
አስቀድሜ የኢትዮጵያዊነት የአክብሮት ሰላምታዬ ይድረሳችሁ:: ከሁለት አመታት በፊት በኢትዮጵያ ፈዴራል ቴሌቪዥን ጣቢያ የጦፈ ክርክር ይካሄዳል :: የውይይቱ ተሳታፊዎች በሙሉ ባላስታውስም አንድ የኢህአዴግ መንግስት የሕግ አዋቂ ህገመንግስቱን እየተረጎመ ያስረዳል:: የፍሬ ነገሩ ውይይት ስለ ብሄርና ማንነት በኢትዮጵያ ነበር ::ህጉን ተመርኩዞ ሲያስረዳ አንድ ኢትዮጵያዊ የብሄሩ መገለጫ በአባቱ ትውልድ መሰረት ይሆናል ያለውን አስታውሳለሁ:: የውይይቱ አንዱ ተሳታፊ አቶ ዘሪሁን ? ( የዛሚ ራዲዮ ባለቤት) ና የህውሀቶች ወዳጅ እኔ እኮ የጂጂጋ ልጅ ነኝ በማለት ይህ ህግ እንዳልተመቸው ያሳይ ነበር::
ይህ እራሱ ብቻ በቂ ነው አቶ በረከት ስምኦንን ከብአዴን ከፍተኛ አመራር ማባረር:: እቶ በረከት ባረቀቅው ሕግ እሱ እራሱ ኤርትራዊ እንጂ አማራ ሊሆን አይችልም:: የራሴ ዘመዶች ቅድመአያቶቻቸው ከጎንደር መጥተዋል በሚል የአማራን ሀገር ሳያውቁ ጎንደርን ሳይረግጡ መታወቂያቸው ላይ ኦሮሞ ቢያስገቡም እሱ ተሰርዞ አቶ በረከት ያሰለጠኑዋቸው ካድሬዎች አማራ ብለው መታወቂያ ሰጥተዋቸዋል::
የነገሮች ሁሉ መስረቱ መሳከሩ እራሱ የሚያሳየው አንድ ወላጆቹ ኤርትራውያን የሆኑ ግለሰብ አቶ በረከት ስምኦን ለዚያውም እውነተኛ ስሙ በውል የማይታወቅ እንዴት አማራ ሆኖ ለከፍተኛ አመራር ይበቃል? ይህ አማራን በቁሙ የገደለ ፀረ አማራ በምን መመዘኛ እስካሁንስ የፈላጭ ቆራጭነት መብት አገኘ? ጎንደር የአማራ ጉድ አዝለሽ ነበር? ያሰኛል::
ብአዴን አሁንም ጥልቅ ተሀድሶውን በጥልቅ የፅዳት ዘመቻ በማካሄድ ድርጅቱን እንዲያዋቅር ያስፈልጋል:: ማንኛውም የብአዴን አመራር
1. በአማራነቱ ማመን ይኖርበታል:: ይህን በቀላሉ ማወቅ ይቻላል:: አማራ ነህ ለሚለው ቀጥተኛ ጥያቄ እውነተኛው አማራ አዎ ነኝ ይላል:: fake አማራው እኔ ወሎዬ ነኝ መታወቂያ አማራ ነው ይልሀል::
2. በ27 አመታት ህውሀት በኢህአዴግ ውስጥ የበላይ ገዢ ነው? እውነተኛው አማራ በአይን አፍጦ የሚታየውን ሀቅ ለምን ትጠይቀኛለህ ?ይልሀል:: fake አማራው በኢህአዴግ የበላይነትና በታች የለም:: ይህን የሚያራግቡት የትግራይ ህዝብ ጥላቻ ያላቸው ሰዎች ናቸው ብሎ ያሸማቅቅሀል::
3. የአማራ እኩል የኤኮኖሚ ተጠቃሚነት የለም? እውነተኛው አማራ እኛ እኮ እንደሁለተኛ ዜጋ መታየት ከጀመርን ብዙ አመታት አለፉ ይላል:: fake አማራ የእኛን ደካማነት በሌሎች ማስታከክ እንወዳለን:: ይህ የትምክህትና የነፍጠኞች አመለካከት የድሮ ስርአት ናፋቂዎች እጃችንን አንሰጥም የሚል ማስፈራሪያም ይጨመርበታል:: ከአማራ የሚወለድ ” ነፍጠኛ” የሚል ቃል ከአንደበቱ አይወጣም:: ይህ ሊሰመርበት ይገባል::
ለአብአዴን አመራር ብቃት ከDNA የተቀላጠፈ ከላይ የዘረዘርኳቸው ማን ለአማራ እንደሚቆጭ በቀላሉ ገላጭ ናቸው::
ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት በተሞላበት ለአቶ በረከት ስምኦን የሰጠኸው መልስ እያንዳንዱን አማራ የሚያኮራ ግለሰቡን ደግሞ እርቃኑን ያስቀረ ምት መልስ ነው:: እኔ ያፈርኩት ጠያቂ ጋዜጠኞች ተብዬዎች የሰውዬውን ፕሮፖጋንዳ ከማራገብ መሰረታዊ የሆነ ሞጋችና አንኳር ጥያቄዎችን አላስተናገዱም የእሱን አዲስ መፅሀፍ አስተዋዋቂ ከመሆን ባሻገር:: ብአዴን ከአቶ በረከት የሞግዚትነት አስተዳደር እራሱን በራሱ ለማስተዳደር በመቻሉ እንኳን በአማራ ክልል ቀርቶ ከክልሉ ውጪ ያለነውን አማራ አንገታችንን ቀና አድርገን የምንሄድበት ዘመን ስላመጣችሁ ለአዲሱ አመራር ከመቀመጫዬ በመነሳት አከብራለሁ:ትግሉ ግን አላበቃም:: በረከት ስምኦን ለሴራና ሸር ብቻ የተፈጠረ ሰው ነው:: አብሮት የሰራ ባልደረባው አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ስለበረከት ተክለሰውነት በጥሩ ሁኔታ ይገልፀዋል:: ይህ ሰው አሁን የቆሰለ አውሬ ነው:: ለእናንተ አይተኛላችሁም:: አጥራችሁን ጠበቅበቅ አድርጉ:: አማራ ያልጠረጠረ ተመነጠረ ይላል:: ዶክተር ዐቢይ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ እናንተ የምታውቋቸው 18 ያህል የንግድ ባንኮች አሉ በእኛ መረጃ ደግሞ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 100? ባንኮች!! አንዳንድ ባለሀብቶች እስከ 300 ሚሊዮን ብር ድረስ በራሳቸው ካዝናዎች አጭቀዋል:: አቶ በረከት የህውሀት ዘውዳዊ ዘእምነ ነገደ አጋዚያን አገዛዝ የሀበት ክምችት ቁንጮ ከበርቴ ነው:: በቀላሉ ድምፅ የመግዛት ሀይል በእጁ አለ:: ይህን በወንጀል የሚፈለግ ተጠርጣሪ እድል ሰጥታችሁ እሰጣ አገባና የብአዴን ስብሰባ ብታካፍሉት በመሀላችሁ ገብቶ ለመበተን እንደሚችል አልጠራጠርም:: ይህ እንዳይሆን አጥራችሁን ካሁኑ ጠበቅበቅ ማድረግ ከፍተኛ አዋቂነት ነው:: የእናንተ ሀይል የፈዴራል መዋቅር ሳይሆን የአማራ ህዝብ ስለሆነ ህዝባችሁን በተገኘው ሚዲያ አሳትፉ:: ይህ የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው::
መንግስቱ ሀይለማርያምን የናቁ እጅግ ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ሌላው ቢቀር ለቤተስቦቻቸው በህይወት አልተረፉም:: ከበረከት ጀርባ እናት ድርጅቱ ህውሀት ዛሬም አለችለት:: የእናንተ ደጀን የአማራ ህዝብ ከዚያም ደራሽ ወንድም ኦሮሞ ነው::ለአማራ ሕዝብ ህልውና የብአዴን በአዲስ መዋቀር ወሳኝና ለሁሉም አማራ ትልቅ ተስፋ ነው:: በርቱ
ልዑል እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቃት