የኢሳቱ መሳይ መኮንን ለካ ዋናው ቅጥረኛ ኖሯል!!! ማስመሰሉን ትቶ ሚዛናዊነት የሚባል ነገር ጨርሶ ራቀው እኮ! ፈጽሞ ሞያዊ ሥነምግባር በራቀው መልኩ በይፋ የዐቢይ ወኪል በኢሳት ሆኖ ቁጭ ሲል የታወቀው አልመሰለኝም፡፡ ዐቢይን ለመከላከል እያለ የሚሔድበት ርቀት በጣም የሚገርም ነው፡፡
ለምሳሌ በዚህ ሰሞኑን በሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በአገዛዙ ዓይን ያወጣና ነውረኛ ሸፍጥ ለመከራ፣ ለሰቆቃ፣ ለውርደት፣ ለእልቂት በተዳረጉበት የሶማሌው ቀውስ ዐቢይ “ቀውሱን ለመከላከልና ለማስወገድ እጅግ አድካሚ ሥራ በመሥራት ላይ ነው ተጠምደን የሰነበትነው!” ብሎ በመናገር እንዳላገጠብን እየሰማ እሱ ግን “በሌሎች ሥራዎች ተጠምደው ነው ለዚህ ጉዳይ በቂ ትኩረት መስጠት ያልቻሉት!” ብሎ ሰውየው እንዳይጋለጥብህ አስገራሚ ጥረት አደረገ፡፡
ባለፈው ሳምንት ደግሞ አንዴ “አንዱን ሲነኩት ሌላው ስለሚናድባቸው ነው አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያልቻሉት!” ሲል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አካባቢው በባዕዳን ቁጥጥር ስር ያለና ጣልቃ ገቡ የሚላቸውን አካላት መጋፋት የማይቻል፣ አደገኛና የማይገባም አስመስሎ ያለን አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው ለማለት “አካባቢው የምዕራባውያን ጣልቃገብነት በከፍተኛ ደረጃ ያለበትና ዘሎ መግባት የማይቻልበት ስለሆነ ነው!” እያለ ስለ ዐቢይ ተጨንቆና ተጠቦ የሚቀባጥራቸው ምክንያቶች በሚዲያ ሲናኙ ላልተፈለገ ውጤት የሚዳርጉና ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ፈጽሞ መረዳት አልቻለም፡፡ የመሳይ ኢሳት ላይ መቀመጥ የኑክሌር ቦንብ ቁልፍ በሕፃን ልጅ እጅ ላይ ያለ ያህል እየተሰማኝ ነው፡፡ መሳይ የሚያየው ዐቢይን መከላከሉን ብቻ ነው፡፡ ሊያመጡት ስለሚችሉት አሉታዊና አደገኛ ውጤት ፈጽሞ እያሳሰበው አይደለም፡፡ ለዛም ነው ዝም ብሎ አፉ እንዳመጣለት የሚረጨው፡፡
መሳይ አንተና ቢጤዎችህ እንደፈለጋቹህ መሆን ትችላላቹህ ነገር ግን በሚስኪኑ ሕዝባችን መዋጮ በሚተዳደረውና ሕዝብ ስንት ዋጋ በከፈለበት ኢሳት ውስጥ ግን ፈጽሞ እንዲህ የመሆን መብት የላቹህምና እባካቹህ እባካቹህ ልቀቁልን???
ክህደታቹህ በኋላ ላይ ዓይናቹህን በጨው አጥባቹህ ሕዝብን ይቅርታ በመጠየቅ መመለስ ከምትችሉበት ገደብ በላይ ያለፈ ስለሆነ ከወዲሁ ተስፋ ቁረጡና አንደኛቹህን ኑና ኢቴቪን ተቀላቅላቹህ ሳትሳቀቁ አገዛዙን ብታገለግሉ ለእናንተም ይሻላቹሃልና እባካቹህ ስለ ፈጠራቹህ ብላቹህ እንደ እባብ ውስጥ ለውስጥ አትስለክለኩብን???
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com