እንደ አገር ካርታ በመሰረተ ድንጋይ ሃውልት ታትሞ ተጥዶላችኋል። ይህስ ምን ልትሉት ነው? እሲኪ መርቃኒዎች ከምርቃናው ውጡ እና የመደመር ትርጉም ከዚህ ክስተት ጋር ትርጉሙ ንገሩን? መደመር ማለት ይህ ከሆነ ኋላ ሜንጫ እንደማይመዘዝባችሁ ምን ዋስትና አላችሁ? ያው ሶማሌዎች ያሳዩት አሳዛኝና ነውረኛ ክስተት አይተነዋል አደለም? 11 ቤተከርስትያን ሲቃጠል? ምን ጉድ ነው እያየን ያለነው? ምርቃናው አሁንም አልለቀቃችሁም? ሰላመዊ ሰልፍ ተደረገ? ልምን አልተደረገም? መልሱ ንገሩን እንጂ ምድረ መርቃኝ ሁላ! ኦርቶዶክሱም መርቅኗል፤ ከሕግ ውጭ ሁለት ፓትርያሪክ ስላገኘ! እኮ ለምንድነው ቤተክርስትያኒቷ ሰላማዊ ሰልፍ አደስ አባባ ልትጠራ ያልፈለገቺው። አብይን ላለማስቀየም!? ይኸኔ እስላሞቹ ቢሆኑ 11 ያክል መስጊድ ቢቃጠልባቸው የኸኔ ኢትዮጵያም ዓለምም ቀውጢ ያደርጓት ነበር። ክርስትያኑ እና አማራው ግን ያው ለጠላቱም አልጋ የሚያነጥፍ ባሕል አለው እየተባለ ስለደነዘ ይመስለኛል፤ አፉን በነጠላ ሸፍኖ ዝም እንዲል አደረጉት።
እውነቱነ ልንገራችሁ።
ከሦስት አመት በፊት በየዩኒቨርሲቲው ግቢ ሁላ ኦሮሚያ…. ሱሉልታ ኬኛ///// እያሉ ሲፎክሩ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ…በግርግሩ ጊዜ እኔ እና ጥቂት ጓዶቼ ከአዲስ አባባ ሲልኩልኝ የነበረው ደብዳቤ እና ስጋታችን እውን እንደነበረ ያየሁበት ክስተት ሕያው ሀኖ ተጠናክሮ ከመቸውም ጊዜ ያየሁት ስጋቴ ዛሬ ነው። ያልጠበቅኩት ክስተት ግን አንድ ነገር ነበር። እሱም ጃዋር አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ ዓይን ያወጣ ብሔራዊ ሉኣላዊነትን የሚጋፈጥበት ዕድል በር ይከፈትለታል ብየ ፍጹም አልገመትኩም ነበር። እነ ለማ ለካ “በኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ሲሉን የነበረው መመርቀኛ ስልታቸው የኦሮሞ ኬኛ ስራቸው በምስጢር ሲያፋፍሙበት የነበረው ነው። ወያኔ የነ ሌንጮ ግንጠላ ከልክሎአቸው እንደነበር እናውቃለን። ለሶማሌውንም እኩል። ዛሬ በስልት ገብተው አላማቸውን አሳኩብን። አስገራሚ ስልት ነው፡ ለብልጥነታቸው “ቆቤን አወረድኩላቸው”።
ከቦሌ እስከ “ሚሊየነም አዳራሽ” የታየው ሉኣላዊነትን የሚጋፋ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ትዕይንት ኢትዮጵያ ምድር እንዲህ ሲታይ “ዜጎች ኩፉኛ ይቆጣሉ” ብየ ነበር፤ እንኳን መቆጣት “ይባስ ብሎ” ንጉሴ ጥላሁን የተባለው የብዕዴን የትግሬዎች ባንዳ ፤ ያ ሁሉ ሉአላዊነትን የሚጻረር ትዕይንት እያየ “ጃዋርን” የነፃነት ታጋይ ብሎ ሲያሞካሸው መስማቴ ዓለም ተገላቢጦሽ የሆነችበት ወቅት ደረስን።
ብዕዴን የተባለው ወልቃይት የትግሬ ነው ብሎ ፈርሞ የሰጠ አስገራሚ የወያኔ አሽከር ያ ሁሉ ውርደት ሳይበቃ አድስ አበባ ጃዋርን ለማስተናገድ አስቀያሚ ክሰተት ከታየበት ትዕይንት በኋላም ቢሆን ይበልጥኑ በሚያናድድ ሁኔታ ጃዋር “ባሕር ዳር” ድረስ ሄዶ ለኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ሞተናል፥ ለወደፊቱም እንሞታለን ፥ ሰንደቃላማችንን የሚዳፈር ክስተት እንጋፈጣለን በሚሉ አማራዎች መንደር ሄዶ እንዲህ ያለ የሞቀ አቀባባልና ክብር ይሰጠዋል ብየ ፍጹም ያልጠበቅኩት ክስተት ነበር። ይህ ስልት በደምብ የተጠና ኦሮሞዎቹ የተፈላሰፉበት ጥናት ነው። ጃዋርን ለምን ተቀበላችሁ በሚል አማራው ክፍል እና ግድ የለም እንደመር በሚሉ የመረቀኑ አማራ ክፍሎች መካካል ልዩነት በመፍጠር የአማራ ሃይል አዳክሞ ለወደፊቱ ብቸኛ ሃይል በመውጣት ስርዓቱን እየመሩ ባሉት ኦሮሞዎች የታቀደው እቅድ እውን ለማድረግ እንደሆነ በምንም አልጠራጠርም። ጃዋር ትግራይ ሲሄድም በዚህ ስልት ትግሬው ለሁለት እንደሚከፍለው በዚህ ተየንኮል ስልት አሮሞዎቹ መለስን ሊበልጡት ትንሽ አልቀራቸውም። ከመለስ ጋር ማሕበረሰብን በማዳከም አሰራር ከጎኑ ሆነው ስለሰሩ ከመለስ ብዙ የተማሩት ስልት ይመስለኛል።
አሁን ግን ትግሬዎቹ ዝምታን መምረጣቸው የጫካው የቆረጣ ስልታቸው በስርዓቱ ገልባጨች ላይ ምን እርምጃ ያመጡባቸው ይሆን የሚለው አስጊ ነው።ትንሽየዋ ጃዋር የወያኔ ምስጥ ስልት ሳታውቅ ከአዲስ አበባ ሸሽተው “መቀሌ ውስጥ ሄደው ለምን ይሸሸጋሉ”? ሲል ይጠይቃል። እኔ ከመሳቅ ሌላ ምን ልበል። ምናልባትም የዘረፉት ገንዘብ እውጭ አገር ስላለ አብይ ስለ እነሱ የያዘው አመስፈራርያ ዱላ ሊኖር የሚችል ነገር ኖሮ ሰግተው ካልሆነ ፤ ጃዋሪኖ እንደምታወሪው ‘ወያኔ በአብይ ላይ ብረት ማንሳት አቅም አንሶት ነው ብየ አልልም’። ለምን ሸሹ በሚለው ትንተና “የለሁበትም’። መቀሌ ስትሄጂ ልዩ ሴራ ይዘሽ ካልሄድሽ በስተቀር ካቴና እንዳያስገቡልሽ ብቻ ተጠንቀቂ። ደብረጽዩን ጋርም እንደተነጋገርሽ ሳትደብቂ ነግረሽናል። ጅብ ለጅብ ያገናኘ የመደመር ጊዜ?
እኔ ግን ያስገረመኝ አማራዎቹ ባሕርዳር ውስጥ በጃዋር ላይ ያሳዩት ማሽቃበጥ ባይደንቀኝም፤ ትንሽ ሕዝባቸውን ምን ይለናል አይሉም ወይ? ነው ያልኩት። ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው እንዳለው “* የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፈጸመው ለዚህ ወንጀሉም ፈጽሞ ይቅርታ መጠየቅ ከማይፈልገውና የመገንጠል ዓላማ ብቻ እንዳለው ካወጀው አሸባሪ የጥፋት ኃይል ጋር ሕዝባቸውን የዚህን አሸባሪ ኃይል አርማ በነፍስወከፍ አስይዘው እየጨፈሩ ባሉበት ሁኔታ “የለውጥ ኃይል ነን! አንድነት፣ መደመር፣ ኢትዮጵያዊነት!” ምንትስ ምንትስ የሚሉትን ነገር እንዴት አመንክ ወገኔ??? ከማለት ምን ማለት ይቻላል?” ይላቸዋል።
እውነቱን ነው ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን። ማመን የሚያስችል ንቃት የላቸውም። ንጉሴ ጥላሁንን አታዩልኝም፤ በዛ ገሃነም እሳት አዳራሽ ውስጥ ገብቶ የአማራን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ተረግጦ እያየ ምንም ሳይሰማው? አማርኛ ቋንቋ ለመናገር በፍቀዱልኝ ልናገር ተብሎ የሚደመጥበት አዳራሽ ውስጥ? አማራ በምንም ታምር ከዚህ በኋላ ይነሳል የሚባል ከዚህ ወዲያ እኔ አላምንም። ተመክሮ ፥ ተብሎ ፥ ተብሎ ፥ እባክህ ተነስ ተብሎ ፤ ጠላቱን
አፍቃሪ፥ ለማንም አስተናጋጅ፥ ሕዝብ አክባሪ ፥ ምናም በሚል ሌላ ቀርቶ ለባንዳም ጭምር አልጋ ሚያነጥፍለት ባህል ያለው ጨዋ ነው! እያሉ የሚያሰራጩ ነፈዞች አማራን ‘ከድጡ ወደ ማጡ” እየነዱት እንደሆነ አልገባቸውም። እኔስ ለብዙ አማታት እባካችሁ ልብ በሉ ፥ ተማሩ ፥ አስተውሉ ፥ እያልኩ ስለፈልፍ የቀሩኝ ቃላቶች የሉኝም፡ ጨርሻለሁ። በሌላ ሰው ቃላት ቢገባቸው ልንገራቸው።
እስኪ ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን በመጨረሻ ጨንቆት ስለ አማራ ወገኖቹን ያስተላለፈውን መልዕክት ልድገምላችሁ እና እኔም በዚህ ልሰናበታችሁ።
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እንዲህ ይላል፦
“ኧረ ተው! ኧረ ተው! በተለይም አማራው ተው ወገኔ ተበላህ ተው??? እኔ ደጋግሜ ተናግሬያለሁ ይሄ ነገር አላማረኝም!!!
እነሱ እነ ጃዋርን አስገብተው በቢልዮኖች ልብ በሉ በሚሊዮኖች (በአእላፋት) አላልኩም በቢሊዮኖች (በብልፎች) ብር ካፒታል (ወረት) ኦኤምኤንን በማንቀሳቀስ ድብቅ ዓላማቸውን ለማሳካት በአስደናቂ ብቃት እያጣደፉት ነው እንቅልፋሙ ወገኔ ግን ለሽ ብለህ ተኝተህ ታንኮራፋልኛለህ! አዎ ተኛ! የማያልቅ እንቅልፍህን በደምብ አድርገህ ለሽልሽ! ቆንጨራውን ይዞ ከፊትህ ላይ ሲቆም ያኔ አንገትህን ለማስቆረጥ ትነቃለህ! እስከዚያው ግን ተኛ እሽ? ተኛ ለምን ብለህ ትነቃለህ ተኛ!!!
“ኧረ አሸሸ ነው አሸሸ ዐቢይ መጣልን ከመሸ!” እያልክ እየዘፈንክም አይደል??? ጎሽ ደግ አድርገሃል ዝፈን! ጨፍር! እንደሱ እያልክ ጨፍር ምድረ ነፈዝ!!! ዐቢይ እና ለማ አንተን በመደመር በአንድነት በኢትዮጵያዊነት ነጠላ ዜማዎች በእንቅልፍህ ላይ እንቅልፍ ጨምረውልህ እንቅልፍህን ጣፋጭ አድርገው እያስለሸልሹ እነሱ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኝነትን በመገንባት ሥራቸውን በአስገራሚ ብቃት እየከወኑ ይገኛሉ እኮነው እያልኩህ ያለሁት፡፡ አንተ ደሞ እየዘፈንክላቸው በደንብ አድርገህ ተኛህ፡፡ አዎ ተኛ ለምን ብለህ ትነቃለህ??? አዎ ተኛ! የማያልቅ እንቅልፍህን በደምብ አድርገህ ለሽልሽ! ቆንጨራውን ይዞ ከፊትህ ላይ ሲቆም ያኔ አንገትህን ለማስቆረጥ ትነቃለህ! እስከዚያው ግን ተኛ እሽ? ተኛ ለምን ብለህ ትነቃለህ ተኛ!!! (ታዲያ ዐቢይ እና ለማን እንዴት እንመናቸው ??? ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው፤- ምንጭ Ethiopanorama ሰረዝ የተጨመረ)
አዎ በጊዜያዊ ምርቃና የተጠለፈው አብዮት ያልጠበቅናቸው ክስተቶች ገና ብዙ ያሳያናል።
ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay