ትህነግ/ህወሓት የአገው ክልል ምስረታ የሚል አዲስ ፕሮጀክት ነድፏል። በዚህ ፕሮጀክት ላይ ዛሬ ሰቆጣ ላይ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። በስብሰባው ላይም የአዲሱ ሀሳብ አራማጅ ነን ያሉት:_

“ክልላችን ከጋይንት እስከ ተንቤን ነው። ህወሓት ፈቅዶልናል። ብአዴንን ልናስፈቅድ ነው” ብለዋል።

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው:_

1) አገው አማራ ነው፣ አማራ አገው ነው። አትከፋፍሉን
2) ይህን ሀሳብ ይዛችሁ የመጣችሁን በየ መስርያ ቤት እናውቃችኋለን። አይደለም የክልል የአንድ ቢሮ ጉዳይ ማስፈፀም አትችሉም

3) ህወሓት ፈቅዶልናል የምትሉት ለምን እንደሆነ እናውቃለን። ይዛችሁት የመጣችሁት የህወሓትን አጀንዳና ሴራ ነው በማለት አሳፍረዋቸዋል።

#በነገራችን ላይ በዚህ ፕሮጀክት ህወሓት፣ አስፈፃሚው የእነ በረከት ቡድን እና ካርታቸውን እስከ ራያ የሚስሉት ፅንፈኛ ብሄርተኞች ፕሮጀክት መሆኑ ተደርሶበታል። የአማራ ብሔርተኝነት አስጊ ነው ብለው ያሰቡት ሶስቱ አካላት በአማራ ሕዝብ ላይ በአንድነት እየሰሩ ነው።

ህወሓት ከቅማንት ጉዳይ ባሻገር የያዘው አጀንዳ ነው። እነ በረከት በተላላኪነት፣ አማራውም በአጀንዳ ለመወጠር ብሎም ለማዳከም፣ በፓርቲ ስልጣን ጉዳይም የእነ ገዱን ቡድን ለመገዳደር የያዙት አጀንዳ ነው። አክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኞች በሕልማቸው የሚያስቡትን ረዥም ካርታ ለማሳካት የአማራውን ሕዝብ አጀንዳ ለመስጠት እየሰሩበት ያለ ጉዳይ መሆኑ ተደርሶበታል።