August 27, 2018
“እኔ [መሪ] አልነበርኩም:: እኔ የአመራሩ አባል ነኝ እንጂ ቦታውን የያዝኩት እኔ አልነበርኩም:: በልኬ የማድር ሰው ነኝ እኮ::” – ዓይኑን በጨው የታጠበው የውሸቱ አባት በረከት ስምኦን
ጉደኛው በረከት ስምኦን እራሱን ብፁህና ምጡቅ አድርጎ ባቀረበበትና ከጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛ ነጋሽ ሙሃመድ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ “አስተያዬት ሰጪ እንጂ ወሳኝ ባለስልጣን አልነበርኩም” እያለ የተንኮል ስራውን ሽምጥጥ አድርጎ ይክዳል:: በረከት ከአንጋፋው የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛ ነጋሽ ሙሃመድ ጋር ባደረገው ትንሽ ቆይታ በግርምት ቅንድብ የሚያሰቅሉ ብዙ የክህደት ንግግሮችን አድርጏል:: ከሁሉ የገረመኝ ግን የሚከተለው ነው:-
በረከት:- “…ባለፉት 5 ዓመታት ትልቁ ፈተና የነበረው መሪዎች እራሳቸውን ለማብቃት ትኩረት አልሰጡም:: የፖለቲካ ውይይት ለማድረግ እንኳ ፈቃደኝነቱ የነበረው አመራር አልነበረም:: አንድ አጀንዳ ጀምሮ የሚጨርስ አመራር አልነበረም::”
ጋዜጠኛ ነጋሽ ሙሃመድ:- “እርስዎም እኮ መሪ ነበሩ አቶ በረከት; አይደለም?”
በረከት:- “እኔ [መሪ] አልነበርኩም:: እኔ የአመራሩ አባል ነኝ እንጂ ቦታውን የያዝኩት እኔ አልነበርኩም:: በልኬ የማድር ሰው ነኝ እኮ:: ሃላፊነቱን ያስረከብኳቸውን ሰዎች አክብሬ በእነሱ ስር ነው የምኖረው:: አስተያዬት ልሰጥ እችላለሁ የሚወስኑት ግን እነሱ ናቸው:: ስለዚህ በእኔ ደረጃ ‘መሪ ነበርክ’ የሚለውን አሳምሽን’ (ግምት) ‘አሳምሽን’ ብቻ ብዬ ነው የምወስደው::”
ከዚያ ሁሉ የበረከት የክህደት ንግግር በሗላ ጋዜጠኛ ነጋሽ ሙሃመድ ምን ብሎ ቃለመጠይቁን ቢዘጋ ጥሩ ነው…”በጣም አመሰግናለሁ አቶ በረከት ስምኦን የኢህአዲግ ነባር ታጋይ; የኢትዮጵያ መንግስት የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣን ለሰጡኝ አስተያዬት::”
Sintayehu Chanyalew
https://youtu.be/Isy4QXX-LyA
https://youtu.be/Xo5dUikWzfo