የሸካ ዞን ተወላጆች ድምጽ ~በውብሸት ታዬ

ሰሞኑን በሸካ ዞን የተለያዩ ከተሞች በተቀሰቀሰና ብሔርን መሰረት ባደረገ ግጭት በቴፒ ከተማ አራት ያህል ዜጎች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ንብረትም ተዘርፏል።

በሸካና ቴፒ ያለው ትርምስ ቀጥሏል። መከላከያ አረጋግቷል ቢባልም የክልሉ ፖሊስ ተደርቦ በሌሎች ተወላጆች ላይ ጥቃቱ ቀጥሏል… በየቤቱ ሳይቀር እየገቡ እየደበደቡ ነው እያሉ ነው። ድረሱልን እያሉ ነው። የመንግስት ያለ! ድምጻችንን አሰሙልን እያሉ ነው።

ይህንን ማህበራዊ ምስቅልቅል በመቃወም የዞኑ ተወላጆች በአሁኑ ሰዓት በኢቲቪ በር ላይ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

►