የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ ቀለማት ምሳሌዎች በሚከተሉት ቃላት ተገልጸዋል (ዊኪፔድያ)። አረንጓዴው ተስፋ፣ ልምላሜና ሀብት፤ ብጫው ፣አበባና ፍሬ፤ ቀዩ ፣ መሥዋዕትነትና ጀግንነት። ባልሳሳት፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ይታተሙ በነበሩት ታሪክና ምሳሌ መድብለ-መጻህፍትየጀርባ ሽፋን ላይ ከተጻፈው ላይ ቀዩ ፍቅርን ጭምር እንደሚያመለክት ይገለጽ ነበር።
የዓለም ባንዲራዎች (“Flags of the World”) በተባለ የባንዲራዎች መዝገበ-ቃላት (Encyclopedia) የኢትዮጵያን ባንዲራ በዓለም ሁሉ ካሉባንዲራዎች “ምናልባትም ከሁሉ በላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ” (perhaps the most influential) ሲል ይገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የፀረ-ቅኝ-ግዛትተጋድሎ በቅኝ ግዛትና በጭቆና ሥር በነበሩ የአፍሪቃ፣ የደቡብ አሜሪካና የካሪብያ ሀገሮች እንደንጋት ኮከብ ይታይ ስለነበር፤ ነፃነታቸውን ሲቀዳጁብዙዎቹ በተለያዩ ቅርጾችና አደራደሮች እነዚህን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ ሶስት ቀለማት ሁሉንም፤ ወይም በከፊል (አንዳንዶቹም ከሌሎችቀለማት ጋር በማሰባጠር) ተጠቅመውባቸዋል።
አንዳንዶችም በቅርቡ በተደረጉ የመንግሥት ግልበጣዎች እንዲቀየሩ ተደርገዋል። ለምሳሌ፤ ሩዋንዳን ብንመለከት ቅኝ ገዦችን ያስወገደውትውልድ የመሰረተው መንግሥት በ1986 ዓ.ም. በኃይል ሲወገድ፤ የነፃነት ምልክት ተደርጎ ተወስዶ የነበረው የሀገራችን የሶስቱ ቀለማት ባንዲራተቀይሮ፤ ቀዩ በዉሃ ሰማያዊ እንዲቀየር ተደርጓል። በዉሃ ሰማያዊው ላይ ደግሞ በብጫ የተሳለ ኮከብ ወይም ጸሐይ መሰል ቅርጽ አርፎበታል።የሚገርመው በኢትዮጵያም የሆነው ተመሳሳይ ነው። ተመሳሳይ ዉሃ ሰማያዊ ቀለም (በላዩ ብጫ ኮከብ) በኢትዮጵያ ባንዲራም እንዲጨመርተደርጓል። እንደነመለስም አመጣጥ ባንዲራውን እስከነአካቴው የመለወጥ ዓላማ ይዘው ላለመምጣታቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም።መለስ ሥልጣን እንደያዘ ለተናገረው የባንዲራ ንቀት የተሞላበት ቃል ሕዝባችን ግዙፍና ቅጽበታዊ አጸፋ ሰጥቶ ባይሆን ኖሮ የኛም ባንዲራ እጣፈንታ ያው የሩዋንዳው ዓይነት ይሆን ነበር። በዚያ ወቅት በመገናኛ ብዙኃን የተዘገበውን ብቻ ብናስታውስ ብዙ የአዲስ አበባ ወጣቶችሕይወታቸውን ከፍለዋል።
የሚገርመው ደግሞ፤ በኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ባንዲራ ይህ ዉሃ ሰማያዊ ቀለም በቅርቡ ደግሞ ወደደማቅ ሰማያዊ (navy blue) ተቀይሯል፤መጠኑም ከፍ ብሏል። የቀለሙ ትርጉም ምን እንደሆነ እስካሁን ድረስ የሰማነው ወይም የምናውቀው የለም። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በነበረው ጦርነት ወቅት፤ ካልጠፋ ሃገርና ጎረቤት ሩዋንዳ ሸምጋይ ተብላ መመረጧ ከመንግሥት ግልበጣውና ከባንዲራ ቅየራ ጋር ለዚያውምዉሃ ሰማያዊ ቀለም አብረን መምረጣችን ግራ ከማጋባት የዘለለ ትርጉም ይኖረው ይሆን? ያሰኛል። የአሁኑን አያርገውና መሪዎቻችንም በአፍላዘመናቸው “አዲሶቹ የአፍሪካ መሪ ዝርያዎች” (the new breed of African leaders) ተብለው ተንቆለጳጵሰው ነበር። “Breed” የተባሉበትን ቃልለእንስሳትና ለአዝርዕት ቢሆን ድቅል ዝርያዎች እንላቸው ነበር። ግን እነሱን ትተን አመራራቸው ከማን እንደተደቀለ ሰያሚዎቻቸው ቢፈቱልን ደስይለን ነበር።
የዚህ አጭር ጽሁፍ ዓላማ ታሪካዊውን (ጥንታዊውን) የኢትዮጵያን የሕዝብ ባንዲራ በኢህአዴግ ዘመን ተግባር ላይ ከዋሉት ባንዲራዎች ጋርያለዉን ምስስል ለመገምገም ነው። ለሁሉም ሰንደቆች (ባንዲራዎች) ማነጻጸሪያ ተደርጎ ተግባር ላይ የዋለው ጥንታዊው የኢትዮጵያ ሕዝብባንዲራ (አረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ አግድም ያሉት) ነው። ሕዝባዊነቱ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታው፣ በሃዘኑ፣ በዘመቻው፣ በፀሎት ቤቱ፣በመንግሥት ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶች፣ ወዘተ ያውለበልበው የነበረውንና በኢህአዴግ ዘመን ሕዝብ ሳይጠየቅ አስገዳጅ አርማያልተጨመረበትን ለማለት ነው። ኢትዮጵያን የመበታተን ዓላማ ያላቸው (ወይም የነበራቸው) የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመመሥረታቸውና ሕዝቡንከመከፋፈላቸው በፊት ህዝቡ ካለማንም አስገዳጅነት ይይዘው የነበረ መሆኑ ለሕዝባዊነቱ እንደማስረጃ ተወስዷል። ጥንታዊነቱም እንደዚያውከታሪክ እንደምንረዳው ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈ ታሪክ፤ (ሌሎችም እንደ ዶ/ር ዮሐንስ ዘለቀ ያሉ የታሪክ ባለሙያዎች እስከ 12ኛው ክፍለዘመን ድረስ ያደርሱታል) ጀምሮ ዕድሜ ያለው ባንዲራ ስለመሆኑ የተባለ ነው። የኢትዮጵያ የተባለበትም ምክንያት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርናኢትዮጵያዊ የሚባል ባንዲራዉን ሲጠቀምበት የነበረ፣ ያለና የሚኖር ሕዝብ ስላለ ግልጽ ነው። በመሆኑም፤ ሕዝቧ እገሌ ከእገሌ ሳይለይሉዓላዊነቷን፣ ክብሯንና ጥቅሟን ለማስከበር መሰባሰቢያ ዓርማው አድርጎ እስከከፍተኛው የሕይወት መስዋዕትነት የከፈለበት በመሆኑ ነው።ከላይ የተጠቀሱት ዓይነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመመሥረታቸው በፊት “ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” ብለው ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉኤርትራውያን አባቶቻችንን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ባንድነት ያውለበለቡት፣ የዘመሩለት፣ የተሰዉለትና እንደብቸኛ አሰባሳቢ አርማ የቆጠሩትባንዲራ ነው እንግዲህ የዚህ ጽሁፍ መመዘኛ የተደረገው። ይህችን ሀገር የመሰረቷትና ያስረከቡን ከረጂም ትውልዶች በፊት የነበሩ የቅድማያትቅድማያት … ቅድማያቶቻችን ቢሆኑም፤ የቅርቦቹ አያቶቻችን የጠበቋትንና ያስከበሯትን ሀገርና ወድቆ የተነሳውን ባንዲራዋን (ትውልዶችደግመው ደጋግመው ከወደቀበት ያነሱት መሆኑ ይሰመርበት፣ ያሁኑን ትውልድ ጨምሮ) መስዋዕቶቹ በሌሉበት ያስረከቡንን ሀገር ባንዲራማዋረድ ክህደት በመሆኑ፤ የሰጡንን ሀገር በሰጡን ባንዲራ ማቆየት የትውልዳችን ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን ከግምት በማስገባት ለዚህ ምዘናታሪካዊውን የሕዝብ ባንዲራ ጥቅም ላይ አዉያለሁ።
የተጠቅምኩባቸው መመዘኛዎች የሚከተሉት ናቸው።
1) የቀለማት ስብጥር ምስስል፤
አረንጓዴ፤ 3.33፣ ብጫ፤ 3.33፣ ቀይ፤ 3.33፣ ድምር፤ 9.99።
አንድ ሌላ ተጨማሪ ቀለም እንደአንድ ቀለም ጉድለት ተቆጥሯል። ሆኖም ከዜሮ በታች አይሰጥም። ለምሳሌ አንድ ባንዲራ ከሶስቱ ቀለማትአንዱን ቢኖረውና ሌሎች ከሶስቱ ውጭ የሆኑ ሁለት ቀለማት ቢኖሩት፤ ከላይ በተመለከተው ሂሳብ ቢሆን ከዚሮ በታች 3.33 የሚሰጠውቢሆንም፤ ከተቀሩት ነጥቦቹ እንዳይቀነስበት ለመከላከል ሲባል፤ ዜሮ ነጥብ ብቻ እንዲያዝለት ይደረጋል ማለት ነው።
2) የቀለማት ቅርጽ (አቀማመጥ) ምስስል፤
ለእያንዳንዱ ቀለም አግድም መሆን 3.33፤ ድምር፤ 9.99።
3) የቀለማት ቅደም ተከተል ምስስል፤
ለምሳሌ፤ አረንጓዴ በመጀመሪያ፤ 3.33 (በስተግራ ወይም ከላይ)፣ ብጫ ከመካከል፤ 3.33፣ ቀይ በሶስተኛ ወይም በመጨረሻ፤ 3.33 (በስተቀኝወይም ከታች)፣ ድምር፤ 9.99።
ከነዚህ ቅደም ተከተሎች ለእያንዳንዳቸው ቀለማት አንድ ደረጃ መዘብረቅ፤ 1.11 (ሲሶውን) እንቀንሳለን። ለምሳሌ አረንጓዴ በሁለተኛ ደረጃቢቀመጥ፤ 2.22፣ በሶስተኛ ደረጃ ቢቀመጥ ደግሞ 1.11 ይሰጠዋል ማለት ነው። ቀዩም ከመካከል ቢሆን 2.22፣ በመጀመሪያ ቢሆን ደግሞ 1.11 ይሰጠዋል ማለት ነው።
አንድ ቀለም ቢደገም ለሁለቱ የሚሰጡ ሁለት ዋጋዎች አማካይ ይሰጠዋል ማለት ነው። ለምሳሌ ቀይ ሁለት ጊዜ (አንድ ቀይ ከላይ ወይም ከግራ፤ሌላ ቀይ ደግሞ ከታች ወይም ከቀኝ) ቢኖር፤ 3.33+1.11=4.44/2 = 2.22 ይሰጠዋል ማለት ነው። በሌላ አንጻር፤ ከሶስቱ አንዱ ቀለም ከላይእስከታች ቢዘረጋ፣ 3.33+2.22+1.11=6.66/3 = 2.22 ይሰጠዋል ማለት ነው።
ከቀለማቱ አንዱ በቀስት መልክ ቢቀመጥ አንደ መጀመሪያ ይቆጠራል። ስለዚህ አረንጓዴ በቀስት መልክ ቢቀመጥ፤ 3.33፤ ብጫ በቀስት መልክቢቀመጥ፤ 2.22፤ ወይም ቀይ በቀስት መልክ ቢቀመጥ፤ 1.11 ይሰጠዋል ማለት ነው። አመዛዘናችን እንዳይለያይ ለማድረግ ሲባል፤ ከቀስቱ ውጭያሉት ቀለማት (ቀስቱን ባልቆጠረ መልክ) በደረጃ ይመዘናሉ። ለምሳሌ ቀስቱ ቀይ ቢሆንና፤ አረንጓዴ ከላይ በሆን፣ ለቀዩ 1.11 እንዲሁምለአረንጓዴው 3.33 ይሰጠዋል ማለት ነው (አረንጓዴውን እንደሁለተኛ አልቆጠርነዉም ማለት ነው፣ ምንም እንኳ ቀዩን ቀስት የመጀመሪያ ብለንብንቆጥረው)።
4) የአርማዎች ቀለማት እንደጉልህነታቸው ተቆጥረዋል፤ አደራደራቸውና አቀማመጣቸው ግን ለዚህ ጽሁፍ ሲባል እንደሌሉ ተወስደዋል።
የባንዲራው ተጠቃሚ | የባንዲራው ምስል | የቀለማት ስብጥርምስስል (ክ9.99) | የቀለማት ቅርጽወይም አቀማመጥምስስል (ከ9.99) | የቀለማት ቅደምተከተል ምስስል(ከ9.99) | አማካይ ምስስል(ከ9.99) |
ጥንታዊው የኢትዮጵያሕዝብ ባንዲራ(መመዘኛ) |
|
9.99 | 9.99 | 9.99 | 9.99 |
ኦፊሴላዊው የኢትዮጵያባንዲራ |
|
6.66 | 9.99 | 9.99 | 8.88 |
የአፋር ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
0 | 3.33 | 2.22 | 1.85 |
የአማራ ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
6.66 | 0 | 4.44 | 3.7 |
የቤንሻንጉል ጉሙዝብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
6.66 | 6.66 | 1.11+3.33+1.11=5.55 | 6.29 |
የጋምቤላ ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
0 | 6.66 | 2.22+3.33=5.55 | 4.07 |
የሐረሪ ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
3.33 | 6.66 | 0 | 3.33 |
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
0 | 3.33 | 1.11 | 1.48 |
*ሌላው በኦነግ ደጋፊዎችተዘውትሮ የሚያዘውባንዲራ (ለማነጻጸሪያ)* |
|
9.99 | 6.66 | 2.22+2.22=4.4 | 7.03 |
የኢትዮጵያ ሶማሌብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
6.66 | 6.66 | 2.22+3.33+3.33 = 8.88 | 7.4 |
የደቡብ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦችክልል መስተዳድር |
|
0 | 3.33 | 3.33 | 2.22 |
የትግራይ ብሔራዊ ክልልመስተዳድር |
|
6.66 | 3.33 | 2.22+2.22=4.44 | 4.81 |
ለማነጻጸር ይረዳን ዘንድ እስቲ አማካይ ውጤቶችን ብቻ ቁልቁል ሰድረን እንይ።
ባንዲራ | አማካይ ምስስል(ከ9.99) |
ጥንታዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ (መመዘኛ) | 9.99 |
ኦፊሴላዊው የኢትዮጵያ ባንዲራ | 8.88 |
የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 7.4 |
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 6.29 |
የትግራይ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 4.81 |
የጋምቤላ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 4.07 |
የአማራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 3.7 |
የሐረሪ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 3.33 |
የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 2.22 |
የአፋር ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 1.85 |
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ | 1.48 |
*በኦነግ ደጋፊዎች ተዘውትሮ የሚያዘው ኢ-ኦፊሴላዊ ባንዲራ (ለማነጻጸሪያ)* | 7.03 |
ሁለተኛው ዝርዝር እንደሚያሳየው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ ከሁሉም በላይ የሚቀርበው ኦፊሴላዊው ባንዲራ ነው። ከዚያም ቀጥሎ ከላይበተጠቀሱት መመዘኛዎች መሠረት ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔራዊ ክልል መስተዳድር ባንዲራ ነው። ከዚያም የቤንሻንጉል ጉሙዝባንዲራ ነው።
ቀጥሎ ያለው ደግሞ የትግራይ ብሔራዊ ክልል ባንዲራ ነው። እንዲህ እያለ እያቆለቆለ ይሄዳል። ከዚህ የሚታየው ሌላው ሐቅ ደግሞ ከሁለቱበቀር ሌሎቹ የክልል ባንዲራዎች ከጥንታዊው የሕዝብ ባንዲራ ጋር ያላቸው መመሳሰል በነዚህ መመዘኛዎች መሠረት ከግማሽ በታች ነው።በሕዝብ ብዛት ቢታይ ደግሞ 90 % ያህሉ ሕዝብ የሚኖርባቸው ክልሎች የተወከሉት ከሀገሪቱ ባንዲራ ጋር ከግማሽ ያነሰ መመሳሰል ባላቸው ባንዲራዎች ነው።
አሁንም ከላይ እንደሚታየው፤ የክልል ባንዲራዎች በአመዛኙ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ እንዲርቁ ተወስኖ የተዘጋጁ በሚመስል ደረጃመቀረጻቸው አስገራሚም አስተዛዛቢም ነው። በተለይ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ የኦሮሞው ልጆች በሰላም ጊዜና በየጦር ሜዳው ለሃገራቸውየከፈሉትን መስዋዕትነት በጣም ዝቅ ባደረገ መልኩ መቀረጹ ኢህአዴግ ሥልጣን እንደያዘ በኦህዴድ ዉስጥ የነበሩ ባለሥልጣኖች ምን ያህልኦሮሞውን ከኢትዮጵያ የማፋታት አባዜ የተጠናወታቸው እንደነበሩ ነው። የሚገርመው የኦሮሚያ ክልል ኦፊሴላዊ ባንዲራ፤ ከግብጽ ባንዲራ ጋር 100 % ተመሳሳይ ነው (ከአርማው በስተቀር)። እዚህ ላይ ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ፤ ለኦሮሞው ሕዝብ በታሪክ፣ በስነ ልቡና፣ ወዘተ የምትቀርበው ግብጽ ናት? ወይስ ኢትዮጵያ? ሌላው ደግሞ ለብዙዎች ላይከሰት የሚችል ጉዳይ፤ ከላይ እንደተመለከተው በኦነግ ደጋፊዎችየሚዘወተረውን ባንዲራ ስናየው፤ ከኦፊሴላዊው የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር ባንዲራ በተቃራኒው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ በጣም የቀረበሆኖ እኛገኘዋለን።
የክልሎች ባንዲራዎች ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባንዲራ ጋር የሚኖራቸው መተሳሰርና መቀራረብ ለአንድነታችን እንደጠንካራ ምልክት ሊያገለግልይችላልና ለማስተካከል ቢታሰብበት መልካም ነው ያስብላል። የኢትዮጵያ ባንዲራ ዝም ተብሎ በዋዛ ፈዛዛ የሚታይ ባንዲራ አይደለም።ከሌሎችም የሚለይባቸው ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩት ቢችሉም የሚከተሉትን ልጠቅስ እወዳለሁ። የመጀመሪያው፤ በዘመናችን ካሉ ባንዲራዎችበአፍሪካውያን የተፈጠረ “ኦሪጂናል”፣ ጥንታዊና ምናልባትም ብቸኛው ባንዲራ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው (የታሪክ ባለሙያዎች አንድ ሊሉበትይችላሉ)። ሁለተኛው ምክንያት፤ ባንዲራው የሚወክለው የኢትዮጵያ ነፃነትና ሕልውና በብዙ መስዋዕትነት የተጠበቀ፤ ይህም መስዋዕትነትእስካሁኗ ሰዓት የቀጠለ ነው። ሶስተኛው ደግሞ፤ ሌላው ቢቀር የዓድዋ ጦርነት የተመራው በዚህች ባንዲራ ሥር ነበር። የዓድዋ ድል ደግሞበአፍሪካውያን ታሪክ ዘለዓለም ሲያንጸባርቅ የሚኖር ድል ነው። ፍሬው ግን ካለመስዋዕትነት ተጠብቆ የማይኖር ነው። ለዚህም ባንዲራውወሳኝ ነው፤ “የኋላው ከሌለ አይኖርም የፊቱ” እንዲል ድንቁ የሙዚቃ ባለሙያ፤ ቴዎድሮስ ካሳሁን (እግረ መንገዴን፤ በኔ እምነት ታሪክና ባህልምአዋቂ ነው)።
የሩቁን ትተን የሰሞኑን እንኳ ብናይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ፣ ከዚያም የቀጠሉት ግድያዎች ከኢትዮጵያ ሕልውና ጋርበቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው። የነዚህን የምናያቸውና ያላየናቸው፤ ግን የሰማንላቸው ኁልቆ-መሳፍርት የሌላቸውሰማዕታት ሁሉ አስተሳሳሪ አርማ ደግሞ ባንዲራችን ነው፣ “እኛ ኢትዮጵያውያን ስንኖር ኢትዮጵያዊ፤ ስንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ ነን” እንዲሉ ዶ/ርዐብይ አሕመድ። ስለሆነም ባንዲራ ክቡር ነው! ሌሎችም ምክንያቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ርቱዕ አንደበትና የተባ ብዕር ያላችሁ ኢትዮጵያውያንወገኖቼ ተጨማሪ ሐቆችን በመጨመር ውይይቱን ብታዳብሩት መልካም ይሆናል።
ይህ ጸሐፊ እንደሚያምነው፤ ከዚህ በላይ የተመለከቱት መመዘኛዎች ከስሕተት የጸዱ፣ ወይም ብቸኞቹ ባይሆኑም፤ በነሱ በመመርኮዝ የተደረሰበት ድምዳሜ ለውይይት መሠረታዊ መረጃ በመስጠት ያግዛል። ውይይቱ ወደተሻለ መግባባት ለምናደርገው ጉዞ ትንሽ ድጋፍ ይኖረዋል የሚል እምነት አለኝ
ለአሁን አበቃሁ።