‹‹ይህ በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ሥራ ይሠራል የሚባለው ፍጹም የማይታሰብና ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ሕዝቡም ማንም ፍታ ስላለው ጠመንጃውን የሚያስረክብ አይደለም፡፡ አርሶ አደሩ ተደራጅቶና ሕጋዊ መሳሪያ ይዞ ሰላሙን እንዲያስጠብቅ እናበረታታለን እንጅ ትጥቁን አናስፈታም፡፡ እንዲያውም ለክልሉ ሰላምና ጸጥታ መጠበቅ ሕጋዊ አሠራርን በተከተለ መልኩ የማስታጠቅ እንጅ የማስፈታት ዕቅድ የለንም፡፡ ሕዝቡ በአሉባልታ መረበሽ የለበትም፡፡››
(አቶ ገዱ አንዳርጋቸው)

Belay Manaye
————————-

ተው! ተው! ተው! አይበጅም!

Getachew Shiferaw

ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት “በፌደራል ደረጃ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሀገር ቤት የገቡ የተቃዋሚ ሃይሎች የታጠቁ ሃይሎች ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ ይደረጋል” ሲል ተናግሯል።

ባለፈው የገበሬዎች ፎቶ እየተለጠፈ “የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች ናቸው” ተብሎ ፕሮፖጋንዳ ተሰርቶበታል። ይሁንና ግንቦት 7 ሲገባ ገበሬዎቹ ቆየት ሲል የተወረሰባቸውን መሳርያ እንደሚመለስ እንዲሁም ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ተደርጎ እንደተቀረፀ እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤም ገበሬዎቹን አግኝተው አረጋግጠዋል። ገበሬዎቹም በቪዲዮ በሰጡት መልስ ይህንኑ አረጋግጠዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች ናቸው ተብለው ፎቶው የተለቀቀባቸው ገበሬዎች ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነም ገልፀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ወታደሮች ናቸው ተብሎ ፎቷቸውን ያየው የአካባቢው ፖሊስ ለክልሉና ለፌደራል ፖሊስ አመልክቶ የገበሬዎቹ ተወካዮች ባህርዳር ድረስ ተጠርተዋል።

ጉዳዩ በዚህ ያበቃል ሲብል ዛሬም በመራዊና በዳንግላ አካባቢ ገበሬዎችን እየሰበሰቡ ፎቶ እያነሱ ነው። ፎቶ ከተነሱት መካከልም ዝርዝር መረጃዎችን ያደረሱን አሉ። ይህ ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም የተቀረፀ ፎቶ ሲወጣ ነገም ገበሬዎቹ ተመሳሳይ ወከባ እንደሚደርስባቸው ግልፅ ነው።

ከምንም በላይ ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት እንደተናገረው ግንቦት 7 የእኔ ናቸው የሚላቸው ገበሬዎች መሳርያቸውን እንዲያወርዱ ይደረጋል።

ይህ ገበሬውን መሳርያውን እንዲያወርድ የሚያደርግ የርካሽ ፖለቲካን ደግሞ መታገስ አይገባም። ይህን ያልተገባ የፖለቲካ ትርፍ ስናጋልጥ ብዙ ሰው የጎንዮሽ ትግል ይመስለዋል። ብአዴን ይሁን አብን፣ ግንቦት 7 ይሁን ሌላ በገበሬው ላይ መሰል ደባ ሲሰራ ዝም ማለት ተገቢ አይደለም።

ለድርጅቱ የምታስቡ ሰዎች ካላችሁ ይህን ርካሽ ንግድ እንዲቆም ብትነግሯቸው ይሻላል።