የትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሰቲት ሑመራ ወረዳ ልኡካን ከ20 ዓመታት በኋላ ወደ ኤርትራ ኦምሃጀር አቅንተዋል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሰቲት ሑመራ ወረዳ የልኡካን ብዱን ከ20 አመታት በኋላ ዛሬ ወደ ኤርትራ ኦምሃጀር ከተማ አቅንተዋል።

የልኡካን ብዱኑ ኣባላት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች የተውጣጡ ሲሆን፥ ቁጥራቸው ከ50 በላይ መሆኑን ተገልጿል።

ነዋሪዎቹ የተከዜ ድልድይ በመሻገር በኦምሃጀር ከተማ ከሚገኘው ከኤርትራ ህዝብና ከሀገሪቱ የሰራዊት ሃይል ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተዋል።

ጉዞው ከኤርትራ ህዝብ ጋር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተነገሯል።

በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን የጎሎመኻዳ ወረዳ 40 ሰዎችን ያካተተው የልዑካን ቡድን ከሁለት ቀናት በፊት ከዛላንበሳ አለፍ ብሎ በሚገኘው ሰርሓ ከተማ መጓዙን ይታወሳል።

የልዑካን ቡድኑ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና እናቶች የሚገኙበት ሲሆን፥ ከኤርትራ አቻዎቻቸው ጋር የሰላም ውይይት አድርጓል።

በጨውን አዲስ ዓመት በዛላአምበሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ከተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች ከተውጣጡ የኤርትራ የልኡካን ቡድን ጋር በጋራ ለማክበር ከስምምነት መድረሳቸውም ተጠቁሟል።

 

Ads by Revcontent
19 Very Cringe Worthy Photos
Ready Set Health
24 Photos Taken Seconds Before Unthinkable Tragedy
Ready Set Health
15 Chilling Childhood Photos of History’s Most Evil People