በጎሕ ላይ ላለመጻፍ ፈልጌ ነበር፤ ግን አንዳንዴ ዓይን ያወጣ ቅጥፈት ሲኖር ዝም ማለት ሞራላዊ ባለመሆኑ የግድ ይህን ልጽፍ ተገደድኩ፡፡ የማውቃቸው ጥቂት የጎሕ አባላት ጥሩ ግለሰባዊ ባሕሪያት ያላቸው አሉ፤ በዚህ ጥፋት ውስጥ ይኑሩበት አይኑሩበት አላውቅም፡፡ ነገር ግን እስካሁንም ዝም ማለታቸው ከጥፋቱ ከተጠያቂነት የሚያድናቸው አይመስለኝም፡፡
ፕሮፌሰር ዓለማንተን ጨምሮ ብዙ የጎሕ አመራሮችን አወያይቻቸው አውቃለሁ፤ የአማራ ተጋድሎ ተቀጣጥሎ በነበረበት ወቅት ብዙዎቹን አግኝቻቸው እርዳታ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸውልኝ ነበር፤ በኋላ መሬት ላይ ሳረጋግጥ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት፡፡ ይህንም ለምቀርባቸው ሰዎች ገልጨላቸዋለሁ፡፡ በሁሉም አህጉራት ከግማሽ ሚሊዮን የአማሪካን ዶላር በላይ ገንዘብ ስብሰበዋል፡፡ በአሜሪካ ሲአትል፣ ዳላስ፣ ዲሲ፣ ቶሮንቶ፣ በአውሮፓ ደግሞ በፍራንክፈርት፣ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከ500 ሺህ በላይ ዶላር ተሰብስቦ ሕምጥ ይግባ ስምጥ አይታወቅም፡፡ የገንዘቡን መጠን የምናገረው ከሲአትል ስብሰባ በኋላ የአገኘሁት የጎሕ አመራር ቃል የተገባውን ጨምሮ እዚያ በላይ እንደሆነ በነገረኝ መሠረት ነው፤ ያን ጊዜ የገንዘብ መጠን መዋጮ መብዛት የድርጅቱን ትልቅነት ይገልጻል በሚል አብረን እንድንሠራ ሲያግባባኝ ነው፡፡
አንድ ጊዜ ከሜልቦርን የአማራ ተወላጆች ወደ 30 ሺህ የሚጠጋ ገንዘብ ተሰብስቦ ወደ ታጋዮች ለማስገባት አነጋገሩኝ፤ መንገዱን ነገርኳቸው፡፡ በኋላ ያነጋገሩኝ ልጆች ለጎሕ መስጠታቸውን ገለጹልኝ (ካነጋገሩኝ ውስጥ ሲሳይ የሚባል ልጅ ነበር)፡፡ በእነርሱ በኩል ደርሷል አሉኝ፡፡ መሬት ላይ ግን ባዶ እንደነበር በጊዜው ባውቅም ከነገ ዛሬ ይሻሻላል በማለት ዝም አልኩ፡፡ በሌላም ግዜ አንድ ዲሲ የሚኖር ወንድሜ የጎንደር ሕብረት ገንዘብ ወደ ታጋዮች እንዲሔድ መንገድ ይፈልጋሉ ብሎኝ ችግር የለም የሚል መልስ ሰጠኹት፡፡ ሲያነጋግራቸው ‹‹አንተ መሆንህን ሲያውቁ ትተውታል›› አለኝ፡፡ ያልገባው ነገር እንዳለም ጭምር በመግለጽ፡፡ በእኔ በኩል ከሆነ በደንብ እንደምረዳቸው ስለሚገምቱ ነው፡፡
ጎቤ ከመሞቱ በፊት ደግሞ ጎቤን ቀለቡን የምንሠፍርለት እኛ ነን አለኝ አንዱ የጎሕ አመራር፤ ጎቤን ስጠይቀው ደግሞ ከማንም ምንም እንደማያገኝ ገለጸልኝ፡፡ ለዚህ ምስክሬ ከሞት የተረፈው ዘመነ ምሕረት ነው፡፡ የጎሕ ገንዘብ የተላከ የማውቀውና የደረስኩበት አዲስ አበባ አካባቢ ለአንድ አክቲቪስት ስንት መቶ እንደሆነች በደንብ ያላወቅኳት ገንዘብና በሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ ባነር ለማሠራት የተላከ ብቻ ነው፡፡
እንግዲህ ይህን ያክል ገንዘብ የት እንደገባ እንኳን በማይታወቅበት ሁኔታ ራስን የለውጥ ሃውሪያ ማስመሰል ሳያንስ በቅርብ ከእስር የተፈቱ ልጆችን በጥቅም በመደለል እንደገና የአማራውን ትግል ወደ ኋላ መመለስ እጅግ አስነዋሪ ነው፡፡ እኛ የቀረን አንደኛው ሀብት ቃል ነው፤ እምነት ነው፡፡ የባለማተቡ ጎንደሬ ልጆች ነን በሚሉት ሰዎች እምነት ሲጎድል ደስ አይልም፡፡ በጣም ይደብራል፤ የሕዝብን ሞራል ይገድላል፡፡ በወጣው ገንዘብ እንኳ አንድ ሆስፒታል ወይም ትምህርት ቤት ቢሠሩበት ምን ነበር! አሊያም አሠርተው ከሆነም ሪፖርት ቢያቀርቡልን፡፡
በነገራችን ላይ የጎሕ ብቻ ሳይሆን በአማራ ስምም የተለመነ ገንዘብ የት እንደደረሰ የግድ መታወቅ አለበት፤ በግልጽ በዚህ መልኩ አደፍርሰን ካላጠራነው የሚጠልፈው ብዙ ነው፡፡ ማንም ችግር ያለበት ካልሆነ ይህን የሚቃወም አይኖርም፡፡
ይህ ጀግና የአማራን ብሎም የኢትዮጵያን ፖለቲካ እስከ መቅኔዉ ነዉ የሚያቀዉ።
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በስሙ ለሚነግድበት ይቅር እና ከባድ መሳርያ ለታጠቀ ጦር ወደኋላ እንዳላለ መታወቅ አለበት!
ማንኛውም በሕዝብ ደምና አጥንት የሚነግድ፣ የሕዝብ ትግል ላይ የሚቆም ፊት ለፊት ሊነገረው ይገባል!
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የጎንደር ሕብረት ገንዘብ ልኬለታለሁ የሚለው ሀሰት መሆኑን፣ ወጣቱም በገንዘብ እንዳይገዛ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።
“ጎህ የሚባል አላቅም ” ብሎ አዳራሹን በድጋፍ ጩኸት ያነቃነቀዉ ኮ/ል ቀጥሎም ይህን ይናገራል።
“~”የአማራን መደራጀት የሚቀበል ከሆነ ሰይጣንም ቢሆን አብረነው እንሰራለን፣ የአማራን መደራጀት የማይቀበል ከሆነ መላዕክም ቢሆን አብረነው አንሰራም”
~አንዳንዶቹ ኮ/ል ደመቀን ይህን ገንዘብ ላክንለት ሲሉ እሰማለሁ። አልደረሰኝም። ልኬለታለሁ የሚል ካለ ከዚህ ቀርቦ ለኮ/ል ደመቀ ይህን ያህል ላኩለት ብሎ መናገር ይችላል። ከእናንተ የምደብቀው ነገር የለም። እኔ ለጥቅም፣ ነገም ከነገም በኋላ በጥቅም አልቆምም። ዛሬ ነው በፌስቡክ የማየው ። ለኮ/ል ደመቀ 30ሺህ፣ ለንግስት ይህን ያህል ሺህ ልኬያለሁ እንዳለ ተፅፏል። እውነት አይደለም። ጎንደር ሕብረት የሚባለው ለእኔ 30 ሺህ ቀርቶ አንድ ሽህ ብር አልሰጠኝም። መጀመርያ እኔ የጎንደር ሕብረትን የምደግፋቸው የአማራን ሕልውና የሚቀበሉ፣ በብሄርተኝነት እንዲደራጅ የሚቀበል ከሆነ ብቻ ነ! ”
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ
“አማራ ኢትዮጵያን አላገኘም፣ አማራን አላዳነም፣ ተንሳፍፈናል። ከአሁን በኋላ አማራ ነኝ ማለት ኩራት፣ መልካም እንደሆነ ለማሳየት አማራ በማንነት መደራጀት ይኖርበታል። አንዳንድ ወገኖች አማራ በብሔር እንዳይደራጅ ሲሰብኩ ቆይተዋል።በዚህ ጦር ነው አማራ እንደ በግ ሲጎተት የኖረው። ለውጥ ስንደግፍ አማራነታችን፣ ማንነታችን፣ ድንበራችን፣ ጥቅማችን ተከብሮ ነው መደመር የምንፈልገው። ለአማራ ብዙ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ስንደመር ቢያንስ የአማራን ማንነት እውቅና የሚሰጥ መሆን አለበት። የአማራ ሕልውናን የሚያምን ሁሉ ሰይጣንም ይሁን አብረን እንሰራለን። የአማራን ህልውና የማያምን፣ አማራ መስሎ ሰይጣናዊ ስራ የሚሰራ ካለ መዕላክም ቢሆን አብረነው አንሰራም። የአማራ ወጣት ስም እየነገደ፣ በገንዘብ አስራ አራት ቡድን አደራጅቶ የሚመጣ፣ አማራ ካለ፣ አሁንም እንቃወማለን! ግለሰብ ይሁን ድርጅት መጀመርያ ስለ አማራ ያለውን አቋም ማወቅ አለባችሁ። የአማራን ሕልውና የሚቀበል ከሆነ ብቻ አብራችሁት ስሩ። የማያምነውን አትቀበሉ። ኢትዮጵያዊ ከሆነ በቂ ነው ይል ነበር አማራ። አሁን ከውስጥ ው ውጭ መለየት አለብን። አማራ ክልል ተብሎ፣ አማራ ላይ ተወልዶ ለምሳሌ ከሽሬ አንድ ፍሬ አመጣች፣ አማራ መሬት ላይ በቀለ። ብርቱካኑ የአማራ ነው። አንድ የትግራይ ሰው ጎንደር ወልዶት እኛ አሳድገነው፣ አባቱ ትግሬ ስለሆነ ብቻ የአማራ ሕዝብ ስልጣን ሰጥቶት የሚሰራው ለትግራይ ነው። ይህን የሰራው ህወሓት ነው። የትግራይ ተወላጆች ካላችሁ፣ እናታችሁ አማራ አባታችሁ ትግራይ ከሆነ ወይንም አባታችሁ ትግራይ፣ ለምን አላስገቡንም ብለችሁ አትቀየሙ። እባብ ያየ በልጥ ደነገጠ ነው። ትናንት ጎንደርን ያህል አብረው ደጋፊ መስለው መኪና እንዲቃጠል ያደረጉ ጎንደር የተወለዱ ነገር ግን የህወሓት ደህንነቶች ነበሩ። ለዚህም መሰለኝ የወጣቶቹ ማህበር መስፈርት አማራ ብቻ ብሎ መስፈርት ያስቀመጠው። ቅሬታ እንዳይሰማችሁ። እኛ ለትግራይ ሕዝብ ጥላቻ የለንም። የሚከፋፍሉ ቡድኖችን ግን አሉ። ከአጎቶቻችሁ፣ ከአክስቶቻችሁ እያቆራረጧችሁ ነው። ከአማራ ተወልዳችኋል፣ በአማራ በጀት ተምራችኋል፣ በአማራ ክልል ስልጣን አላችሁ። ለአማራው ስሩ! ወጣቱ ለሆዳቸው ከሚኖሩት ተጠንቀቁ። ወጣቱ ጥላቻ ሳይኖረው መጠንቀቅ አለበት። ……ወጣቶች ከይሉኝታ፣ ከጓደኝነት፣ ነፃ መሆን አለበት። አማራዊ ጉዳይ አላማ ነው። እኔ እንድኖር ያደረገኝ ይህ ወጣት ነው። እንድንፈታ ያደረጋችሁን እናንተ ናቸው። ሕዝብ ነው! ይህ ሕዝብ ነው። ጎንደር ወጣቱን ለመከፋገል እየተሰራ ነው። ከእስር የተፈታነው ተገርፈናል ብለን የምንናገረው ለማስተማር ነው እንጅ አማራ ተገረወፌያለሁ ብሎ መናገር ሀፍረቱ ነው። እናንተ ተገረፍን ስትሉ መስማት አልፈልግም። ከህግ ውጭ መጥቶ ማንም ከእየ ቤቱ እየመጣ እየለቀመ እንዲወስድ አትፍቀዱ።
አማራ መጀመርያ የሚፈራው እግዚያብሄር፣ አላህን ብቻ ነው። የሚያከብረው ህግንና አባትና እናቱን ነው። ከዚህ የተረፈው በሕግ መሆን አለበት። ለመግደል የሚመጣ አካል ሁሉ እንደ እኔ ህይወት ይዞ ነው የሚመጣው። በስሜት እንዳንነዳ፣ ሁሉን ነገር በማስተዋል ማድረግ አለበት። አባቶችን አማክሩ። በስሜት ከተነገዳን አላማ እንስታለን። አማራ ትልቅ ሕዝብ ነው፣ ነገም ትልቅ ይሆናል። በጥቅማጥቅም እንዳንደለል። አንዳንዶቹ ኮ/ል ደመቀን ይህን ገንዘብ ላክንለት ሲሉ እሰማለሁ። አልደረሰኝም። ልኬለታለሁ የሚል ካለ ከዚህ ቀርቦ ለኮ/ል ደመቀ ይህን ያህል ላኩለት ብሎ መናገር ይችላል። ከእናንተ የምደብቀው ነገር የለም። እኔ ለጥቅም፣ ነገም ከነገም በኋላ በጥቅም አልቆምም። ዛሬ ነው በፌስቡክ የማየው ። ለኮ/ል ደመቀ 30ሺህ፣ ለንግስት ይህን ያህል ሺህ ልኬያለሁ እንዳለ ተፅፏል። እውነት አይደለም። ጎንደር ሕብረት የሚባለው ለእኔ 30 ሺህ ቀርቶ አንድ ሽህ ብር አልሰጠኝም። መጀመርያ እኔ የጎንደር ሕብረትን የምደግፋቸው የአማራን ሕልውና የሚቀበሉ፣ በብሄርተኝነት እንዲደራጅ የሚቀበሉ ከሆኑ ብቻ ነው። መጀምርያ የእነሱ አላማ ጤነኛ ከሆነ ነው የምቀበለው። …አማራን በጠላት የሚፈርጀውን መቼም ቢሆን የአማራ ወጣቶች ይቀበሉታል ብየ አላምንም”