……
1~ “Ulysses” በተባለው ምርጥ ልቦለድ ውስጥ ላቲቨን የሚባል ገፀ ባህሪ አለ። ይሄ ሰው ስለታሪክ የሚከተለውን ይላል << Histroy is a nightmare,which I am trying to wake> > ( ታሪክ ለመንቃት የምሞክረው ቅዤት ነው) በማለት ይገልፀዋል።
ይሄ አባባል ለኦሮሞ ኤሊቶችና ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ተስማሚ አባባል ነው። ለኦሮሞ ኤሊቶች ታሪክ ቅዤት ብቻ ሳይሆን ሁሌ አልርጅክ እንደሆነባቸው ነው። ታሪክ አልስማማቸው ብሎ ሲፎክቱ ነው የሚውሉት ። እነዚህ ፖለቲከኞች ታሪክን ጭንቅላቱን ቁልቁል እግሩን ወደ ላይ አድርገው ሰቅለውታል። ነገር ግን ታሪክ ቢገድሉት አልሞትም ፣ ቢቀብርቱም አልበሰብስም ብሎ አስቸግሯቸዋል።

2 ~ ትናንት 5 የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች ባወጡት አስቂኝ መግለጫ “ፊንፊኔ በታሪክም ሆነ በህግ የኦሮሞ ናት ” በማለት አላግጠዋል። ይሄ መቼም የክፍለዘመኑ ቅዤት መሆን አለበት ።
ለመሆኑ ፊንፊኔ በታሪክ የኦሮሞ ናት ሲሉ ታሪክን ከየት ጀምረውት ነው?
የታዛባ ታሪክን የሚስተካከለው ከታሪኩ ከመሰረቱ በመነሳት ነው እንጅ ታሪክን ከወገቡ በመጀመር አይደለም ።
ኦሮሞዎች ከታሪክ አንፃር የአዲስ አበባ ባለቤትነት ማስረጃን ሲጠቅሱ ወደ ኋላ መቶ አመታትን ብቻ መሄድ ይፈልጋሉ ። ከመቶ አመታት ገፋ ካደረጉ ቅርቃር ውስጥ እንደሚገቡ ያውቋታል። ታሪክ የባለቤትነት ማስረጃ ሆኖ የሚቀርብ ከሆነ መቶ አመታት ብቻ መጓዙ እርባና የለውም ከዛም በፊት ተጉዞ የ300 እና የ400 አመታትን ታሪክ ማጣቀስ አስፈላጊ እና ግደታም ነው።እስከ 16ኛው ክዘ ድረስ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ኦሮሞ የሚባል ህዝብ እንደማታውቅ እነ አልቫሬዝ፣ ረብ ፋቂህነ በሺህ የሚቆጠሩ የታሪክ ፀሃፊያን ያስቀመጡት ጉዳይ ነው። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ኦሮሞ ኦሮሞ ለበረራ ወይም ለአዲስአበባ እንግዳ ነው እንጅ ባለቤት ፈፅሞ አይደለም ። ከታሪክ አንፃር የአዲስአበባ ባለቤት ኦሮሞ ሳይሆን አማራውና ሌሎች ናቸው።

3~ከህግ አንፃርም ቢሆን የኢፌድሪ ህገመንግስት አንቀፅ 49 አዲስአበባ የሁሉም ብሄርብሄረሰቦች ከተማ እንደሆነችና ባለቤትነቷም በውስጧ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የተሰጠ እንጅ ፈፅሞ ለኦሮሞ በህግ አልተሰጠውም ። ብቸኛዋ ቁንፅል አንቀፅ 49 (5) አዲስአበባ በኦሮሚያ መሀል እንደሚገኝ ቢገልጽም በተጨማሪም ይኸው አገላለጽ የባለቤትነት ማረጋገጫ ፈፅሞ ሊሆን አይችልም ። በተጨማሪም አንቀፅ 49 ከንኡስ አንቀፅ 2-4) ያሉ የንኡሳን አንቀጾች የጥግግት ንባብ የሚነግረን አብይ ቁምነገር ኦሮሚያ በከተማው ላይ የበይ ተመልካችነ ምንም እንደማያገባው ነው።
በዚህም መሰረት አዲስአበባ ከታሪክ ሆነ ከህግ አንፃር የከተማዋ ነዋሪዎች እንጅ ፈፅሞ የኦሮሞ አይደለችም።

4~ ታዲያ ኦሮሞ ከታሪክም ሆነ ከህግ አንፃር ከሌላው ህዝብ የተለየ መብት ከሌለው ይሄ ሁሉ የመግለጫ ጋጋታ ለምን መጣ? የዚህ ምክንያት የኦሮሞ ፖለቲከኞች አልጠግብ ባይነትና የሌላው ህዝብ መለማመጥ የወለደው እብሪት ነው ። ባለፈው እንደገለፅኩት ከኦሮሞ ፖለቲከኞች አንፃር ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚከተለው አፒዝመንት ፖሊሲ ነው ።

ዊንስተን ቸርቺል ማባበል የሚባል ፖሊሲ እንደማያዋጣ በአንድ ወቅት እንደሚከተለው መግለፁን ፅፌ ነበር
<< An appeaser is someone who feeds a crocodile hoping it will eat him last. >> (የሚያባብል ፣ የማያስቆጣ ሰው ዐዞው ራሱን እስኪበላው ድረስ ጊዜ ለመግዛት ዐዞውን የሚቀልብ ሰው ማለት ነው) በማለት ነበር የገለፀው። አሁንም የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጨርሰው ህዝቡን እስኪውጡት ማባበል እጅግ አደገኛ ነው ።

5~ ኦሮሞ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ሙልጭ ያሉ አጭበርባሪዎች እንደሆኑ የታወቀ ነው። ፊኛቸው ጠባብ ነው ፣ጥጋብ አይችሉም።ንጥፈ ድኩማኖች ናቸው።ቅዤታቸው እንደማይሳካላቸው ስለሚያውቁ ስትራቴጂያቸው ሁሉ ስነልቡናዊጦርነት እና የፕሮፓጋንዳ ሽብር በማፋፋም ዛሬ ላይ ሆነው የህዝቡን የነገ ተስፋ በመስረቅ ላይ የተመሰረተ ነው(Plagirizing the future)ነው። ለስነልቡናዊና የፕሮፓጋንዳ ጦርነት መፍትሄው ደሞ ስነልቡናዊና ፕሮፓጋንዳዊ ጦርነት በእነሱ ላይም ማፋፋም ነው።

6~ በመሰረቱ ማንም ፓርቲ የፈለገውን መግለጫ ማውጣት ይችላል።
በዚህም መሰረት ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ዩሪ ጋጋሪ የሞስኮ ባንዲራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከለባትን ክብ ጨረቃ የኦሮሞ ናት ብሎ መግለጫ ማውጣት ይቻላል። ያን ቅዤት ግን ወደ ተግባር መለወጥ ፈፅሞ አይቻልም ።
እርግጥ ነው ልጓም ያልተበጀለት የኦሮሞ ፖለቲካ ክፉ መርዝ በቃልና ድስኩር ተጀምሮ ዛሬ የት እንደደረሰ እናውቀዋለን። የአንድነት ሀይሉም የነጠረ ርእዮት አለም ቀርፆ መታገል ሲገባው መገተሩን አብዝቶታል ። የአንድነት ሀይሉ መገተር ደሞ ፅንፈኛ የኦሮሞ ብሄርተኞች ሽቅብ እንዲሸኑ ምክንያት ሆኗል።

7~ ምን ይደረግ ? ለዚህ ጥያቄ መልስ ታዋቂው የአማራ አርበኛ ራስ አሞራው ውብነህ የተናገራት ወይራ የሆነች ንግግር ለአንድነት ሀይሉ ጥሩ ምክር ትመስለኛለች ።
ጣሊያን ኢትዮጵያን የወረረ ጊዜ የጎንደሩ ራስ አሞራው ሊማሊሞ ላይ መሽጎ ቁልቁል እየተንደረደረ ረፍት በመንሳት ብዙ የጣሊያን ወታደርን ፈጀበት ።
በዚህ ክፉኛ የተበሳጨው ግራዚያኒ ከሰማይ በአውሮፕላን ከመሬት በመድፍ ሊማሊሞ እንድደበደብ ትእዛዝ ይሰጥና በግራዚያኒ ትእዛዝ መሰረት ሊማሊሞን ከላይም ከታችም ሲወግሩት ያድራሉ።
በነጋታው የራስ አሞራው ወታደር ወደ ምሽግ ይገባና…
<<ጌታዩ! ጣሊያን ሊማሊሞን በመድፍ ሲደበድበው አደረ! >> ይለዋል።ራስ አሞራውም ሳቅ በማለት << ተወው ይበለው ፣ እሱም መገተሩን አብዝቶት ነበር ።>> አለው ይባላል።

አሁንም የአንድነት ሀይሉ ፣ አዲስአበቤውና ኢትዮጵየዊው ብሄርተኛ መገተሩን በማብዛቱ በኦሮሞ ብሄርተኛ የመግለጫ መድፍ እየተደበደበ ይገኛል። ይሄ ነገር ከዚህ በኋላ ግን ሊቆም ይገባል እላለሁኝ።