በጅግጅጋ ከተማ ከተቃጠሉ ቤተክርሲቲያኖች መካከል

በሶማሌ ክልል በዋና ከተማው ጂግጂጋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የተፈፀመው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ከከፍተኛ ድብደባ በኋላ በሕክምና የተረፉት የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ገለፁ። በኢትዮጵያ ሶማሌ ሀገረስብከት በጂጂጋ ምስራቀፀሐይ ኪዳነምሕረት ካቴድራል አስተዳዳሪ መላከፀሐይ አባገብረፃዲቅ ደባብን አነጋግረናቸዋል።

በሶማሌ ክልል በዋና ከተማው ጂግጂጋን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የተፈፀመው ጥቃት እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ከከፍተኛ ድብደባ በኋላ በሕክምና የተረፉት የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ገለፁ።

የክልሉ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ በበኩላቸው ፤ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ተቆራርጠዋል በእሳት ጨምር ተቃጥለዋል ብለዋል። “በክልሉ በዜጎች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ወንጀል ሰው ሆኖ ከተፈጠረ የማይጠበቅ ነው።” ብለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ) VOA Amharic