
በተለይም በአሁን ጊዜ የበለጠ በአማራውና ኦሮሞ መካከል ለማናቆር የማይቆፍሩት ጉድጏድ የለም:: አብን በንቃት መጠባበቅና መመከት ይኖርባችሗል::ወቅታዊ መረጃዎችን በመበተን ማምከን ትችላላችሁ:: በስማችሁ መግለጫዎች እንዳይወጡ መከላከልና መጠበቅ የአንድ ድርጅት ትልቅ ሀላፊነት ነው::ቤንሻንጉል በአማራ ላይ በዚህ ወቅት እንኳ የአማራ ጠል ሀይሎች የሚያቀናብሩት የዘር ፍጅትን የሚያይ ኢትዮጵያዊ የሞራል ልዕልና ኖሮት አማራ አይደራጅ ብሎ እይሞግትም:: በተለይም ከአማራ አብራክ የተፈጠረው የአማራ ልጅ ፈሪነቱን አመላካች እንጂ የሚጨምርው ቁምነገር የለም::አብን ከተቋቋመ ገና 3 ወራት ሆኖ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሳካችሁት እጅግ በጣም የሚደነቅ ነው:: አብን ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ የአማራን ህዝብ በመላው የሀገራችን ክልሎች ለማደራጀት በመንቀሳቀሱ ለትልቅ ስኬት እንደሚደርስ አልጠራጠርም:: ይህ እድገታችሁ ለአማራ መገፋትና መፈናቀል 27 አመታት ደንታ ያልሰጣቸው የፖለቲካ ደላሎች በእናንተ ላይ ቢዘምቱ የገቢያ ሽሚያ ስለሆነ እናንተ ከቆማችሁበት አላማ እንዳትዛነፉ::የተበደለ ህዝብ ማን ከማን ጋር እንደቆመ ለይቶ የሚያይበት ልዩ መነፅር አለው:: የአማራ ህዝብ ከናንተ ጋር ነው:: ከሁሉም በላይ አማራ ለድህንነቱ ለመደራጀት ሞግዚት አይፈልግም:: ህውሀት ሻቢያና ኦነግ አማራን ጨቋኝ እድርጎ ፍረጃ 40 አመታት አለፉ:: የቤንሻንጉል ጭፍጨፋም የዚህ ስራ ውጤት ነው:: እስካሁን የአማራን የብሄሮች ጭቆና ትርክት ስህተት መሆኑን በይፋ የገለፁት የሻቢያ ኤርትራ መንግስት የማስታወቂያ ሚንስትር አቶ የማነ ብቻ ናቸው:: ትልቁን የአማራ ህዝብ ያልሆነውን ነበር በማለት አማራ ጨቋኝ: አማራው የገዢ መደብ ነው:: አማራ ጠላታችን ነው በማለት ለፍፈናል ተከራክረናል:: ይህም በሙሉ ስህተት ነበር::ነፃ ከወጣንም በሗላ ይህንን ስህተት ማስተካከል ሲገባን አላደረግነውም::ይህም እንደገና ትልቅ ስህተት ሆኗል:: ስለዚህም ለተከበረው የአማራ ህዝብን በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እንጠይቃለን:: ፍቅር ያሸንፋል!!” ( አቶ የማነ ገብረአብ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቃል አቀባይ) የሰው ልጅ ስህተት የማይሰራ የለም ትልቅነት የሚለካው ስህተትን አምኖ የሚቀበል ነው:: ለዚህ ስህተት የህውሀት: ኦነግና ግንቦት 7 አመራሮች ግን ይቅርታን ገና ከአማራ ህዝብ አልጠየቁም::
ስለዚህ አብን
1. በሚቻለው ሁሉ ከአዴፓና ሌሎች የአማራ ድርጅቶች ጋር የጋራ ራእይ መቅረፅ
2. ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች በተለይም ለአማራ ህዝብ ጤናማ አመለካከት ካላቸው ጋር መቀራረብ ለምሳሌ በኦሮሚያ በአቶ ለማ መገርሳ በሚመራው ቲም ለማና በዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሚመራው ኢትዮጵያዊ መንግስት ለአማራ ክፉ ስለማያስቡ በእነሱ ላይ ጤናማ አመለካክት ማሰረፅ
3. ሆን ተብሎ የአማራው ህዝብ ቁጥር ከአማራ ክልል ውጪ እንዳይቆጠርና እንዳይታወቅ ሆኗል:: አብን ይህን እንዲከታተል::
4. ዛሬም የአማራ መከራ በሰፊው ይካሄዳል::ለምሳሌ በጎጃም መተከል በነበረው አስተዳደር በዛሬይቱ ቤንሻንጉል 22% ህዝብ አማራ ሆኖ ዛሬም በአማራ ጠላቶች ስውር እጅ ይፈናቀላል:: ይህ እንድይቀጥል አ ብ ን መታገል አለበት::
5. አማራ በማንነቱ የሚታፈርበት ታሪክ የለውም:: እፄ ምኒልክ የባርያን ንግድ ስያስቆሙ ዋናው የባርያ ንግድ ያስፋፉ የነበሩት ከታሪክ እንደምንረዳው የጂማው ንጉስ አባ ጅፋር ነበሩ:: እፄ ምኒልክም ሆነ ታላቁ አባጅፋራም ኢትዮጵያውያን ነበሩ:: በ1953 ዓ.ም ከታሪክ እንደምንረዳው የንጉሱን ፊውዳል መንግስት እውርደው ወደ ዲሞክራሲ ኢትዮጵያን ለማሸጋገር የሞከሩትና ህይወታቸውን ያጡት ጄኔራል መንግቱ ነዋይና ወንድማቸው ገርማሜና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየው በዚህ ዘመን የብሄር ፍረጃ አማሮች ሲሆኑ ይህን የለውጥ ህይል ያጨናገፉት ኦሮሞዎቹ ጄኔራል ታደሰ ብሩና ጄኔራል ጃገማ ኬሎ ናቸው:; ዛሬን አሻግረን ስንመለከት እነ ጄኔራል መንግስቱም ሆኑ ጄኔራል ታደሰ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ሊያድኗቸው የፈለጉት አፄ ሀይለስላሴም ( ተፈሪ መኮንን ጉዲሳ) ኢትዮጵያዊ ንጉስ በዘር ከተቆጠረ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነበሩ::ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አያና ህውሀትና ሻቢያ አማራ አድርጎ ቢቀርፀውም በዘሩ ኦሮሞ ነው ሆኖም ይህን ገዳይ ሰው አማራው የሚያየው በኦሮሞነቱ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ ነው:: የአማራ ጨቋኝነት ትርክት ውሀ አይቋጥርም::
6. አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ መሆኑ አማራን በጨቋኝነት አያስፈርጀውም ::ከ80 በላይ ቋንቋዎች በሚነገርባት ሀገር አንድ መግባቢያ ቋንቋ መኖሩ ላወቀበት ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ልዩ ፀጋ ነው:: በአፍሪካ የራሱን ፊደል ያለው ብቸኛ አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ መሆኑ ለአማራ ህዝብ የሚመሰግንበት እንጂ የሚፈረጅበት መሆን አይገባም ነበር:: አማርኛ ኢትዯጵኛ ሆኖ ቢሰየም ይገባዋል::
አማራ በአማራነቱ የሚያፍርበት ታሪክ የለውም:: በዐቢይ ዘመነ መንግስት አ ብ ን የትግሉን ስትራቴጂ ማስተካከል ያስፈልገዋል:: በአማራነት መደራጀት ትክክልና ፍትሀዊም ነው:: ሆኖም ዐቢይ በመላው የአማራህዝብ እጅግ ተአሚነት ስላለው ሆን ብሎ እንደወያኔ ዘመን እማራን ያገለለ ስርአት ይገነባል ብለን አንገምትም:: ይህም ሆኖ
አ ብ ን በመላው ኢትዮጵያ የሚኖረውን አማራ በማደራጀት ድምፁ ከፍ ብሎ እንዲሰማ ሊያድርግ ይችላል:: የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) በእጭር ጊዜ ከህውሀት አገልጋይነት እራሱን ነፃ በማውጣት ለአማራው ህዝብ እውነተኛው ወኪል መሆኑን ስላሳየ አ ብ ን ከአዴፓ ጋር ጤናማ ግኑኝነት ቢኖረው አዴፓ በአማራ አስተዳደራዊ ወሰን የአማራ ድምፅ አ ብ ን ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ተበትኖ የሚኖረውን የአማራ ህዝብ በማሰባሰብና በማደራጀትለመብቱ ይታገላል:: ከአማራ አስተዳደራዊ ወሰን ውጪ ያለው አማራ ቁጥር ስለማይታወቅ አ ብ ን መረጃ በመሰብሰብ ይህን ለህዝብ ማሳወቅ ይገባል:: ህውሀት ሆን ብሎ የአማራ ቁጥር እንዲቀንስ ወይንም በይፋ እንዳይወጣ ቢሰራ ላያስገርመን ይችላል:: ስለዚህ አ ብ ን ና እዴፓ በጋራ የአማራህዝብ ቁጥር መረጃ ለመላው ኢትዮጵያውያን ማሳወቅ ይግባቸዋል ::
በመጨረሻ የማሳስብህ አማራ መሪ በመሆንህ ብቻ ገና ብዙ መከራ ስለሚደርስብህ በከፍተኛ ትእግስተኛ ሆነህ ብቻ መገኘት ይኖርብሀል:: በመረጃ የተደገፈ ሀቅና ብዙ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ደጀን ከሗላህ ስላለ የሴራ ፖለቲከኞች በዚህ ዘመን የከሰሩ ይሆናሉ::
በኢትዮጵያ እስካሁን የተገነዘብነው የአማራ ህዝብ ጨቋኝ ተብሎ ሲዘመትበት በኢትዮጵያዊነት አፉ ተሸብቦ እንዲገዛ ከአማራም ውስጥ መሪ ሆኖ እንዳይወጣ ስውር የፖለቲካ እርግማን በሀገሪትዋ ያለ ይመስላል::ይህን አልፎ አ ብ ን ወቅቱን ጠብቆ የመጣ አሰባሳቢ ሀይል ነው::
በርቱ
ከሰላምታ ጋር