August 27, 2018

የኢትዮጵያ፤የውዪዪትና፤መፍትሔ፤መድረክ
Ethiopian Dialogue Forum
ethiodialogueforum@gmail.com
Tel: 919 641 0267
9900 Greenbelt RD. E#343 – Lanham, MD 20706

ለዜና ማሰራጫዎች ሁሉ:-

ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህ የለውጥ ጊዜ ኢትዮጵያውያንን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃ ሆኖ ይታያል። በዚህ የለውጥ እንቅስቃሴ ወቅት የለውጡ ሃይል ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተደምረው ለውጡን እንዲደግፉ ጥሪ በተደረገላቸው መሰረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲደግፉ ይታያል። የለውጡን ሃይል የመደመር ፖለቲካ ለመደገፍ የድጋፍ ሰልፎች በብዙ ቦታ እየተካሄደ ነው። ተደምረናል! ተደምረናል!!…. የሚለው ሃሳብ ገዢ ሆኗል። በርግጥ ታዲያ ይህ የመደመር መርህ በበጎ ሃሳብነቱ ቅቡል ነው። ይህ ቅቡል ኣሳብ ከሃሳብነቱ ኣልፎ ወደ ተግባር የምንገባበት ዋዜማ ላይ ነን። እስካሁን በለውጡ ሃይል የተገቡ የመደመርን መርህ በተግባርና በህግ ማእቀፍ የምናይበት ወቅት እየመጣ ነው። ታዲያ ይህ የመደመር መርህ ከኢኮኖሚ ኣንጻር የሚኖረው የኢኮኖሚ ስትራክቸር ምን መምሰል ኣለበት? መደመር በኢትዮጵያውያን የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ውስጥ እንዴት መገለጽ ኣለበት? መደመርን መሰረት ያደረገ ህገመንግስት እንዴት ይኖረናል? በመጀመሪያ ህገ መንግስቱ የመደመርን መርህ በምልዓት ይገልጻል ወይ? የተደመሩ ኢትዮጵያውያን ቃል ኪዳን ነው ወይ? ከባህልና ከቋንቋ አንጻር መደመር እንዴት ይገለጻል? ማንነት እንዴት ይደመራል? ታሪክ በመደመሩ ሂደት ምን ሚና ኣለው? የሚዲያዎች መደመር እንዴት ይገለጻል? ና የመሳሰሉ ጭብጦችን ይዘን በጥልቀት መወያየት ያለብን ሰዓት ላይ ነን።

የኢትዮጵያ የምክክር ኮርፖሬሽን EDF (Ethiopian Dialogue Forum) በነዚህ ጭብጦች ላይ ውይይት ለማድረግ የፊታችን መስከረም 8 ቀን 2018 በዋሽንግተን DC በኢትዮጵያ ኤምባሲ ኣዳራሽ ውስጥ የአንድ ቀን ሙሉ ኮንፈረንስ ያደርጋል። በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ከየሙያው ሊቆችን ጠርተናል። ለሽግግር የሚሆኑ፣ ለፖለሲ ግብዓት የሚሆኑ ኣሳቦችን ከዚህ ስብሰባ እንጠብቃለን። የሃገራችንን የለውጥ ሃይል ገንቢ የለውጥና የፖሊሲ ኣቅጣጫዎችን ኣሳቦችን ከዚህ ኮንፈረንስ እንጠብቃለን። በመሆኑም በዚህ የአንድ ቀን ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት ውይይቱን ለኢትዮጵያውያን እንድታስተላልፉልን እንጠይቃለን። ለተጨማሪ መረጃ በመደወል ማብራሪያ ልታገኙ ትችላላችሁ።

ከአክብሮት ጋር!


የኢትዮጵያ የውይይትና መፍት ሄ መድረክ ኮንፈረንስ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ

ፕሮፌሰር አቻምየለሀ ደበላ

ተደምረን እንሻገራለን!” ዶክተር አብይ አህመድ