ሰኔ 16 ጠ/ሚንስትራችን ላይ ቦንብ ተወረወረ፤ 2 ሰው ሞተ፤ ብዙ ሰዎች ቆሰሉ፡፡ ወንጀለኞቹ ተይዘው ለህግ ቀረቡ፡፡ አንድ ዜጋ ሰውተን፣ የተወሰኑ ዜጎች አካላቸው ጎድሎ፣ ወንጀለኞቹን ለህግ አቅርበን እንደማህበረሰብ ያለንን ጥንካሬና ቀጣይነት አረጋገጥን፡፡ ማህበረሰባዊው ስርአት በቀላሉ ሊናጋ እንደማይችል አሳየን፡፡
.

ከትናንት በስቲያ ሻሸመኔ ላይ፣ ‹‹ቦንብ ሊወረውር ነው›› በሚል፣ አንድ ንጽህ ዜጋ ተገድሎ፣ ተዘቅዝቆ ተሰቀለ፡፡ የአውሬ ጭካኔና በተላበሱ ነውጠኞች በሚነዳ ነውጥ ሰው ተዘቅዝቆ ሲገደል፤ በአካባቢው የተገኘው ማህበረሰብ እንደታቦት አጀባቸው፡፡ ይህ በሻሸመኔ ብቻ አይደለም፤ በሌሎች በርካታ አካባቢዎችም ተፈጽሟል፡፡ ማህበረሰብ የሚደርስበትን ጥቃት የሚያቆመውና ደህንነቱን የሚያረጋግጠው የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ እንጂ፣ ያጠቁኛል ያላቸው ላይ፣ አውሬያዊ ‹‹ስብእና›› በተላበሱ ሰዎች በሚመራ ሞብ የሚፈጸምን ኢሰብአዊ ድርጊት በመፍቀድ አይደለም፡፡ ይህ ሲሆን ማህበረሰቡ አይቀጥልም፤ በስርአተአልበኝነት እርስ በርሱ ይጨራረሳል፤ እንደማህበረሰብ ይሞታል፡፡ . . . . የሻሸመኔው ቦንብ ውሸት መሆኑ ተረጋግጧል፤ እውነት ቢሆን እንኳን፣ ወንጀለኛው ከነቦንቡ ቢያዝ እንኳን፣ ገድለነው – ዘቅዝቀን ሰቅለነው – በመኪና ጎትተነው፣ ከሰለጠነ ሰብአዊ የአስተዳደር ስርአት ወጥተን፣ እንደ ማህበረሰብ ከመሞት፣ ቦንቡ ተወርውሮ፣ እንደግለሰብ ሞተን፣ ወንጀለኛውን ለፍርድ አቅርበን፣ እንደማህበረሰብ መኖር ሺህ ጊዜ ይሻላል፡፡ (በዚህና በአጠቃላይ በወቅታዊው ቡድናዊ ስርአተአልበኝነት ላይ በሚቀጥለው ቅደሜ በሚወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አንድ ጽሁፍ ይኖረኛል