*★★★
– ነገ ግን ጊዜው ሲደርስ በወርቅ ይሠራል!!!
ዘመድኩን በቀለ
– የሆነ እንግዳ የሆነ ደብዳቤ ሰሞኑን እንዲህ ሲል ሰነበተ።
“የአዲስ አበባ ቆርቋሪና መሥራች፣ የዓደዋው ጦርነትና ለተገኘውም ድል ቁልፏና ወሳኟ ሴት፤ ለእምዬ ምንሊክ ባልተቤት ለነበሩት ለእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ የመታሰቢያ ሃውልት ሊሠራ ነው። እናም የፊታችን ሐሙስ ዛሬ ማለት ነው። ነሐሴ 24/2010 ዓም ከቀኑ 7:30 የዓደዋ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ሲግናል አደባባይ ላይ እንድትገኙ፤ በሥነ ሥርዓቱም ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታደለ ኡማና ከረጅም ዓመታት የስደት ህይወት በኋላ ወደሀገሯ የተመለሰችው አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆም በክብር እንግድነት ይገኛሉ” የሚል መልእክት ተሸክሞ በዚሁ በፌስቡክ መንደራችን ሲንጎማሸር ዋለ።
~ መሸ ነጋም #ሀገር_ወዳድ_ኢትዮጵያውያንም ይህን ዜና በሰሙ ጊዜ ከመደሰታቸው ብዛት የተነሳ ምድሪቱ አልበቃ አለቻቸው። ፈነጠዙ፣ ጨፈሩ፣ በደስታም ሰክረው አቅላቸውንም ስተው ሲፈነጥዙ ዋሉ፣ አደሩም።
~ ወዲያውኑ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ደግሞ ይህን ዜና በሰሙ ጊዜ እንዲህ አሉ። ፊኒፊኔን ኬኛ። እስቲ ወንድ የሆነ ሃውልቱን ሲያቆም፣ ደግሞም ሲሠራ እናያለን። ተደምረናል ስንል የምር መሰላችሁ እንዴ? ኦሆሆ እስቲ ሞክሯት። ዋ ! እንተያያለና ብለው እሪሪሪሪ አሉ። እሪሪሪ አሉ አይገልጸውም።
★ ክርክሩ ዳኝነት አሰፈለገው

“በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያለው መረጃ ሁሉ እንደ እውነት ከተወሰደ አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል…” በማለት በውስጠ ዘ “የኦሮሞ አክቲቪስቶች ያሉት ትክክል ነው”። እናም [ የእቴጌ ሃውልት አይሠራም ]። አከተመ። አራት ነጥብ። ብለው ክርክሩን ዘጉት።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከ400 በላይ ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ያንፀባረቁበትን ጦማሮቻቸውን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ ሲደልቱ ውለውና ከርመው መንጋው መስማት የሚፈልገውን ” ኢትዮጵያ ” የሚለውን ቃል እየመረራቸው በመጠቀም ወደከተማዋ ከንቲባነት የሥልጣን እርከን መምጣታቸውን ዘንግቶ በግድ የኢትዮጵያዊነትን ካባ ካልተላበሱ ብሎ ይወበራል። ጓደኛቸው ጠ/ሚ ዶኮ ዐቢይ ኢንጂነሩን ወደዚህ ቦታ ሲያመጧቸው ” ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ” ካላልክ መንግሥትህ አይጸናልህም ብለው እንደመከሯቸው ማወቅ መስማትም አይፈልጉም። እናም ኢትዮጵያዊ መልኩን ነበር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይለቅ ሁሉ ከደም የተዋሐደ ፀረ ኢትዮጵያዊነት መቼም እንዳይለቅ ሊታወቅ ግድ ይላል።
ለቦብ ማርሌ ሃውልት ያቆመች አዲስ አበባ ለመላው ጥቁር ህዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ ላደረጉት ጀግናዋ እቴጌ ጣይቱ ግን ራሳቸው ቆርቁረው ስምም አውጥተው ” አዲስ አበባ ” ብለው ለጠሯት ከተማ ግን ቁራሽ መሬትና አንዲት ሃውልት ተነፈጉ።
