“ከኢትዮጵያዊነት መውረድ ባንዳነት ነው።”
(ዶ/ር ዳኛቸው ዘውዴ)

ኢትዮጵያዊ ችግርን ለመፍታት ኢትዮጵያዊ መፍትሄዎችን ማቅረብ እንጂ ከኢትዮጵያዊነት ወርዶና በገዳይ የርዕዮት ፈረስ መጋለብ ‘ተኩላን ያመለከችውን አህያ (the jackass worshiped the jackals) መሆን ብቻ ነው።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

አይሁዶች፣ ቼኮች፣ ፓሊሾች፣ ሩሲያዎችና ጀርመኖች ወ.ዘ.ተ. በሂትለር የተቃጣባቸውን የህልውና ጥቃትን ለመከላከል የናዚ ርዕዮት ተቀብለው ናዚዎች አልሆኑም። የአርያን ዘርን መስለውና አርያኖችንም ሆነው አልተደራጁም። ጣሊያኖችም እንደዚሁ ሞሶሎኒን ተከትለው ፋሺስት አልሆኑም። ጀርመኖችም ጀርመናዊ፤ ጣሊያኖችም ጣሊያናዊ ሆነው ነው ናዚዝምንና ፋሺዝምን እንደ ክፉ ሥርዐት የተዋጉት።

ጣሊያን ኢትዮጵያን ስትወርና በቅድሚያ ‘አማራንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ማጥፋት” በሚል መሪ ቃል (motto) ስትዘምት ጀግናው አፄ ሚኒሊክ ምላሽ የሰጡት በኢትዮጵያዊነትና ከኢትዮጵያውያን ጋር በኢትዮጵያዊ ሕብረት፣ ክብርና ጀግንነት ነበር። የድሉም ሚስጥር ይህ ነው።

በአንድ ጎን በጎሣ ፓለቲካ ተዘውረው በጎሣ እየተደራጁ አደረጃጀቱን የጎሣ ፓለቲካ “ፀበል” እየረጩ፤ በሌላ መልኩ ይህን ጎሣዊና ቋንቋ ተኮር አደረጃጀትና ርዕዮቱን “የጎሣ ፌደራሊዝም” ማውገዝ በአንድ እራስ ሁለት ምላስ (doublethink) ነው::

“በጎሣ ፌደራሊዝም” አደረጃጀት ውስጥ አንድ ጎሣ የሚኖረውን ተሣትፎ መስበክ ይህን እንሠሣዊ ርዕዮት ማወደስና ዴሞክራሲን ማሣነስ ነው:: “የጎሣ ፌደራሊዝም” የህልውና መሠረት የጎሣ ብሔረተኝነት፣ የዴሞክራሲም መሠረቱ ሲቪክ ብሔረተኝነት ብቻ ነው:: የመጀመሪያው በጎሣ ምንነት ላይና በአግላይነት የኋለኛው በዜግነትና በአሣታፊነት እሣቤ ላይ ያጠነጥናል::

“በጎሣ ፌደራሊዝም” እና ጎሣዊ ብሔረተኝነት ሐገራዊ አንድነትና ዴሞክራሲ ወይም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጭራሹን አይታሰብም:: “በጎሣ ፌደራሊዝም” እና ጎሣዊ ብሔረተኝነትን (Ethnic Nationalism) ፓለቲካዊ የአደረጃጀት ቅርፅ እየሠጡ ከአንድነት ይልቅ ለልዩነት መስመር እያሠመሩ መጓዝ “ለጎሣ ፌደራሊዝም” እውቅና መስጠትና ነባሩን ጭቃ ማቡካትና በህዝብ ላይ መለሠን ነው::

የጎሣን ፓለቲካ በጎሣ ፓለቲካ አይመክንም። ፓለቲካ ርዕዮት እንጂ የተሸነቀረ እሾክም አይደለም። የጎሣ ፓለቲካ ወደ ዘር ማፅዳትና ጭፍጨፋ የሚውስድ አውራ መንገድ ነው። የሕዝብንና የሐገርን የመኖር ህልውና አደጋ ላይ ይጥላል። የጎሣ ፓለቲካና ውጤቱ የሆነው የሃገርና የሕዝብ የህልውና ጥቃት ከሥሩ ተገንድሶ የሚወድቀው የዴሞክራሲ ሥርዐትና የሕግ የላይነት ሲሰፍን ብቻ ነው።

በመንጋው ከተሠላ የተሣሳተ ሃሣብና አመለካከት ጋር ከመንጎድ (swimming with the stream) በማስረጃና በመረጃ በምክንያታዊነት ከታነፀ ሃሣብና ዕይታ ጋር መክነፍና የማህበር እሣቤን መግፋት (going against the tide of prevailing opinions) ይበጃል::
ለአንድ ዓይነት ጥያቄ፣ ሃሣብና አመለካከት ሁለት ዓይነት መልስና ግንዛቤና ማዘል ስህተት ነው::

ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀጭጨው “የጎሣ ፌደራሊዝም” እና ጎሠኝነት ነው:: በጎሣዊ አደረጃጀትና “የጎሣ ፌደራሊዝምን” በአንቀልባ እሹሩሩ እያልን ኢትዮጵያዊነትን ማምጣት አይቻልም:: “የጎሣ ፌደራሊዝምን” ጎሠኛ አደረጃጀት ተላብሰን ሌላውን ጎሠኛ ማለትም ግብዝነት ነው። የጎሣ ጥቃት ደረሰብን ብሎ ማላዘንም ‘የአዞ እንባ’ መርጨት ነው።

የኢትዮጵያም ይሁን የጎሣዎቿ አባላት ችግር የሚፈታው በሕግ የበላይነትና በዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታና መርሆዎች ብቻ ነው:: ጎሣዊ አደረጃጀትና “የጎሣ ፌደራሊዝም” በተግባር የሚታወቁት ችግርን ሲሠሩና ሲፈጥሩ ነው:: የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ችግር ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ አይደሉም:: ችግሩ የፓለቲካ ሥርዐቱ እርሱም “የጎሣ ፌደራሊዝም” ነው:: ችግር የሚፈታው በችግሩ ሣይሆን የችግሩን መንስኤ የሆነውን “የጎሣ ፌደራሊዝም” ነቅሶ በማውጣት ለችግሩ ሌላ መፍትሄ በመፈለግና ችግሩን ከሥሩ መንቀል ሲቻል ነው:: መፍትሄውም አሁንም የሕግ የበላይነትና ዴሞክራሲ ሥርዐት ነው::

“ዴሞክራሲ ሁለት ተኩላዎች እና አንድ በግ ምሣቸው ምን እንደሚሆን በድምፅ ብልጫ የሚወሥኑበት ነው::
መብትና ነፃነት በሚገባ የታጠቀው በግ የነዚህን የተኩላዎች ድምፅ አሰጣጥ የሚቃወምበት ነው”
(ቤንጀሚን ፍራንክሊን)

“Democracy is two wolves & one sheep voting on what to have for lunch.
Liberty is a well-armed sheep contesting the vote”
(Benjamin Franklin)