ይሄ አጭሉግ ጭራሽ እኮ ማሰብ ማገናዘብ የማንችል ነፈዞች አድርጎ እኮ ነው የሚያስበን!!! ወይ ነዶ!!!
ለነገሩ ልክ ሳይሆን ይቀራል??? ምክንያቱም በሚያደርጋቸው ተራ የመደለያና የማወናበጃ ተግባራቱ ስንቱን ማጃጃል እንደቻለ በየዕለቱ እየተመለከተ እንዴት እንደዚህ አያስበን???
ዐቢይ ዛሬ ይሄ የምታዩትን ፎቶ (ምሥለ አካል) በማኅበራዊና በመደበኛው የብዙኃን መገናኛዎች የለቀቀው አገዛዙ ድሃ አቋጣሪ፣ ለዝቅተኛው ኅብረተሰብ አሳቢ፣ ለዜጎች ደኅንነትና መብት ተቆርቋሪ መስሎ በመታየት የኢትዮጵያን ሕዝብ አንጀት ለመብላት፣ ልባችን ላይ ለመጎዝጎዝ መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡
ይታያቹህ! ዐቢይ ማለት የሶማሌ ክልል በሚሉት የሀገራችን ክፍል የሚኖሩ ሶማልኛ ተናጋሪ ዜጎች እንደሚወራው መስሏቸውና ለዘመናት ሲፈጸምባቸው የነበረውንና ያለውን ኢሰብአዊ ግፍ፣ ይፈጠራል ብለው የሠጉት አደጋና ቀውስ “ዐቢይ እንዲፈጠር አይፈልግምና ፈጥኖ መፍትሔ ይሰጠናል!” ብለው ተስፋ በማድረግ ሶማሊኛ ተናጋሪው ሕዝብ ከምሁራን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከእስልምና መሪዎች ወዘተረፈ. የተውጣጡ በርካታ ተወካዮችን ልኮ ለበርካታ ቀናት ከጠ/ሚ ጽ/ቤት ቅጽር ውጭ ደጅ ሲጠኑ ቢከርሙም መልስ እንኳ የሚሰጣቸው አጥተው “መልስ ካላገኘን በስተቀር ወደ ሕዝባችን አንመለስም!” በማለታቸውና በየቀኑ ደጅ መጥናታቸውን ማቆም ባለመቻላቸው በመጨረሻ ላይ ዐቢይ ያውም በመልእክተኛ ነው እራሱ አይደለም ለአገዛዙ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል በእነሱ ላይ አብዲ ኢሌና ልዩ ኃይሉ የሚፈጽመውን አረመኔያዊ ግፍ ከምንም ባለመቁጠርና የተሠጋው ቀውስ እንዲፈጠር በመፈለግ “በክልሉ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም!” የሚል ሕጋዊ የሚመስል ነገር ግን የለየለት ሕገወጥና ፈጽሞ ኃላፊነት የጎደለው፣ ጠያቂ አካል ካለም በከፍተኛ ኃላፊነትን ያለመወጣት ወንጀል ሊያስጠይቀው የሚችለውን መልስ በመስጠት መልሷቸውና እነኝህ ሰዎች “ኧረ የመንግሥት ያለህ! ቀውስ ሊከሰት ነው፣ ሰብአዊ መብቶቻችን በሙሉ ተጥሰው ሰቆቃም ተፈጽሞብናል እየተፈጸመብንም ይገኛል ማዕከላዊ መንግሥት ፈጥኖ ይድረስልን፣ ፈጥኖ ጣልቃ ይግባና ያንዣበበው ቀውስ እንዳይከሰት ያድርግ!” ያሉት ቀውስ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ጽ/ቤትም በየደረጃው ላለው የአገዛዙ አካላት እስከ ዐቢይ ድረስ ከፍተኛ ሥጋት መኖሩን በማስረጃ አስደግፎ አመልክቶ እያለ እንኳን የአካባቢው ተወላጅ ሕዝብ “ድረሱልን አለቅን!” እያለ ይቅርና ባይልም እንኳ ችግሩ እስካለ ጊዜ ድረስ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 74፣ 77፣ 93 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 359/95ዓ.ም. መሠረት የክልሉ መንግሥት ከሚሉት አካል ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ጣልቃ ገብቶ መፍትሔ መስጠት ሲችል ለአገዛዙ ርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ሲል ሆን ብሎ ኃላፊነቱን ባለመወጣት፣ አግባብነት ያለው መልስ ባለመስጠት ክፍተቱ እንዲፈጠርና ቀውሱ እንዲከሰት አድርጎ በዘግናኝ አኳኋን ሕዝብ አስፈጅቶ፣ ሕፃናትን አስደፍሮ፣ አብያተክርስቲያናትንና ሌሎች ቤት ንብረቶችን እንዲወድሙ፣ አካባቢው በቀውስ እንዲናጥ አድርጎ ሲያበቃ ይሄንን ባደረገ በቀናት ልዩነት ውስጥ ደግሞ ዛሬ ጥቂት እንኳ ሳያፍር ይሄው ይሄንን ፎቶና ትዕይንት በማኅበራዊውና በመደበኛው የብዙኃን መገናኛ ለቀው በማጥለቅለቅ ለአንድ ዝቅተኛ ዜጋ እንኳ ሳይቀር አሳቢ ተቆርቋሪ መስሎ በመታየት ሕዝብን ለማጃጃል ጥረት ማድረጉ እጅግ እጅግ አሳፋሪና ነውረኛ ተግባር፣ ጤና የተለየው እፍረተቢስነትም ነው፡፡
ከዚህ የበለጠ ንቀት አለ ወይ??? በዚህ ደረጃ እየተጃጃልንስ ንቀቱ አይገባንም ወይ??? እስኪ ታዘቡ በዚህ ሆን ተብሎ እንዲፈጠር በተደረገው ቀውስ ጉዳይ ቀውሱ ሆን ተብሎ እንዲፈጠር እንዲፈጸም የተደረገ ለመሆኑ በቂ መረጃ እያለ እስኪ የትኛው ለሕዝብ ቆሜያለሁ ባይ የፖለቲካ (የእምነተ አሥተዳደር) ድርጅት ችግሩን በትክክል በተመለከተ አኳኋን መግለጫ አውጥቶ ማን አወገዘ??? እንኳን የፖለቲካ ድርጅቶች የቀውሱ ከፍተኛ ተጎጅ የሆነችውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን እየመራ ያለው አካል እንኳ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ ትቶ አይደለም ወይ አገዛዙን ተጠያቂ ላለማድረግ የሆነ ያልሆነውን ሲቀባጥርብን የሰነበተው???
እኛ ምእመናንስ ይሄንን አደገኛ ሸፍጥ በቁጣ ወጥተን አወገዝን ወይ??? ታዲያ እኛ ያልተናቅን ማን ይናቅ??? እኛ ያልተላገጠብን ማን ይላገጥበት???
እግዚአብሔር ይበቀላቹሃ ሌላ ምን እላለሁ???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com