25/08/2018

ብአዴን አማራ ጎንደር ከነፃነት ደንቀራቸው ተገላገሉ

መንገሻ ዘውዱ ተፈራ

የህውሓት ቅኝ ግዛት አስፈፃሚ ደቀ መዝሙር አቶ በረከት ስምኦን ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴነት ተባረረን መስማት ትልቅ ግልግልና እፎይታ ቢሆንም በተለይ ለጎንደር  ከዚያም የበለጠ መገለጫ ቃል የማይገኝለት ፍፁም ግልግል ነው።

ጎንደር ለበረከት እሱን የፈጠሩ ቤተስቦቹ ከመቀበል ጀምሮ እርሱንና መላ ቤተሰቡን ተንከባክባ ከማሳደግ ከምስኖር ሲሞቱ አልቅሶ ከመቅበር ውጭ እሱ በሆዱ አዝሎት ያደገው ቂም እንዳለው የውስጥ ስለሚሆን ባናውቅም እኛ የምናውቀው ከታላላቆቻችን የሰማነው ግልፅ በደል ግን አልነበረም።
አቶ በረከት ግን ጎንደርን ድሀና ሀብታም ባለስራና ስርአጥ አማራና ቅማንት ሹሚና ሻሪ ጉርምርምታ ሲሰማ ቀድሞ ደርስሽ እሳት አጥፊ በመሆን ለጎንደር ማህበራዊ ቀውስ ኢኮኖሚ ውድቀት መሬቶቻችን ለማይመለከታቸው አሳልፎ በመስጠት በራሳችን ሀብት የበይ ተመልካች ድሆች አድርጎን የኖረ ብአዴንንም በቀጭን ትዕዛዝ መስራት ቀርቶ መተንፈስ እንዳይችሉና ከህዝባቸው ተገልለው በጥላቻ እንዲታዩና እንዲተፋ አድርጎ የኖር መገላጫ የማይገኝለት ፍጡር ነበር።
ዛሬ ብአዴን አማራ ጎንደር መላው ኢትዮጽያ ከትልቅ የነፃነት ደንቀራ ተገላገልን።በዚህ ያበቃል ብለን አንጠብቅም እንዲህ ከቀረማ ነገ እሱን የሚተካ ግፈኛ ላለመፈጠሩ ምን ዋስትና ይኖራል።
ኢትዮጽያ በክብር ለዘላለም ትኑር ።