ውሳኔዎቹ በጉባኤው ከፀደቁ በኋላ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን አንኳር አንኳር ጉዳዬቹ በቀላል ቋንቋ የሚከተሉት ናቸው።
1.የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ርዕዮታለምን በሌላ ለመቀየር እቅድ ተይዟል።የቡድን ብቻ ሳይሆን የግለሰብ መብትን የሚያስከብር ርዕዮታለም ይቀረፃል።
2.የብአዴንን ስም ይቀየራል
የብአዴን አርማ/ሎጎ ይቀየራል።
A.የክልሉን ሰንደቅ አላማ ለመቀየርና የፌደራሉም እንዲቀየር ሀሳብ ለማቅረብ እንዲሁም የአማራንም የኢትዮጵያንም ህዝብ ባህል፣ ስነልቦናና ታሪክ ባገናዘበ መልኩ ለመተካት ተወስኗል
B.ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የአማራ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አህዴፓ) ሊባል ይችላል።ስሙ የግል ፍላጎቴ ነው ሃሃሃ
3.ከማዕከላዊ ኮሚቴ አመራርነት ውጭ ያሉ ነባር ታጋዮች በማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሌሎች ወሳኝ ጉባኤዎች እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያ እንዲቀየር ተስማምተዋል
4.ለብአዴን አባልነት አማራ ያልሆነ ሁሉ ይችላል የሚለው ድርጅቱ ለአማራ እስከሆነ ድረስ አባላቱም ከአማራ ህዝብ መሆን አለበት በሚል ተወስኗል።ይህ የቀድሞው እና አሁን የተቀየረው የብአዴን የአባልነት መስፈርት በኦህዴድ፣ ህወሃትና ደኢህዴን ውስጥ የማይተገበር ብአዴን ውስጥ ብቻ የሚተገበር ነበር።
5.ነባር አመራሮች በጡረታ እንዲገለሉ ተወስኗል።እነ በረከትና ታደሰ እንዲታገዱ ተወስኗል።ለማገድ ጉባኤውን መጠበቅ ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ ቢነሳም ከሁኔታዎች አንፃር ቀድሞ ለማገድ እንደተገደዱ ታውቋል።
6.የክልሎች ወሰኖች ህዝቡን አሳታፊ በሆነና ህገመግስቱን ባማከለ መልኩ እንዲካሄዱ ተስማምተዋል።(የክልሎች ወሰን የተወሰነው ከህገ መንግስቱ መፅደቅ ሶስት አመትን ቀደም ብሎ ሰለሆነ ወሰናቸው ህጋዊ መሰረት የሌለው እና ህዝባዊ ተሳትፎ ያልተደረገበት ነው።
7.በመላው ኢትዮጵያ የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎችም ኢትዮጵያውንያን ራሳቸው ፈቅደው እንዲወስኑ እንጅ በሌላ ቡድን እንዳይወሰንባቸው፣ የተወሰነባቸውም እንደገና እንዲታይላቸው ለኢህአዴግ ምክርቤት እና ስራ አስፈፃሚ ለማቅረብ እና ለመታገል ወስኗል
8.የጥረት ኮርፖሬት ኢንዶውመንቶች ወደክልሉ መንግስት (የአማራ ህዝብ) ሀብትነት እንዴዛወር ወስኗል።የShare holdersም ሀብቱን እንዳያዘዋውሩ ማስፈፀሚያ ህግ ሊወጣ ይችላል ተብሏል።
9.ብአዴን ሳያውቀው በኢትዮሱዳን በኩል የአማራን መብት በደፈረ መልኩ መሬት ተሰጥቷል፤ ይህ ወንጀልም ምንም በማያውቁት አመራሮች ተሳቧል።ይህ የመሬት ገዳይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራበታል።የአማራ አርሶ አደር መሬት በአማራ ቁጥጥር ስር ይውላል።
(የብአዴንን የውሳኔ ሀሳብ ሌሎች እህት ድርጅቶችም በበጎው አይተው አብረውት ይሰለፋሉ ተብሎ ይገመታል።ይህንን የማይቀበል ደግሞ ተመልሶ ደደቢት በረሃ የሚገባ ይመስለኛል።ምክንያቱም የዛሬ 40 ዓመት በቀረፁት ርዕዮታለም እና የትግል ሰነድ ሀገር አይመራምና)