“ነገርን ከሥሩ ውሀን ከጥሩ” እንዲሉ፣በአማራነት የመደራጀት መሰረታዊ ምክንያቱንመሠናክሉን እና መፍትሄውን ከሥር ከመሠረቱ  ጀምረን በጥልቀት አንብበን ከተረዳን፣ንቃታችንና የመንፈስ ጥንካሬያችን ይዳብራል፣ብሎም በራስ ላይ መተማመንን ያላብሰናል።አንድ ጊዜ አመዛዝነን የመፍትሄ መንገድ ከያዝን በኋላ፣ዓላማው ግቡን እሥኪመታ ድረስ  በቆራጥነት ከመጓዝ የሚያግደን አንዳችም ነገር የለም።  ይህን ሥናደርግ ነው ለወገናችን ህልውና መረጋገጥ ሠራን ማለት የምንችለው።

ማሳሰቢያ! “ወያኔና ህዋሀት”የሚሏቸውን የትግርኛ  አጠራሮች ለትግሬዎች ትተን፣ ለአማራው ገበሬጠላትህ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ነው(ትነግ ወይም ትህነግ) “ብለን ብንነግረው በቀላሉ ይረዳዋል።ትክክለኛ መጠሪያቸውም ይህ ነው።

 

ክፍል1

በአማራነት የመደራጀትመሠረታዊ ምክንያት!

በአረጋዊ በርሄ ሊቀመንበርነት የትግሬ  ነፃ አውጭ ግንባር(ትህነግ) ትግሬ  ውስጥ ደደቢት ላይ የካቲት 11ቀን 1968ዓም ያወጣው የፀረ አማራና የፀረ ኦርቶዶክስ ማኒፌስቶ(ፕሮግራ) ይዘትና አላማ  “ትግራይ በዐፄ ምኒልክ የዐማራ ቅኝ አገዛዝ   ግዛት ሥር ከመውደቋ በፊት ለብዙ ዘመናት ራሷን የቻለች ነፃ አገር ነበረች። ለዚህም ብቸኛው መፍትሄ የትግራይ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን ዐማራ ማስወገድና  በመገንጠል  የትግራይን ፐብሊክ አገር መሥርቶ የትግራይን ሕዝብ ከድህነት ማውጣት ነው።ትግራይን እንደአገር በእግሯ ለማቆም፣ ከጎንደር ወልቃይትን፣ጠለምትን፣ጠገዴን፣ታችና ላይ አርማጨሆን፣ሠቲትን ወዘተ፣ከወሎ ደግሞ ራያ፣ዋጃ፣አላማጣ፣ኮረም፣ቆቦ፣ወልድያን ወዘተ ከዐማራ በማፅዳት ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ማጠቃለል” የሚል ነው።

ለዚህም ተግባራዊነት አባሎቻቸውን በቅድሚያ ወደትግራይ ሕዝብ አሠማርተው ሥብከት ሲያካሂዱ፣ የተቃዎሟቸውን የራሳቸውን አባሎች እና  በአንድነት የሚያምኑትን  ቀሳውስቶችንም ሆነ ተራ ትግሬዎች  አንድ በአንድ ለቅመው ጨርሰው፣ኢትዮጵያዊነትን ከትግራይ ምድርና ከትግራይ ሕዝብ አእምሮ እንዲጠፋ አደረጉ።  ያልተቃወሟቸውን ቀሳውስቶች ግን ካድሬዎች አደረጉ።

ቀጥሎም ፊታቸውን ወደ ዐማራው፣ ወደእነወልቃይት ጎንደር እና ወደእነራያ ወሎ አዙረው “የአማራን ሕዝብ ሥነልቦናና ባህል ቀስ በቀስ  በማስለወጥ፣ ነባር ማንነቱን አውልቆ የትግራዊነት ማንነት ሊያጠልቅ እንዲችል መሥራት። ግዛቶቹም የትግሬ እንደሆኑ ሲነገረው  ከተቀበለ ጊዜያዊ አጋራችን አድርገን እንጠቀምበታለን፣የማይቀበለውን እናጠፋዋለን” የሚል  አቋም ያዙ። የአማራው ሕዝብ ግን እሥከዛሬዋ ዕለት ድረስ  “አማራ ነኝ” በማለት ዕውነታውን በመናገሩ፣ትግሬዎች ዘር ማጥፋቱን እንደቀጠሉበት ተጨባጩ ሁኔታ ምሥክር ነው።

ምንም እንኳን የትህነግ የመጀመሪያ እቅዱ ትግራይን ከጎንደርና  ከወሎ በሚወስዳቸው ግዛቶች ገንጥሎና አሥፍቶ ለመኖር ቢሆንም፣በለስ ቀንቶት ከትግራይ አልፎ ሠፊዋን ኢትዮጵያ ከ300አማራ በላይ አሶሳ ውስጥ በላውንቸር ገድሎ ከተቀላቀለው ኦነግ ጋር በመሆን ተቆጣጥሮ አዲስ አበባ ገብቶ በ1983ዓ.ም ግንቦት ወር የሽግግር መንግሥት ሲያቋቁም፣ከአማራው በስተቀር ሁሉም ነገዶች የየጎሳ ድርጅቶቻቸውን በመወከል የኢትዮጵያን አንድነት በናደው ስብሰባ እንዲገኙ አደረገ።

በዚህም ኮንፈረንስ ተብዬው፣(1ኛ)የኢትዮጵያን አንድነት በማጥፋት፣በዘር በተከፋፈሉ በዘጠኝ(9)መንግሥታትና ባንዲራዎች በመተካት፣(2ኛ)የነባሯን የኢትዮጵያ የማንነት ካርታን በመለወጥ፣በዘር በተሸነሸነች አዲስ ካርታ በመተካት፣(3ኛ)ሠንደቅ ዓላማዋን አሽቀንጥረው በመጣል፣ በተግባር የብሔሮችንና የሃይማኖቶችን እኩልነት ሳይሆን በዘርተለያይቶ መጠፋፋትን ባመጣልን በሌላ ባንዲራ በመተካት

የእነመለስ ትህነግ!የካቲት 11ቀን በ1968ዓም ደደቢት ትግሬ ውስጥ “አማራንና አማራን አቅፎ ደግፎ ያቆመውን ኦርቶዶክስን ከምድረገፅ በማጥፋት እርስቱን መቀራመት ነው” ብለው የፃፉትን የፀረ አማራ ማኒፌስቶ በተዘዋዋሪ ያቀፈ እና አበዳሪ አገሮችን ለማታለል ብቻ ተግባር ላይ የማይውሉ የይሥሙላ ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎችን ያካተተ፣በሌሎቹ አማራ ጠሎች በእነሌንጮ ለታ |ዲማ ነገዎ|ዳውድ ኢብሳ| አባ ቢያ (ኦነግ) ተባባሪነትና አርቃቂነት  ዘርና ቋንቋን መሠረት ያደረገ ህገ መንግሥት ተብዬውን  አፀደቁ።

ልብ ያለን ልብ እንበል! ለብዙዎቻችን ሁኔታው እየታዬን የመጣው ዛሬ ካልሆነ በሥተቀር፣ ኢትዮጵያ እንደአገር የተበተነችው፣ኢትዮጵያውያኖችም እንደሕዝብ የተበተንነው፣የዝሆኑን ድርሻ መሬቶች(ከአማራው የተሠረቁትንም ጭምር)ሁለቱ  ተዋናኞች የትግሬው ትነግና የኦሮሞው ኦነግ  በ1983ዓም የዘርና የአንቀፅ39 ህገ መንግሥት ሲያፀድቁና ሲያስፀድቁ  ነው። ዛሬም እነኚህ ጉዶች በዚያን ጊዜ  ያካለሉትን ክልል ላለማጣት እየተሟሟቱ የሚገኙት ለዚህ ነው

ትህነግ!እግረ መንገዱንም ለወደፊት ሁኔታው ካላመቸው  ቀደም ሲል  ያሰበውን የትግሬን መገንጠል “ህጋዊ ሽፋን” ለማላበስ ይረዳው ዘንድ አንቀፅ 39ኝን በህገ መንግሥቱ አካተተ።

በዚህ ሥብሰባ ላይ የአዲስ አበባን ዩኒቨርሲቲ ወክለው ከሄዱት ውስጥ ፕሮፌሰር አሥራት አንዱ ሥለነበሩ፣በግልፅ ተቃውሟቸውን አሠምተው ጥለው ወጥተዋል።

ትህነግ! የተለያዩትን ነገዶች በክልል የሸነሸናቸው ለነገዶቹ ጥቅም አስቦ ሳይሆን፣ በጠላትነት የፈረጀውን አማራ ኅልውናውንና ቋንቋውን ከጊዜ ጋር አዳክሞ በማጥፋት፣ የሚቀራመተውን መሬት ቋሚና የተረጋገጠ ዋስትና እንዲኖረው ለማድረግ  በአገሪቱ ውስጥ ለደረሱት ሁሉ ችግሮች በዳይና ጨቋኝ፣የኢትዮጵያ ሀገራዊና ህዝባዊ አንድነት በሚል የቆሙትና የብሔሮችን እኩልነት የማይቀበሉት ትምክህተኛ አማሮች ናቸው ብሎ በመስበክ፣ የተለያዩት ነገዶች  ከጎኑ  እንዲቆሙና በአማራው ላይ  እንዲዘምቱበት ለማሥቻል ነው

ትህነግ! ከእነሌንጮ ኦነግ ጋር በመተባበር የመጀመሪያው የአማራ ማዳከሚያ ያደረጉት ነገር ቢኖር “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” እንዲሉ፣ አማራው የሚኖርባቸውን አካባቢዎችና መሬቶች በጉልበታቸው በመቀራመት ፣የዝሆኑን ድርሻ መሬቶች መውሰድ ነ

ቀሪውን የአማራ መሬት ሠፊውን የወሎ የምሥራቅ አካባቢ ለኤርትራ አሰብ ከተሰጠው በተጨማሪ ወደአፋር፣ ሌላውን ሰፊውን መተከልን ወደቤኒሻንጉል በማካለል መሸንሸንና አማራውን አጣብቂኝ ውስጥ ማሥገባት ነው።በዚህ ብቻ አላቆመም፣ በሚከልለው የአማራ ክልል ውስጥም የአማራ፣የአገውና የቅማንት ሕዝብ በባህልም በሥነልቦናም አንድ እንደሆነ እየታወቀ፣ የሌለ ልዩነት በመፍጠርና እርስ በርሳችን ለማናከስ የአገው፣የአዊ፣የቅማንት፣ የአርጎባ ወዘተ የሚሉ ቦታዎችንም ሥንቅር አሥገባ።ለሱዳን የሚሠጠውንም የአማራ መሬት ወሰነ።

 ትህነግ! ይህን አመቻችቶ ሲጨርስ፣እና እንደ እሥከዛሬው  ተኝተን  ካየነውና ከተሳካለት የቤኒሻንጉልን ከህዳሴው ግድብ ጭምር፣ የአፋርንና በቅማንት ሥም ከጎንደር የሚወሰዱትን መሬቶችም ወደፊት ከተቻለ በውዴታ፣ካልተቻለ በጉልበት ወደታላቋ ትግራይ ማጠቃለሉ  አይቀሬ የሆነ ዕቅዱ ነው።

ለማንኛውም ከዚህ ኮንፈረንስ በኋላ በአማራ ሕዝብ ላይ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል፣የዝመቱበት ቅስቀሳ ሲካሄድበት፣አማራው ያንን የተለመደ ትዕግሥቱንና ሆደሰፊነቱን መሳሪያ በማድረግ የጎሳውን ጥቅምና ጥያቄ ከኢትዮጵያ አንድነትና ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሳዎች አብልጦ ባለማየቱ በዘር መደራጀት ከሰማይ የራቀ ሀሳብ ሆኖበት ነበር።

በመጀመሪያዎቹም ዓመታት፣በቅድሚያ በጃራ ይመራ የነበረው የእስላማይ ኦሮሞ ድርጅት ቀጥሎ ኦነግም በወያኔ እሥከተባረረበት  ጊዜ ድረስ በእነሌንጮ  እየተመራ ከወለጋ ጀምሮ በሐረር በደኖ፣ ወተር፣በአርባጉጉ፣አሰቦት ገዳም ወዘተ አማራውን አፈናቅሏል፣ገሏል። ወጣት የአማራ ሴቶችንና ልጃገረዶችን አስገድደው  በሞጋሳ እያገቡ በማሥወለድ ኦሮሞ እያደረጉ የኦሮሞን ዘር ሲያበራክቱ፣የአማራው እንዲቀንስ ሠርተዋል።

በተለያዩት የአገሪቱ ክፍሎችም ሁኔታው መረን ለቆ፣አማራው”ክልልህ አይደለምና ውጣ”  እየተባለ  ያለማቋረጥ  ሲሰደድ፣ሲፈናቀል፣ሲገደልና ሰቆቃው ጣራ ነክቶ ህልውናው አደጋ ላይ ሲወድቅ፣አርቆ አሳቢው ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን(መዐሕድን) አቋቁመው የአማራውን ሠቆቃ ለመታደግ ተነሱ፤አንጀቱ ያረረውና ቀድሞ የነቃው አማራ ያላንዳች ማቅማማት ከጎናቸው ቆመ።የትግሬ ወራሪዎች መዐሕድ እየጎለበተ ሲሄድና ሲያሰጋቸው ፕሮፌሰርን ከመሰሎቻቸው ጋር ለእሥር ዳርገው ለሞት አበቋቸው፣ ድርጅቱም ተዳከመ።

ኦነግ በትህነግ ሲባረር ደግሞ ይህንን ተግባሩን ኦሕዴድ ተረክቦት በትህነግ አጋፋሪነት በተለያዩት አካባቢዎች በተለይ ደግሞ አሩሲ  ከ1986 እሥከ 1989 የአማራን ዘር ያለማቋረጥ አድኖ ጨርሷል። የአኖሌን ሀውልትም እሥከማቆም ደርሷል።

መዐሕድም ከተዳከመ በኋላ ከአማራ ድርጅትነት በኢንጂነር ሃይሉ ሻወል አሳሳቢነትና ሊቀመንበርነት ወደ መኢአድ የኢትዮጵያ አንድነትነት ተለወጠ። ግድያው ግን  ከድሮው በባሰ  መልኩ እየጨመረ ሄዶ እሥከ 2008ዓም ሰኔ ድረስ መንግሥት ነኝ ባዩ ትህነግ ያመነው 2.4ሚሊዮን አማራ እንደጠፋ ቢሆንም፣የተገደለው፣የታሰረውና የት እንደደረሰ ሳይታወቅ የጠፋው ከአምሥት(5) ሚሊዮን  በላይ እንደሆነ ታምኗል።

“ከቡሃ ላይ ቆረቆር” እንዲሉ፣ ከርሀብና ከቸነፈር በባሰ መልኩ፣ሁሉም ነገዶች በሚባል መልኩ በየትኛውም ቦታ አማራውን እንደመጤ ፈርጀውና አሥፈርጀው ያላንዳች ጥፋት የሀሰት ክስ በመመሥረት፣በማሠር እና በመግደል ብዙ ወንጀሎችን ከመፈፀማቸውም ባሻገር፣የአማራውን ታሪካዊ ቅርስ በመዝረፍና በማራቆት፣በኢኮኖሚውም እንዳያድግ የኢኮኖሚ አፈና በማድረግ፣ባህሉን በማንቋሸሽና በማራከስ፣ ዘሩ ቀጣይነት እንዳይኖረው መካን በማድረግ፣ በራሱ ላይ እምነት አጥቶ በማንነቱ እንዲያፍር፣ ሞራሉን በመንካትና ቅስሙን በመሥበር፣ ሥር ነቀል የሆነ የሥነ ልቦና ጦርነት ያለማቋረጥ ለ27 ዓመታት እንዲካሄድበትና ሰቆቃውም ሥር እንዲሰድ አደረጉ።

ከመዐሕድ አማራ ድርጅትነት  በኋላ ወደ መኢአድ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትነት በመለወጡ፣ ለብዙ ዓመታት አማራው ያላንዳች “ብሶት ነጋሪ” ሲቀጠቀጥ ከኖረ በኋላ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በውጭ አገር ድርጅቶች ብቅ ብለው የአማራውን ሠቆቃ ማጋለጥ ተያያዙት።

ይህ በዚህ እንዳለ  የወልቃይ የአማራ ማንነት ጥያቄ ሐምሌ 5ቀን 2008ዓም ፈንቅሎ ሲወጣ፣በ25ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያ አንድነት ትግል ያላሥመዘገበውን  “የአማራ ማንነት ጥያቄ” አሥመዘገበ።

ትግሉ እየጎላ በመጣ ቁጥር፣ማንም እንደሚገነዘበው በአማራው ዘር ላይ በተደጋጋሚ በአዋጅ የተደገፈ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ዘመቻ  በጎንደር መተማ ጭምር፣ጎጃም፣በወልድያ፣በመርሳ፣በሀራ፣በጎብዬ፣በቆቦ ራያ፣እንዲሁም በመተከል በትግሬ በሚታገዙ ቤኒሻንጉሎች፣በኦሮሞዎች በጂማ፣በወለጋ፣በምዕራብ ሸዋ ወዘተ ጭምር እንደተካሄደበት እንደሆነ ይታወቃል። የአቢይ ንግግርም  ዛሬም ድረስ አማራውን  ከሞት አላዳነውም፣እየሞተ ነው።

 

ክፍል2

መሰናክሉ!

በዚህ በ27ዓመት ውስጥ ተጨባጩ ዕውነታ  ቁልጭ አድርጎ ያረጋገጠልን  ነገር ቢኖር፣እሥከአፍንጫቸው ታጥቀው በጉልበታቸው የዝሆኑን ድርሻ መሬቶች ከአማራው የቀሙት የእነመለስ ትህነግ ትግሬዎችናእነሌንጮ ኦነግ ኦሮሞዎች አቀነባብረው በወሰኑት መሠረት፣የኢትዮጵያን ሕዝብ  በዘር በመከፋፈል የየግሉን ክልልና ባንዲራ ተብዬውን እንዲታቀፍና አማራውን ከየአካባቢው በጠላትነትና በመጤነት በመፈረጅ ዛሬም ድረስ አገር አልባ  እንዲሆንና ዘሩ እንዲጠፋ እንዳደረጉት ነው።

አማራው ግን ሁሉም በዘራቸው እንደቆሙና እሱንም ከኖረበት  “ቀዬ መጤ ነህ” እያሉ እንደሚያፈናቅሉት እያወቀ ፣ቀፎውን የቀረ የአንድነት ዋሻ ውስጥ ገብቶ፣ በአማራነት ተደራጅቶ ማንነቱን ከማሥከበር ይልቅ በህገ መንግሥት ተብዬው የተጠላውንና የተጣለውን  የኢትዮጵያን አንድነትና የአገር ሉዐላዊነትን ፣ብቻውን ያመጣ ይመሥል” 27ዓመት ተጉዞበት፣

(1)የትነግ ኢህአዴግን የፀረ አማራ ህገ መንግሥት እድሜ በማራዘም የአማራውን ሠቆቃ ያበራከተበት፣የአማራ   ማንነቱን ያጣበት፣ሲገደልበት፣ ሲመታበት፣ መሬቱንና ሚስቱን ከልጆቹ ጭምር ሲያሥረክብበት የኖረበት መንገድ እንደሆነ  በወቅቱ ለመገንዘብ አለመቻሉ፣

(2) አማራ ጠል ቡድኖች “አማራው ተደራጅቶና ጠንክሮ ህልውናውን ካሥከበረ የተቀማውን መሬቶች ከማሥመለስም አልፎ የኢትዮጵያን አንድነት ተግባራዊ ያደርጋል። አማራው እንዳይደራጅና እንዳይጠናከር ለማድረግ የሚቻለው  በኢትዮጵያ አንድነት ሥም ሥንከፋፍለው ነው።

በተለይ ያልነቃ ቁጥሩ የማይናቅ ብዙ አማራ ሥላለ፣የኢትዮጵያ አንድነት ቃሉ ብቻ ተደጋግሞ  ሲነገረው  አማራነትን አውልቆ እሥከመጣል  ሥለሚደርስ፣የገንዘብ፣የፕሮፓጋንዳና የጉልበት ድጋፍ እንዲሰጥና በአማራነት እንዳይቆም ካደረግነው፣አማራው ይዳከማል፣የገንዘብ ምንጩም ይደርቃል።ሌላውን በገንዘብ የሚገዛውን ግን ገንዘብ ሠጥተን እናመጣዋለን” በማለት የውሸት አንድነቶች ጭምር  እሥከዛሬዋ ዕለት ድረስ እያዘናጉ ሲጠቀሙበት አለመንቃቱ፣

(3)አማራን የሚያጠፉ ኃይሎች በረቀቀ መንገድ በሚወረውሩልን የቤት ሥራዎች በመጠመድ የገዛ ዘራችንን አማራን በመቃወምና በማውገዝ መጠመዳችን፣

(4) የተጨበጠ ነገር ቢኖርም ባይኖርም፣አልሚያችንም ይሁን አጥፊያችን፣ነገሩን በጥልቀት ሳንመረምር፣ ኃይለኛ ተናጋሪ ብቅ ብሎ“ኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን አንድነት” ከጠቀሰልን  የሆይታና የጭብጨባ ግልብ አካሄድ እንከተላለን።በአማራነትም የሚታገሉትን እያዳከምን፣ገንዘቡን በተዘዋዋሪም ይሁን በቀጥታ ለሚያጠፉን መገበራችን፣ወዘተ….

የመሳሰሉት  ችግሮች ናችው ለእሥከዛሬው መገደልና መሳደድ  ያበቁን።

 

መፍትሄ!

የኢትዮጵያ አንድነት የፈረሰው በ1983ዓም  በዘር ላይ በተዋቀረ ህገ መንግሥት ሥንቀዬድና 9 የመለያያ የዘር ክልሎች ሥንታጠር ነው።ሁሉም ብሔሮች ድርጅቶቻቸውን አቋቁመው፣የየግል ባንዲራቸውን ተክለው በብሔርትኝነት ነዳጅ እየተገፉ  የብሔሮቻቸውን ጥቅምና የኢኮኖሚ  አቅም በማዳበር በአንድ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲዘምቱበት፣አማራው! በአማራነትና በኢትዮጵያዊነት  መካከል ያለውን የማይሸፈን ሀቅና  ራሱን በአማራነት የማዬት ችሎታ ሥላልነበረው ብዙ ሠቆቃዎችን እየተጋተ ዛሬ ላይ  ደርሷል።

“ፍዬል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” እንዲሉ፣ከተጨባጩ  ዕውነታ  ውጭ ሥለምንመኘውና ሥለፈለግነው ብቻ “የኢትዮጵያ አንድነት” እያልን ብንጮህ፣ራሥን ከማታለልና የኢህአዴግን የፀረ አማራ ህገ መንግሥት እድሜ ከማሥቀጠልና የአማራውን ሠቆቃ ከማራዘም  ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም።

ዝንጀሮ “ፊት መቀመጫዬን “እንዳለቸው  ዕውነታውን አምነን በመቀበል መጀመሪያ  ለአማራው ብቸኛ አማራጭ የሆነውን  የአማራን ድርጅት አጠናክሮና ታግሎ ማንነቱንና ህልውናውን (የመኖር ዋሥትናውን)  ካረጋገጠ በኋላ፣በሚፈጠረው ተጨባጭ ሁኔታ ተመርኩዞ ሥለኢትዮጵያ አንድነት መታገል ይቻላል።ሥለዚህ መፍትሄዎቹ፣

(1) (ሀ)አማሮች ሆነው ከሌሎች ብሔሮች ጋር የተጋቡ፣(ለ) ሁሉም ከአማራና ከሌላ ብሔር የተወለዱ፣(ሐ)ከሌሎች ሁለት ብሔሮች  ወይም ከዚያም በላይ ሲወርድ ሲዋረድ የዘር ግንድ ያላቸው ወገኖች ፣ቋንቋቸው አማርኛ ብቻ ከሆነና ባህላቸውም ሆነ ሥነልቦናቸው ከአማራው ጋር አንድ ዓይነት እሥከሆነ ድረስ ፣በአማራነት መቆም ከደም፣ከአጥንት፣ከዲ ኤን ኤ በላይ ሥለሆነ ያላንዳች መሸማቀቅ ከአማራው ጋር  አብረው የመቆም መብት አላቸው።ሥለሆነም በቅድሚያ “አማራ የብቻው መደራጀት የለበትም” በማለት ለጠላት ዱላ ከማቀበል ተቆጥበን፣ ዛሬ  በአገራችን  ያለውን ብሔረሰብን መሠረት ያደረገ ተጨባጭ  ሁኔታ በጥልቀት ተረድተን፣ በጋራ  የአማራውን መሳደድ ማሥቆምና ህልውናውን ማሥጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፣

(2)አማራን አጠፍቶ የኢትዮጵያን አንድነት ማሰብ እንደማይቻል ተረድተን፣ከግራም ከቀኝም የሚወረወሩትን የጠላት ጫጫታዎች ከምንም ሳንቆጥር አማራነትን አጎልብተን የመኖር ህልውናችንን ዋስትና ባለው መንገድ  ማስጠበቅ የተፈጥሮ ግዴታችን እንደሆነ አውቀን ፅኑ አቋም መያዝ አለብን፣

(3)ለ27ዓመት  በጀርባችን ከተዘረርንበት ለመነሳትየአማራው ዘመድ እራሱ አማራው ብቻ  እንደሆነ” አምነን በፅናት በመቆም ከሚደርስብን በደል ራሳችን በራሳችን ፈንቅለን መውጣት  ይገባናል፣

(4)አማራው ህልውናውን ሊያስከብር የሚችለው በራሱ ጥረት ብቻ  እንጅ፣ሌሎች የእሱን ችግር እንደማይፈቱለት ከልብ  ማመን አለበት፣

(5) አማራው!ህልውናውን ለማሥጠበቅ ሲጥር፣ጠላቶች አማራውን እንደለመዱት መጠቀሚያ ለማድረግ ”አማራ ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” እያሉ ያላዝናሉ፣መልሳችን ግን አማራው ካልተደራጀ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ነው፣በዚህ በ27ዓመት ውስጥም የታዬው ዕውነታ ይኸው ሥለሆነ፣

(6)ንቃታችንን አዳብረን የሚሠራብንንም ሆነ የሚነገረንን እያንዳንዱን ነገር፣ጊዜ ሳንሰጥ ቁምነገር ሠጥተን በመመርመር  ከውድቀት ለመዳን ፈጣን እርምጃ የመውሰድ አቅም እናዳብር፣

(7) አማራው “ትምክህተኛ ወዘተ” እየተባለ ከአምሥት (5)ሚሊዮን በላይ  “በትግሬዎች የአማራ ዘር ዕልቂት” እሥከዛሬዋ ዕለት ድረስ እንደሚፈፀምበት ሁሉ፣ ከአንድ(1) ሚሊዮን ሕዝብ ያላነሳ ያጡት ቱትሲዎችም “እርሙቻዎች”እየተባሉ  “በኢንትራሀምዌ ሁቱዎች የዘር ዕልቂት”ወቅት ባዶ እጃቸውን

ሲገደሉና ሲሰደዱ ከኖሩ በኋላ፣ ሲጠናባቸው ታጥቀው ሁቱዎችን  አሸንፈው ሥልጣን ሲቆናጠጡ ግድያው ቆመ። በአማራው ላይ የሚደረገውንስ ግፍ እንዴት እናስቆመው ይሆን? መፍትሄው በመዋብ ጭምር ይሁን፣

(8)እኛ አማሮች እሥከዛሬ ከደረሰብንና ከሚደርስብን ከልክ ያለፈ በደል በመነሳት  በዕውነት የአማራውን ህልውና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያዋጣን፣ ነገሮችን በአጭር  ሳይሆን ጥበብ በተመላበት አካሄድ በረዥም ርቀት ማዬት ሥንችል ነው፣

(9)የአማራው ሕዝብ በራሱ ድርጅት አማካይነት ትግሉን አጠናክሮና አጎልብቶ ሲወጣ ወደሥር ነቀል ለውጥ  ሊሸጋገር እንደሚችል ማመን አለበት፣

(10) አማራው! ከሁሉም ነገር የተገለለ ተሳዳጅ ሥለተደረገ ህልውናውን በራሱ ጥረት  አሥጠብቆ፣የዘር ህገ መንግስትንና የዘር ክልሎችን እስካላስቀየረ ድረስ  ጥቅሙም፣መብቱም፣እርስቱም፣ወዘተ አይከበርለትም።ማንነቱም ሆነ ህልውናውም በቋሚነት አይረጋገጥለትም።እነኚህን ተግባራዊ ሳያደርግ፣የኢትዮጵያን አንድነት ያሥጠብቃል ማለት ዘበት እንደሆነ እንዲገባው ያሥፈልጋል። ከዚህ ውጭ የሚለፈፉ አንድነቶች ባዶ ቃላት ከመሆን አያልፉም።

 

ማጠቃለያ!

አማራው! ይህንን ተጨባጩን ሁኔታና ዕውነታ  ማየት ተስኖት ሥለሚመኘውና ሥለፈለገው ብቻ የኢትዮጵያን አንድነት የሙጥኝ ብሎ የህልውናው ዋሥትና የሆነውን በአማራነት መደራጀትን ከልብ ባለማመኑ፣በአማራ ጠሎች ሀያ ሰባት (27)ዓመት ተዘመተበት።ይህንን ከየትኛውም አቅጣጫ እየተዋከበና ግፉ እየተበራከተ በሚሊዮኖች  የሚቆጠር ሕዝብ እንዳጣ፣ በመኖርና ባለመኖር መካከል  የሚገኝ  ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀ ሕዝብም  እንደሆነ ዛሬ እያየው መጣ።ይህንን ተጨባጭ ዕውነታ በመረዳቱ መጀመሪያ  ለአማራው ብቸኛ አማራጭ የሆነውን  የአማራን ድርጅት አጠናክሮና ታግሎ የመኖር ዋሥትናውን  ለማረጋገጥ ቅድሚያ ሰጥቷል።ይህ እሰዬው ያሰኛል።

ይህም በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ዙሪያ የተሰበሰበው ትንታግ ወጣት ትውልድ! “አማራው በአማራነት ብቻ እራሱን እያጎለበተ በሄደ ቁጥር፣ የሰቆቃውን ጊዜ ያሣጥራል” ብሎ እንደተነሳ ይሰማኛል።

ቀኝም ነፈሰ ግራ አማራው! ትግሉን አሁን እደረሰበት ደረጃ አድርሶታል። ትግሉ ይቀጥላል።መውደቅ መነሳት ያለ ነው።ይህንንም ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት የግድ ይላል። ህልውናውን ከማሥከበርም ባሻገር ከሌሎች ጎሳዎች ጋር  ሕዝባዊ ትብብሩን አጠናክሮ እሥከ ኢትዮጵያ አንድነት ለመዝለቅ ይጥራል።

 

አማራው ህልውናውን ዕውን ያደርጋል!

አያሌው ፈንቴ