የኢትዮጵያ ጀግኖች የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስከበር የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚያሳይ ጥናታዊ ቪዲዮ አቅርበንላችኋል። ቪዲዮው በኢትዮጵያ የቅርብ ታሪክ ውስጥ የምድር ጦር (እግረኛ)፣ የባሕር ኃይልና የአየር ኃይል የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያበረከቱትን አስተዋጽኦዎች አጠር ባለ ሁኔታ ያሳያል። ቪዲዮው በተለይም ለመካከለኛና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህርት በዋቤነት ሊቀርብ የሚችልና የተሟላ መረጃዎችን አካቶ የያዘ ነው።
ቪዲዮውን ያዘጋጀው ወጣት አማኑኤል ገበየሁ ሲሆን በአሁን ጊዜ ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዓመት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል። ስለ ቪዲዮው ያለዎትን አስተያየት ለመስጠት በዚህ ኢሜል ይላኩለት።
https://www.youtube.com/watch?v=pxcCl_Cja5g