የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት፣በኢትዮጵያ የነዳጅና የጋዝ መሠረተ-ልማት፣የኢትዮጵያ ኤርትራ የአሰብ ወደብ፣የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው በትረ፣ተመክሮ
ፖለቲካን ሽሮ መብሊያቸው ካደረጉ አድርባይ ምሁራን ተማሩ!!!
ከውጭ የመጡ ፖለቲከኞች ‹‹ሆቴል ቤት ለእንቦሳ›› የተባሉ ይመስል አንዴ ከሸራተን ሆቴል አንዴ ከሂልተን ሆቴል ሲምነሸነሹ የዘውጌ ፖለቲካን ሽሮ መብሊያቸው ያደረጉ እንጂ ስንትና ስንት የደሃ ልጅ በጥይት የተፈጀበት፣ በእስር ግርፋት የተሰቃየበትና ከሃገር የተሰደደበት መሆኑና በተለይ ልጆቻቸው መስዋእት የሆኑ ወላጆች አስታዋሽ አጥተው ጦሪና ቀባሪ ልጆቻቸውን ተነጥቀው ያሉባት ሃገር ውስጥ መምጣታቸውን የዘነጉ ይመስላሉ፡፡ የዘውጌ ፖለቲካን ሽሮ መብሊያቸው ያደረጉ ዲያስፖራዎችና ባላገሮች ከዚህ ደሃ ህዝብ ላይ እንደ ወያኔ ኢህአዴግ መኖሪያ ቪላ ቤት የሚከራዩት፣ ቪኤይት መኪና የሚነዱት፣ ከፍተኛ ደሞዝና የቦርድ አባል ሆነው የሚሾሙበት፣ 500 ሜትር ካሬ ቦታ ቤት ለመሥሪያ የሚዘርፉበት ወዘተ ጥቅማ ጥቅሞች ለማግኘት ሲቆምጡ ይስተዋላሉ፡፡ ዲያስፖራና ባላገር ፖለቲከኞች ዘረፋው ተራ በተራ የሚሆን መስሎቸው ከሆነ ተሳስተዋል፣ ከዚህ ዘመን በሆላ ልዩ ልዩ የሙስናና የሌብነት ጥቅሞች ከወደቀው ከወያኔ ኢህአዴግ ሹማምንት ጋር አብሮ አክትሞል እንላችኃለን፡፡ ጋዜጠኞች የነዚህን ፖለቲካን ሽሮ መብሊያቸው ያደረጉ ዘውግ በቅፌ ዲያስፖራዎችንና የሃገር ቤት ፖለቲከኞች በመከታተል የሆቴል ፊርመኞች/ ሲግኔቸር ወጪ፣ በመገናኛ ብዙሃን የማጋለጥ ሥራ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ቃል እንገባለን፡፡ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ፣ ከምድረ አሜሪካ የመጣ ዲያስፖራ እንዲሁም አቶ ጌታቸው በትረ፣ ከምድረ እንግሊዝ የመጣ ዲያስፖራ ከወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት ላይ እንደ መጅገር ተጣብቀው ህዝብ ያዘረፉ አድርባይ ምሁራኖች ትምህርት ትቀስሙ ዘንድና ነግ በእኔም እንድትሉ የአመለካከት ለውጥ እንድትቀስሙ ተጋብዛችሆል፡፡ እናት ሃገራችንን በሃቅ ለማገልገል ቃል እንግባ!
{1} በኢትዮጵያ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ፣ በኢትዮጵያ በ1959ዓ/ም በቀ.ኃሥ ዘመነ መንግሥት በአስብ ወደብ የመጀመሪያው የነዳጅ ማጣሪያ በሶብየት ህብረት ባለሙያዎች ተገነባ፡፡ የአሰብ ድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ በዓመት 500,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ የማጣራት አቅም ነበረው፡፡ በወታደራዊው መንግሥት ዘመን የነዳጅ ማጣሪያው የማስፋፍያ መርሃ ግብር በማድረግ ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅሙ ወደ 800,000 ሜትሪክ ቶን ተሸጋግሮ ነበር፡፡ በ1983 ዓ/ም ሻብያ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በመገንጠል፣ የነዳጅ ማጣሪያውን በመውስድ፣ ወያኔ ኢህአዴግ ለሻብያ የወደብ የአገልግሎት ክፍያ በመፈፀም ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ በ1989 ዓ/ም ጀምሮ ኢትዮጵያ የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ መጠቀሞን አቁማ የተጣራ የነዳጅ ውጤቶችን ከውጪ አገራት ማስገባት ጀመረች፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በአመት 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ትጠቀማለች፡፡
በ4 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፍያ ቦንቦ መስመር ፕሮጀክት፣ የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለሪፖርተር እንደገለፁት ‹‹ የነዳጅ ማጣሪያውን የሚገነቡት በእስያ በነዳጅና በመሠረተ ልማት ግንባታ ከተሠማሩ ባለሃብቶች ጋር በመተባበር ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ የቦታ መረጣ ሥራ መከናወኑን አቶ ዘመዴነህ ተናግረዋል፡፡ የነዳጅ ማጣሪያው በዋነኛነት ለኢትዮጵያ የሚያገለግል ሆኖ ለሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመው፣ ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ ቦታዎችን ካጠናን በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የነዳጅ ዴፖ በሚገኝበት አዋሽ ከተማ እንዲገነባ መርጠናል ብለው ነበር፡፡››
Ethiopia oil refinery planned as Blackstone pipeline shelved by Pal Burkhardt and Nizar Manek/ 30 Jan 2018/ Bloomberg
“Ethiopia’s fast-growing economy has Asian investors lining up to build a new $4 billion oil refinery, even as a Blackstone Group LP-backed fuel pipeline project is shelved. The proposed 120,000 barrels-a- day plant has generated interest from Japanese, South Korean and Indian investors, said Zemedeneh Negatu, chairman of U.S.-based Fairfax Africa Fund.”
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ከጅቡቲ ወደብ ወደ መሃል አገር የምትገነባው፣ የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፍያ ቦንቦ መስመር ፕሮጀክት ሲሆን ናፍጣ፣ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ ከጅቡቲ ወደብ አዋሽ ዴፖ ማለትም አዋሽ አርባ የሚገኘው የነዳጅ ዴፖ የሚደርስ 550 ኪሎ ሜትር ርዝመት ድረስ እንዲያጎጉዙ የተጠና ሲሆን አጥኝዎቹ ነዳጅ በቦንቦ ማስተላለፍ ነዳጅ በተሸከርካሪ ለማጎጎዝ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ እንደሚቀንስ፣ ጊዜን ከመቆጠቡም በላይ የነዳጅ ስርቆትንና ብክነትን መከላከል እንደሚረዳ ብላክ ራይኖ የአዋጭነት ጥናት ሠርቶ ለወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት አቅርቦ ነበር፡፡ ፕሮጀክቱ በአሜሪካው ብላክ ስቶን ኢንቨስትመንት ቡድን የሚደገፈው ብላክ ራይኖ ኩባንያ ሲሆን የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 1.55 ቢሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ በቀረበው ዕቅድ የወያኔ መንግሥት በደስታ ተቀብሎት ነበር፡፡ ብላክ ራይኖ ባቀረበው ጥናት የኢት ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፍያ 2 ኢንች ስፋት ያለውና በቀን ከ 120,000 እስከ 240,000 በርሜል ነዳጅ የማስተላለፍ አቅም እንደሚኖረው ገልፆ ነበር፡፡ የኢትዮጵያና የጅቡቲ መንግስታት በ2015 እኤአ ስምምነት ተፈራርመው ነበር፡፡ የነዳጅ ቦንቦ ዝርጋታ ፕሮጀክቱ በ2017 እኤአ ተጀምሮ በ2019እኤአ እንደሚጠናቀቅ ተገልፆ ነበር፡፡ ብላክ ራይኖ መሠረተ ልማቱን ለ30 ዓመታት አስተዳድሮ ለወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት የማስተላለፍ ስምምነት ነበራቸው፡፡ የፕሮጀክቱ ኢንቨስትመንት የግንባታ ወጪ ብድር የሚያመጣው ኩባንያው ነበር፡፡
የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት ለወያኔ ኢህአዴግ በማጥናት በኮሚሽን ጠቀም ያለ ገንዘብ በማግኘት ሃገር የሸጠ የወያኔ የጥቅም ተቆዳሽ መሆናቸውን የሚያሳየን ደግሞ ፌርፋክስ የሄሎ ካሽ የአክሲዮን ባለቤት ሲሆን በተጨማሪም ሲንጋፖር ካለ ካንፓኒ ጋር በመሆን ከወያኔ ኢፈርት የመሶቦ ሲሚንቶ ጋር በ70 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የቤት ጣሪያ አምራች ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ በማቆቆም ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ ሁለትና ሦስት ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች ለማቆቆም መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ከአሜሪካ ሲመጡ ከጎደኞቻቸው ጋር ሆነው የሞዴስ ፋብሪካ ለማቆቆም አስበው አልተሳካላቸውም ነበር ከዛም ለአሜሪካ ድርጅት ለሆነው ‹እርነስት ኤንድ ያንግ› ተቀጥረው በማገልገል ቆይተው፣ ከወያኔ ጋር በመወዳጀት በአጭር ጊዜ ከባህር ማዶ ሃገራትና ካንፓኒዎች ብድር በማፈላለግ ኮሚሽን በመቦጨቅ ቢሊየነር የሆኑ ሆድ አደር ምሁር በመሆን በቦሌ ክፍለከተማ መዋኛ ገንዳ ያለው ፎቅ ቤት የሰሩና ከጎኑ 1000 ሜ/ካሬ ቦታ በ20 ሚሊዮን ብር በመግዛት የደረሱ የናጠጡ ባለፀጋ መሆን ችለዋል፡፡ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የውሽት ጥናት የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እዳውን ለመክፈል ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን በማመላለስ በተለይም ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ መሃል አገር በባቡር ለማመላለስ የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት በማጨናገፍ ከወያኔ ጋር አብረው አገር ዕዳ ለመክተትና ኮሚሽን ለመብላት የሞከረ አድርባይ ምሁር የወያኔ መሶቦ ፋብሪካን ሲገነባ ማየት የህዝብ ልጆች በጥይት ሲቀጠፉ እያየ በሁለት አሃዝ አደግን እያለ በመገናኛ ብዙሃን ሲዘለብድ የከረመ ምሁር በህግ ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ መለመላውን ከምድረ ጦቢያ ገብቶ፣ በውሽት ጥናት ያካበተውም ኃብት በሙስናና በወያኔ ሽርክና የተገኘ በመሆኑ የሃብቱ ምንጭ በዋና ኦዲተር ምርመራ ሊደረግበት ይገባል እንላለን፡፡
Fairfax plans to build USD 4 Bln oil refinery in Ethiopia/ 13 January 2018/ by Kaleyesus Bekele /The Reporter
“ Fairfax Africa Fund, a US-based investment firm, in collaboration with multiple partners from Asian countries is planning to build an oil refinery in Ethiopia with a total investment cost of four billion US dollars. Zemedeneh Negatu, Global chairman of Fairfax Africa Fund, told The reporter that his company has undertaken the feasibility study.”…… “Fairfax is a founding shareholder in Hello Cash. And it recently teamed up with a Singaporean company and Messebo Cement to establish a roofing material manufacturing company with an outlay of USD 70 million. It is processing two more manufacturing projects to be finalized in next two or three months. “” We are heading to manufacturing and infrastructure,”” Zemedeneh said.”
{2} ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ዘመናዊ የኤሌትሪክ ባቡር፣ በቻይና የሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና ቻይና ሲቨል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን 3.4 (በሦስት ቢሊዩን አራት መቶ ሚሊዩን) ዶላር ብድር እየተገነባ ያለው 758 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው፣ የሰውና ዕቃ ማጎጎዣ የኤሌትሪክ ባቡር አዲስአበባ ከተማን ከጅቡቲ ጋር ያገናኛል፡፡ በአንድ ግዜ 2760 ሰዎችን ጭኖ በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር እንዲሁም 3500 ቶን ሸቀጥ በመጫን በሰዓት 80 ኪሎ ሜትር የመጎዝ አቅም እንዳለው መስከረም 26 ቀን 2009ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቦል፡፡ የአገር አቋራጭ የባቡር መስመር ዝርጋታ የአዲስ አበባ-አዳማ-ድሬዳዋ-መኤሶ-ደወሌ-ጅቡቲ መስመር አንዱ ሲሆን 758 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የፕሮጀክቱ የግንባታ ወጪ 3.4 ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በአንድ ግዜ 4000 ቶን ጭነት ያጎጉዛል ተብሎ ይገመታል፣እንዲሁም የባቡሩ ሃዲድ ጥንካሬ እስከ 3500 ቶን ክብደት ድረስ መሸከም ይችላል፡፡ ግንቦት 2006 እኢአ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ2004 ዓ/ም የተጀመረው የሰበታ ደወሌ አካል የሆነው አንደኛው ከሰበታ መኢሶ፤ሁለተኛው ከመኢሶ እስከ ደወሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ ሃዲድ በማንጠፍ ስራው ተጠናቆል፡፡ከመኦሶ በድሬዳዋ አድርጎ ወደ ደወሌ የሚዘረጋው 339 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው የባቡር መስመር ፕሮጀክት በአራት ቢሊዩን ዶላር ወጭ ሲኖረው፣ በጠቅላላው 740 ኪ/ሜ ይሸፍናል፡፡ በ2008 አ/ም ይጠናቀቃል የተባለው ይህ ፕሮጀክት በህዳር 2010 ዓ/ም ተጠናቆል፡፡ ሥራ ተቆራጩ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጁ ዩ ዋን ሊ ባቡሮቹ፤ ፉርጎዎቹና የሲጊናል ሲስተሞች በቻይና ደረጃ መፈብረካቸውን አስታውቀዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለሁለት ሽህ በላይ የሠለጠኑ ሠራተኞችን የሥራ ዕድል እንደሚሰጥ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ጂቡቲ የባቡር ፕሮጀክትና ለተበደረው 2.5 ቢሊዮን ዶላር የወለድና የግዴታ ክፍያ መክፈል የጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ ግን ወደ ሥራ አለመግባቱ ይታወቃል፡፡ በሃምሌ ወር 2008 ዓ/ም 35.47 ሚሊዮን ዶላር (784 ሚሊዮን ብር) መክፈሉ ታውቆል፡፡ በ2009 ዓ/ም ጥር ወር 45 ሚሊዮን ዶላር (1.06 ቢሊዮን ብር) ለመክፈል አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአዲስ አበባ ጂቡቲ አዲስና ዘመናይ የባቡር ሐዲድ አራት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተወሰደ ብድር ተገንብቶ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እዳውን ለመክፈል ባደረገው ጥናት መሠረት ባቡሩ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን በማመላለስ በተለይም ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ መሃል አገር በባቡር ለማመላለስ አንድ መቶ ያህል የነዳጅ ማመላለሻ ፉርጎዎች አዘጋጅቶል፡፡ በጥናቱ መሠረትም የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ነዳጁን ለማመላለስ ዝግጁ ሆኖ ሳለ የተጣራ የነዳጅ ውጤቶች ማስተላለፍያ ቦንቦ መስመር ፕሮጀክት፣ ከጅቡቲ ወደብ አዋሽ ዴፖ የቦንቦ መስመር መዘርጋት አዋጭ እንደማይሆንና ሃገሪቱን ለተጨማሪ እዳ እንደሚዳርጋት እየታወቀ በሃገርና በወገን ኮሚሽን ለመቦጨቅ ሹማምንትና ምሁራን በተለይ የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው በትረ የሃገር ክህደት ፈፅመዋል፡፡ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ሃገራቸውንና ህዝቡን ለባህር ማዶ ብድር የዳረጉ አድርባይ ምሁሮች ስለሆኑ በሙስና ያፈሩት ሃብትና ንብረት በዋና ኦዲተር እንዲመረመር እንጠይቃለን፡፡ ሁለቱ ምሁራን ለተመሳሳይ አገልግሎት ሁለት የተለያዩ መሠረተ ልማቶች መገንባት በሃገር ኢኮኖሚ የብድር ጫና መፍጠርና በደኃው ህብረተሰብ ላይ ኮሚሽን ለመብላት መሆኑን የምጣኔ ኃብት ልሂቃን ያምናሉ፡፡
የኤርትራ አሰብ ወደብ ኪራይ ለዩናይትድ አረብ ኢምሬት፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት የኤርትራውን አስብ ወደብ ለ30 አመት የወታደራዊ ቤዝነት መከራየቶን መሠረቱን ቤሩት ያደረገ የአረብኛ ቴሌቪዝን አልማያድን ዘግቦል፡፡ አረብ ኢምሬት ከአሰብ እስከ አዲስ አበባ የነዳጅ መስመር ግንባታ ለማድረግ እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በከፍተኛ ፍጥነት ወደቡን ለመስራትና የጅቡቲን የወደብ ኪራይ ጫና ለመቀነስ ያስችለናል የሚል እሳቤ አላት፡፡ ሆኖም የአሰብ ወደብ በእርግጥ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለ30 አመታት በኮንትራት የተሰጠ ከሆነ፣ ለኢምሬት የወደብን ኪራይ የመክፈል ግዴታ ይኖርብናል፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬት የነዳጅ ማስተላለፍያ ቱቦ ዝርጋታ ፕሮጀክት ሥራና የተጣራ ነዳጅ ሽያጭ ለሃገራችን ለማቅረብ ጥያቄ ማቅረባቸው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አዋጭነት አጥኝ ኮሚሽን በማቆቆም ልሂቃን የአዋጭነት ጥናት በማቅረብ ለሀገርና ህዝብ የሚጠቅመውን ከተለያዩ ፕሮጀክቶች መሃል አንዱን በመምረጥ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ የአዋጭነት ጥናት፣ ለግለሰቦች መተው እንደ የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው በትረ የሃገር ፕሮጀክት ሃላፊነት መስጠት ከእንግዲህ መቆም አለበት እንላለን፡፡
United Arab Emirates to exhaustively invest in Ethiopia. Multi-billion dollar oil pipeline onstruction among key projects. Source : EBC borkena August 10,2018
“The United Arab Emirates wants to exhaustively use all investment opportunities in Ethiopia,” Al-Hashimi told reporters after her meeting with the prime minister. Apart from that, UAE planning a multi-billion dollar oil pipeline construction from Assab, about nine hundred Kilometers east of Ethiopia’s capital, to Addis Ababa. Feasibility study for the project is expected to kick off rather sooner based on information from Ethiopian government sources. UAE has a military base in Assab, which has been under the Eritrean government since 1991. Since Assab is currently under the government of Eritrea, construction of oil pipeline will certainly involve an agreement with Eritrea as well. Ethiopia has been mostly using Djibouti port to import refined oil for the last two decades which proved to be expensive from the point of view of transportation which probably necessitated, among other things, railway project which was completed recently. In 2015, Ethiopia unveiled a plan to construct an oil pipeline from Djibouti to Addis Ababa only to cancel the project due to financial reasons according to report by the Ethiopian Reporter sometime in December 2017. The Djibouti-Addis project was to be delivered by Black Rhino Group at a cost of US $1.5 billion dollars. Abiy Ahmed was awarded UAE’s highest order of medal along with Eritrean president Isayas Afeworki just days before he traveled to the United States to meet with Ethiopians last month.
Ethiopia, UAE plan oil pipeline linking Assab and Addis Ababa 11 August 2018 By Staff Reporter
Ethiopia and the United Arab Emirates (UAE) are planning to build an oil pipeline linking Eritrea’s port city of Assab and Addis Ababa. This was revealed yesterday during a meeting between Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) and Reem Al Hashimy, UAE’s Minister of State for International Cooperation. During the meeting, the two sides also discussed ways to implement previously concluded investment agreements, which among others, include development of real estate and resorts, according to Fitusm Arega, chief of staff at the Office of the Prime Minister. The two countries also agreed to conduct a study to build an oil pipeline linking the port of Assab and Ethiopia, Fitusm, who attended the meeting, said. After the discussion, Reem Al Hashimy told Fana Broadcasting Corporation (FBC) that the UAE is keen to exploit the investment opportunities available in Ethiopia. The peace deal reached between Ethiopia and neighboring Eritrea is a good opportunity for the UAE to invest in Ethiopia, she added. (FBC)
UAE to build oil pipeline between Eritrea and Ethiopia Posted by: ecadforum in News August 10, 2018
NAIROBI, Aug 10 (Reuters) – The United Arab Emirates will build an oil pipeline connecting Eritrea’s port city of Assab with Ethiopia’s capital Addis Ababa, an Ethiopian state-affiliated broadcaster said on Friday. Fana Broadcasting said the information was revealed during a meeting in Addis Ababa between Ethiopia Prime Minister Abiy Ahmed and Reem Al Hashimy, the UAE’s state minister for international cooperation. It did not provide further details, but Abiy’s chief of staff, Fitsum Arega, told Reuters that the discussion with Hashimy was largely on investment in sectors including “industries, agriculture, real estate, (the) oil pipeline, (and) resorts”. “Most are under study,” Fitsum said in a message. The announcement is the latest sign of the UAE’s increasing involvement in the Horn of Africa. The UAE played a behind-the-scenes role in helping Ethiopia and Eritrea end a two-decade state of war last month, Reuters reported this week. The oil-rich Gulf state, driven by a desire to tap Ethiopia’s growing economy and by a fear that rivals such as Iran or Qatar could gain a foothold, has pushed into the region for more than a decade. Abu Dhabi has a military base in Assab which it uses to help prosecute the war in Yemen, located just across the Red Sea.
{3} የኢትዮጵያ የፖታሽ ማዕድን ኃብት፣ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ ባቡር፣ የመቐሌ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ ባቡር መስመር ልማት ግንባታ፣ አንዱ የሆነው አዋሽ-ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ ሲሆን 375 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (2015/16 – 2019/20) ሁለተኛው የአምስት አመት እቅድ መሠረት የተቀመጠው ውጥን ደግሞ በአጭሩ እንቃኛለን፡፡ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ከመቐለ-ታጁራ ወደብ በ3.2 ቢሊዩን ዶላር ለሚገነባው ባቡር መስመር የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦል፡፡757 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በሁለት ክፍል ተከፍሎ የሚካሄድ ነው፡፡ የመጀመሪው ከመቐለ እስከ ወልዲያ (ሃራ ገበያ) የሚገነባው 368 ኪሎ ሜትር የባቡር መሥመር በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (ሲሲሲሲ) የግንባታ ሥራ ተከናውኖል፡፡ ይህ ግንባታ 1.6 ቢሊዩን ዶላር ሲሆን ከቻይና ኤግዚም ባንክ ብድር ተገኝቶል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ 389 ኪሎ ሜትር የባቡር ሃዲድ መሥመር በቱርክ ኩባንያ ያፒ ማርከንዚ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ በ1.7 ቢሊዩን ዶላር የግንባታ ወጪ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ብድሩ በቱርክ መንግስትና ከክሬዲት ስዊስ እንደተገኘ ተገልፆል፡፡ የባቡር መስመሩ ስሜን ኢትዩጵያን ከማዕከላዊ የአገሪቱ ክፍል የኢትዩጵያ ዋነኛ የወጪና ገቢ ንግድ በር ከሆነው ጂቡቲ ወደብ ያገናኛል፡፡ በአፋር ክልል የተገኘውን የፖታሽ ማዕድን ወደ ትግራይ ክልል በማጠቃለል ይህን የፖታሽና ሬድ ፖታሽ በማውጣት ከ250 እስከ 500 ሚሊዩን ዶላር የውጪ ምንዛሪ የወያኔ መንግስት ለማግኘት እንደሆነ ሚስጥራዊ መረጃ አጋልጦል፡፡ አላና የፖታሽ ማዕድን ይዞታ 300 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 200 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሆነው ቦታ በፖታሽ ማዕድን የተሸፈነ መሆኑ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ አላና ፖታሽ በዳሎል 3.2 ቢሊዩን ቶን የፖታሽ ክምችት መኖሩን ጥናቱ ጨምሮ አረጋግጦል፡፡ የኖርዌ መንግስት ኢንቨስት ላማድረግ እቅድ አለው፡፡ በአፋር ክልል የጨው ምርት ክምችትም በብዛት ይገኛል፡፡ የአንድ ቶን ፖታሽ ዋጋ 570 ዶላር የነበረ ሲሆን ዋጋው በመቀነስ አሁን 280 ዶላር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ ባቡር ፕሮጀክት፣ መነሻ መቐለ ከተማ ሲሆን በአፋር ክልልና በአማራ ክልል ውስጥ በምትገኘው የሰሜን ወሎ ዞን ሃራ ገበያ አልፎ ከአዋሽ ኮምቦልቻን ተሸግሮ ከሚመጣው የምስራቅ ክፍል የባቡር መስመር ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት ይበቃል፡፡ የባቡር መሥመሩ 216 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው በአማራ ክልል ውስጥ 55 ኪ/ሜ፣ በአፋር ክልል ውስጥ 52 ኪ/ሜ እንዲሁም በትግራይ ክልል ውስጥ 108 ኪ/ሜ የግንባታ ሥራ ይከናወናል፡፡ ፕሮጀክቱ 9 ዋሻዎችን ከሁለት እስከ 2.7 ኪ/ሜ (መንጨልፎ ዋሻ) ያካትታል፡፡ ፕሮጀክቱ ትላልቅ ድልድዮችና 372 ትናንሽ፣ የእንሰሳትና የውሃ መተላለፍያ ድልድች አሉት፡፡ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ የባቡር ፕሮጀክት በጥናት ላይ ያልተመሠረተ በወያኔ የጠባብ ብሄረተኝነት ስሜት ላይ ያተኮረ ብሄራዊ ኢኮኖሚውን ለዕዳ የዳረገና ያለጥናትና እቀድ የተከናወነ ፕሮጀክት ነው ፡፡ በተመሳሳይ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ የባቡር ፕሮጀክት፣ከቱርክ ኤግዚም ባንክ እንዲሁም ከክሬዲት ስዊስ የተገኘው 1.165 ቢሊዮን ዶላር ብድር የወለድና ግዴታ ክፍያ በሃምሌ ወር 2008 ዓ/ም 18.73 ሚሊዮን ዶላር (413.66 ሚሊዮን ብር) ተከፍሎል፡፡ በ2009 ዓ/ም በጥር ወር ሁለተኛው ክፍያ 22.41 ሚሊዮን ዶላር (530.92 ሚሊዮን ብር) መክፈል አልተቻለም፡፡ በአጠቃላይ የኢትዩጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያለበት ብድር 5 ቢሊዩን 4 ሚሊዩን ዶላር እንደሆነ ሂሳቡን ማስላት ይቻላል፡፡ ከመቐለ-ታጁራ ወደብ የባቡር ፕሮጀክት ሥራ ቆሞል ያለጥናት የተጀመረ ሥራ ውጤቱ የሃገር ኪሳራና ለሙስና የተጋለጠ ነው፡፡
የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ዶክተር ጌታቸው በትሩ ለተለያዮ የባቡር መሠረተ ልማት ፕሮግራሞች ከተለያዩ አገራቶች የተወሰደው ብድር ክምችቱ ከፍ ማለቱና የብድር ወለድ መክፈል በመጀመሩ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጫና ውስጥ መግባቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 15 ቀን 2009 ዓ/ም ገልፆል፡፡ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የዕዳ ክምችት በ2008ዓ/ም መጨረሻ ከነበረበት 95.97 ቢሊዮን ወደ 102.5 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሎል፡፡ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከውጭ አገር ባንክ የተወሰደ ብድር ክምችት ከነበረበት 71.2 ቢሊዮን ብር ወደ 76.37 ቢሊዮን ብር አድጎል፡፡የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከአገር ውስጥ ባንክ በቦንድ ሽያጭ የተወሰደ የረዥም ጊዜ ብድር በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከነበረበት 15.4 ቢሊዮን ብር ወደ 17.6 ቢሊዩን ብር ዕድገት አሳይቶል፡፡ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኪሳራ 1.8 ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡ በአገሪቱ የባቡር ፕሮጀክቶች ያዋጭነት ጥናት ሳይደረግ በዘፈቀደ በብድር ገንዘብ በመስራት ህዝቡን ዕዳ ከተው፣ ለቻይና መንግሥት ወለድ አግድ አስይዘውና ዘርፈው ከመጡበት ሃገረ-እንግሊዝ ሸሽተው ተሰደዋል፡፡ የወያኔ መንግሥትና የምድር ባቡር ኮርፖሬሽኑን የተወሰነ ድርሻ ለባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ስም ለቻይና መንግስት በመሸጥ የዕዳ ጫናቸውን ከመቀነስ ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ ‹‹የቻይና ድራጎኖች ስውር ቅኝ አገዛዝ በኢትዩጵያ!!!›› እንደዛ ነው፡፡
{4} የኢትዮጵያ የገቢ ንግድና የወጪ ንግድ የወደብ አገልግሎት ምርጫ
የኤርትራ መንግሥት በቀይ ባህር አዲስ ወደብ የፖታሽ ማዕድን ኃብት ለወጪ ንግድ አገልግሎት ለማዋል በተለይ ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች፣ ለኢትዮጵያ የኤርትራው የአንፊል ወደብ አገልግሎት ምርጫ ከፖታሽ ማዕድን ኃብቱ 1.2 ቢሊዮን ሜትሪከ ቶን እምቅ ኃብት 75 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ መገኘቱ አንዱ እንደሚሆን በአማራጭም አሰብና ምፅዋ እንደሉ፣ ታጁራ ወደብ በጅበቲ፣ በርበራ ወደብ በሱማለያ፣ ላሙ ወደብ በኬንያ፣ ፖርት ሱዳን በሃገረ ሱዳን የወደብ አገልግሎት ምርጫዎች እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በሃገረ ጅቡቲ ታጅራ ወደብ በቻይና ኩባንያዎች በመገንባት ላይ ሲሆን የፖታሽ መዕድን ሓብት በውጭ ንግድ ከኢትዮጵያ በጅቡቲ በኩል ወደ ቻይናና ኖርዌ ለመላክ የታሰበ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት እርቀ ሠላም መውረድ የተነሳ የተገኘ አማራጭ የአንፊል ወደብ አገልግሎት ከፖታሹ ማዕድን በ75 ኪ/ሜ ርቀት ላይ መገኘት ከአሉት የወደቦች ምርጫ ተመራጭ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከተለያዩ የአዋጭ ጥናቶች በመነሳት፣ ንግድ ንግድ ስለሆነ አዋጩን ጥናት መምረጥ ያሻል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የኢኮኖሚ አዋጭነት አጥኝዎች ኮሚሽን በማቆቆም ልሂቃን የአዋጭነት ጥናት አማራጮች በማቅረብ ለሀገርና ህዝብ የሚጠቅመውን ከተለያዩ ወደቦች መሃል አንዱን መምረጥ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡
Eritrea Mulls port as Ethiopia rapprochement spurs investors by Nizar Manek 23 Aug 2018 / Bloomberg
Eritrea is considering building a port on its Red Sea coastline to export potash from deposits being developed in the Horn of Africa nation, a mines ministry official said. Plans for the harbor signal he country’s reemergence as a potential investor destination after its surprise rapprochement with neighboring Ethiopia last month ended two decades of political tensions. The facility could be used to ship potash from Ethiopia and adds to a series of port developments in the strategically located region by nations including Djibouti, Somalia, Sudan and the self-declared Republic of Somaliland. The port would be situated at the Bay of Anfile, 75 kilometers east of the 1.2 billion-metric-ton Colluli potash deposit, Alem Kibreab, director-general of mines in the Ministry of Energy and Mines, said in an interview in the capital, Asmara. A feasibility study is under way to decide on the specific site, with the start of construction envisaged about five years after a mine starts operating there, he said.
Existing Port Contruction of the mine is expe to take about two years, before the start of production that will eventually rise to 472,000 tons per year, Crnelius said. Output initially will be shipped from the existing Eritrean port of Massawa, which has sufficient capacity to handle the mine’s exports but is further away than Anfile, he said. Alem said Anfile could be used by potash projects being developed in Ethiopia as an export route, instead of Djibouti, which is farther away. Oslo-based Yara Intternational ASA plans to establish a $700 million potash plant near the Eritrean border, wile British Virgin Islands-registered Circum Minerals Potash Ltd. Has amining license there covering 365 square kilometers.
Diboutian ports authority Chairman Aboubaker Omar Hadi said the country’s Chinese-built Tadjourah port is expected to start potash exports by the start of 2020 and is in talks with exporters like Yara. A 128-kilometer road linking the port to the Ethiopian border is scheduled to open in January, he said. ” it’s a no-brainer than if you could have a port there and potash on the Ethiopian side, obviously you will choose that port,”” Alem said. “”Before the peace came, that was impossibility.”
ለኢትዮጵያ የገቢ ንግድና የወጪ ንግድ የወደብ አገልግሎት ምርጫ
{1} አሰብ ወደብ ኤርትራ፣ የመኪና መንገድ ርቀት ከአዲስአበባ 882 ኪሎሜትር፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{2} ጅቡቲ ወደብ ጅቡቲ፣ ከአዲስአበባ 981 ኪሎሜትር ይርቃል፣ 757 ኪ/ሜትር የኤሌትሪክ ባቡር አገልግሎት አለ፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{3} በርበራ ወደብ ሱማልያ የመኪና መንገድ ርቀት ከአዲስአበባ 937 ኪሎሜትር፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{4} ምፅዋ ወደብ ኤርትራ የመኪና መንገድ ርቀት ከአዲስአበባ 1163 ኪሎሜትር፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{5} ላሙ ወደብ ኬንያ፣ ከአዲስአበባ 1276 ኪሎሜትር ይርቃል፣ የባቡር አገልግሎት በመሠራት ላይ ያለ፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{6} ፖርት ሱዳን ወደብ ሱዳን፣ ከአዲስአበባ 1900 ኪ/ሜ ይርቃል፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ የመኪና መንገድ አለ፣ ፖለቲካ ተግዳሮት የለም፡፡
{7} ሞምባሳ ወደብ ኬንያ የመኪና መንገድ ርቀት ከአዲስአበባ 2067 ኪሎሜትር፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
{8} አንፊል ወደብ ኤርትራ የመኪና መንገድ ርቀት ከአዲስአበባ 882 ኪሎሜትር፣ የባቡር አገልግሎት የለም፣ ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል፡፡
ለኢትዮጵያ የገቢ ንግድና የወጪ ንግድ የወደብ አገልግሎት ምርጫ
(Port choice for Ethiopian importers/exporters)
ወደብ
|
አገራት | የመኪናመንገድ ርቀትከአዲስአበባ(በኪሎሜትር)
Road distance from Addis aba(kilometres) |
የባቡር መሥመር ርቀትከአዲስ አበባ(በኪሎ ሜትር) Rail distance from Addis
Ababa (kilometres) |
የመሥመሩ ተግዳሮት
Route limitations
|
አሰብ | ኤርትራ | 882 | የባቡር አገልግሎት የለምNo railway line | ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶልPolitical |
ጅቡቲ | ጅቡቲ | 918 | 781(constructed)የኤሌትሪክ ባቡር ተሠርቶል | አስተማማኝአማራጭ ችግርLack of viable alternatives |
በርበራ | ሱማልያ | 937 | የባቡር አገልግሎት የለም | ፖለቲካ ችግር |
ምፅዋ | ኤርትራ | 1 163 | የባቡር አገልግሎት የለም | ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል |
ላሙLamu | ኬንያ | 1 276 | የባቡር አገልግሎት የለም | በመሠራት ላይ ያለUnder construction |
ፖርት ሱዳን | ሱዳን | 1 900 | የባቡር አገልግሎት የለም | ረዥም የመኪና መንገድLong road distance |
ሞምባሳ | ኬንያ | 2 067 | የባቡር አገልግሎት የለም
|
ረዥም የመኪና መንገድ |
አንፊል | ኤርትራ | 1 163 | የባቡር አገልግሎት የለም | ፖለቲካ ተግዳሮት ተወግዶል |
Source: UNCTAD.
ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ፣ ፖለቲካውን ይቆጣጠራል!!! የፌዴራላዊ መንግሥት መሥራቾች፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተጠቃሚነት መብት አላቸው!!! (19 ነሐሴ 2010 ዓ/ም ተፃፈ)