አቶ በረከት ሲሞኦን በሰይፉ ፈንታሁን ፕሮግራም ብዙ አስገራሚ ቃለ ምልልስ
ከብአዴን እስከ መጪው መስከረም ድረስ የታገደው አቶ በረከት ስምዖን ከብአዴን የታገድኩት በኢሳያስ አፈወርቂ ምክር መሆኑን ተናገረ:: ከጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ጋር በኤፍ ኤም ራድዮ ቃለምልልስ ያደረገው በረከት ከዶ/ር አብይ ጋር ዛሬ ጠዋት ተደዋውለን ነበር ብሏል::
ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ኤርትራ በሄደበት ወቅት ከርሱ ጋር አብረው አንዳንድ የአማራ ክልል ባለስልጣናትም መሄዳቸውን የገለጸው አቶ በረከት ሃይለማርያም ኢሳያስን “ህወሃቶቹና ነባሮቹ አስቸገሩን” ብለው ነግረውታል ብሏል::
“ባህርዳር የማ/ኮሚቴ ለመሳተፍ የደህንነት ዋስትና አልተሰጠኝም። መታገዴን የሰማሁት ከሚድያ ነው። የብአዴን መሪዎች ስልክ አያነሱልኝም።” የሚለው በረከት አሁን ያለው የብ አዴን አመራርም ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው በማለት በአደባባይ ውንጀላ አቅርቧል::
ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ መቼ ተገናኛችሁ በሚል በሰይፉ ፋንታሁን ለቀረበለት ጥያቄ አቶ በረከት ሲመልስም ዛሬ ጠዋት በስልክ አነጋግሮኛል ብሏል:: ሥራ አዞኝም እርሱን እየሰራሁ ነው ብሏል::
ሙሉ ቃለምልልሱ በዘ-ሐበሻ ኦፊሻል ዩቱብ ገጽ ይገኛል::
https://youtu.be/oPfFmeb3TVY