============================
የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች እና የተከበራችሁ የኦ ኤም ኤን ተከታታዮች
ዛሬ የኦ ኦም ኤን ልኡካን ቡድን ለመቀበል በሻሻመኔ ከተማ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በታደሙት ፕሮግራም ላይ በሰው ብዛት ምክንያት በመረጋገጥ በደረሰው አደጋ የሰው ህይወት በማለፉና የአካል ጉዳት በመድረሱ የተሰማንን ከፍተኛ ሀዘን እንገልፃለን፡፡ ለተጎጂ ቤተሰቦች፤ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለህዝባችን መፅናናትን እንመኛለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ሁኔታዎችን ወደ ብትጥብጥ ለመቀየር የተንቀሳቀሱ ሀይሎች ሰላማዊ ህዝቡን ተገን በማድረግ የፈፀሙትን ርካሽና ኢሰብኣዊ ተግባር አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ይህ ድርጊት የሻሻመኔና አካባቢዋን ቄሮ ኣልፎም ሰፊውን ህዝብ የማይወክል መሆኑን እናምናለን፡፡ ድርጊቱን የፈፀሙት አካላትን መንግስት ተከታትሎ ለህግ እንዲያቀርብ በዚሁ አጋጣሚ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የኦ ኤም ኤን ዋና ዳይሬክተር ኣቶ ጀዋር መሃመድ ባደረጉት አስቸኳይ ዉይይት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ የኦ ኤም ኤን ልኡክ ያቃዳቸው የጉብኝት መርሃግብር ለጊዜው እንዲቋረጥ ወስነዋል፡፡
ለጉብኝቱ ዝግጅት ላይ የሚትገኙ ከተሞችም ይህን ሁኔታ በመረዳት ውሳኔያችንን በበጎ እንዲትወስዱ በትህትና እንጠይቃለን፡፡ ያለውን ሁኔታ አጥንተን የወደፊቱን መርሃግብር የምናሳውቅ መሆኑንም እንገልፃለን፡፡
ኦ ኤም ኤን
ነሃሴ 12 ቀን 2018