ብአዴን በረከት ስምኦንን እና አቶ ታደሰ ካሳን የጥረት ኮርፖሬትን ንብረት በማባከንና አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ሕዝብ ጥቅም ስለማያስጠብቁ በሚል ምክንያት እስከ የሚቀጥለው ድርጅታዊ ጉባኤ ድረስ አግጃለሁ!” በማለቱ በደስታ ጮቤ የረገጡ ወገኖችን እያየሁ ነው፡፡

ነገር ግን እርምጃው ጊዜያዊ እገዳ እንደመሆኑ የታገዱት እነበረከት ላለመመለሳቸው እርግጠኞች አይደለንምና ደስታቹህን በቅጡ አድርጉት ማለት እፈልጋለሁ፡፡

ሲቀጥል የሕዝብ ጥያቄ እነኝህ እና ሌሎች የወገናችንን ደም ጭልጥ አድርገው የጠጡ አውሬዎች ለፈጸሙብን ግፍና ዝርፊያ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢና ተመጣጣኝ ፍርዳቸውን እንዲያገኙ እንጅ ከዘረፉት የሕዝብ ሀብት ጋር ተሸኝተው በድሎት እንዲኖሩ እንዲደረግ አይደለም ሕዝብ የጠየቀውና የታገለው፡፡ ስለሆነም ይህ የሕዝብ ጥያቄ ተፈጻሚ እስካልሆነ ጊዜ ድረስ ሸፍጥ በተሞላ በብአዴን ውሳኔ መደሰት መፈንጠዝ ግልብነት ነውና አድቡ!!!

በመጨረሻም ብአዴን እነኝህን ግለሰቦች አማራ ባለመሆናቸውና የአማራን ሕዝብ ስለማይወክሉ!” የሚል ምክንያት መጨመር ሲኖርበት ንብረት ስላባከኑ፣ ወቅታዊ አቋማቸው የአማራን ሕዝብ ጥቅም የሚያስጠብቅ ባለመሆኑ!” የሚለውን ምክንያት የተጠቀመው በሌሎች ብአዴንን በሚዘውሩት በሚያሽከረክሩት ብአዴን ውስጥ በብዛት ባሉ ትግሬ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ ላለመውሰድ በማሰብ በመሆኑ አሁንም ትግሬ ከብአዴን ተመንጥሮ እስካልወጣና እስካልተወገደ ጊዜ ድረስ መወገድ ብቻ ሳይሆን በፈጸሙት ወንጀልና ግፍ ልክ ተጠያቂ እስካልተደረጉ ጊዜ ድረስ አሁንም ደስታ የለምና አድቡ!!!

ዝምብሎ በምኑም በምኑም ጮቤ መርገጥ አቅለ ቀላልነት፣ ግብዝነት ነውና አድቡ!!! እንደ ሕፃን ልጅ በምኑም በምኑም የምንደለል የምንታለል መሆን የለብንም!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com