በመቀሌው አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ የተያዙት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከታሰሩበት ተለቀቁ !

ከሁለት ሳምንት በፊት ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፍቃድ ውጭ ገብተዋል ያላቸው አርባ አምስት የፌደራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አባላት ከመቀሌ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

አባላቱ በአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የመጡበት አላማም እስኪታወቅ ድረስ እንቅስቃሴቸው ተገድቦበ በፌደራል ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎ እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አስፈላጊ አለመሆኑን ተናግረዋል። ጨምረውም ክልሉ ድጋፍ የሚጠይቀው ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥም ወይም በልዩ ሁኔታ ከተወሰነ መሆኑን ጠቅሰው “ሁለቱም ጉዳዮች እኛ ጋር የሉም” ብለዋል።

“ለተወሰኑ ቀናት የፌደራል ፖሊስ አባላት በካምፑ ውስጥ ቆይተዋል። ወደ ክልሉ የገቡበት መንገድ ችግር ነበረው። እኛ ባልጠየቅንበት እና በማናውቀው ጉዳይ ነው የመጡት” በማለት የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይሉ ለምን መቀሌ እንደተገኘም ግልፅ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

“ለምን እንደመጡ ከፌደራል መንግሥት ጋር መነጋገር ያስፈልግ ስለነበር ፤ ከፌደራል መንግሥት ጋር እስክንግባባ በቦታው እንዲቆዩ ተደርጓል። አሁን ደግሞ እዚህ መቆየታቸው የሚጨምረው ነገር ስለሌለ ወደመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ አድርገናል። “ብለዋል

በወቅቱ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ጉዳዩን መካዳቸው የሚታወስ ነው። የዚያ አይነት ምላሽ የተሰጠበት ምክንያት እንደነበረው አቶ ረዳኢ ይናገራሉ ።

“እውነት ነው ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተራ ወሬ ነው የሚል መልስ ስንሰጥ ቆይተናል። ምክንያቱም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከእውነት የራቀ መረጃ እየተሰራጨ ስለነበርና፤ ለትግራይ ህዝብ እና ለትግራይ መንግስት ብሎም ለስርአቱ ስለማይጠቅም የሚሰሩ ስራዎች ተሰርተው ወቅቱን ጠብቆ በትክክለኛ ጊዜ መነገር ስለነበረበት ነው” ብለዋል።

የፌደራል ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ከክልሉ መንግሥት ፍቃድ ውጭ መግባቱን አስመልክቶ ከፌደራል መንግሥት ጋር ቅራኔ ተፈጥሮ እንደሆነ አቶ ረዳኢን ቢቢሲ ጠይቋቸዋል።

“ከፌደራል መንግሥት ጋር የሚያቃቅር ነገር የለም። ለተልእኮ መጥተው ከሆነ ለዚያ የሚሆን ነገር የለም። አንድ ሃገር ከመሆናችን አንፃር ከመረዳዳት ውጭ ምንም ነገር የለም” ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ግብረ ኃይሉ እንዲወጣ ባዘዛው መሰረት ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገልጿል።
.
©BBC News Amharic

 

የትግራይ መንግሥት ሳያውቀው መቀሌ የገቡ የፀረ ሽብር የፌደራል ፖሊስ አባላት


አሉላ አባነጋ ኤርፖርት
አሉላ አባነጋ ኤርፖርት 

ከ18 ቀናት በፊት የትግራይ ክልል መንግሥት ሳያውቀው ወደ መቀሌ ከተማ ገብተው የነበሩ 45 የፀረ ሽብር የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መጡብት በዛሬው ዕለት ከተያዙበት ተለቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

ከ18 ቀናት በፊት የትግራይ ክልል መንግሥት ሳያውቀው ወደ መቀሌ ከተማ ገብተው የነበሩ 45 የፀረ ሽብር የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ መጡብት በዛሬው ዕለት ከተያዙበት ተለቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

እነዚህ አባላት መቀሌ ከተማ እንደገቡና በአሉላ አባነጋ ኤርፖርት አካባቢ የሚገኝ የፌደራል ፖሊስ ካምፕ በትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይል ሥር እንዲቆዩ ተደርጓል ተብሏል።

የክልሉ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ረደኢ ሐለፎም አባላቶቹ ወደ ትግራይ የመጡበት አካሄድ ሥህተት ነበረበት እኛ ሳናውቀው ነው የገቡት አሁን ግን ከፌደራል መንግሥትጋ በመረዳዳት ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

►