የማይሰራው ጨዋታ
የአዲስ አበባ ወጣቶችን በህገ ወጥ መንገድ በካምፕ አጉሮ በጀርመን በአዳራሽ ለማስጨብጨብ መሞከር የማይሰራ ጨዋታ ነው።
ከአለም አቀፍ የፍትህ ግብረሃይል
ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
ያሰሩዋቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች ባስቸኩዋይ ይፍቱ!!!
የአዲስ አበባ ወጣቶች ባስቸኳይ ይፈቱ!!!
ፍትህ ለአዲስ አበባ ወጣቶች !!!
ይህ የህግ ጥሰት ባስቸኳይ እንዲመረመር እንጠይቃለን!!!
ኮሚሽነር ዘይኑ በህግ ይጠየቅ!!!
ከጀርመን አገር ቃል በቃል የዘር ማጥፋት ጥሪ ለረዥም ጊዜ በተደጋጋሚ ያደረገችውን በአማራው ላይ የሚኒሊክ ሰፋሪ መጤ በማለት ከአዲስ አበባም ሆነ ከሌላው ቦታ ጥረጓቸው በሉዋቸው አሁንም በመቀጠል በቅርቡ በኪነጥበቡ ባለሞያ ቴዲ አፍሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ ግደሉት ብላ ጥሪ ያስተላለፈችውን በማህበራዊ መገናኛ ጂጂ ኪያ ብላ ራሷን የሰየመችው እጅጋየሁ የተባለች በጀርመን አገር የምትኖር ከመስከረም ወር ጀምሮ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በምታስተላልፈው ጥሪ ኦሮምኛ ተናጋሪ ባልሆኑ ማህበረሰብ አባላት ላይ የጀርመን ናዚዎች በይሁዳውያን ላይ ካደረጉት ባልተናነሰ ቃል በቃል ኢሰብአዊ ስድቦች እና ማንቛሸሾች ብሎም የዘር ማጥፋት ጥሪ የምታስተላልፈውን እጅጋየሁን በጉያ ይዞ የአዲስ አበባን ወጣቶች በወያኔ ያስመረረንን የጅምላ አፈሳ ከየቤታቸው እና ከመንገድ ላይ እንዲሁም መንግስት እውቅና ከሰጣቸው ንግድ ቤቶች እያፈኑ እያፈሱ ዘንዶ እባብ እና የወባ በሽታ ባለበት ካምፕ ውስጥ ከህግ ውጭ በሆነ መንገድ አጉሮ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው ማለት ራሱ ህገ ወጥነት ነው። በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እየሰበሰቡ ማጎር ለማሸማቀቅ እንጅ ለማስተማር አይደለም።
ወያኔ የሰራውን ስህተት አይድገሙ በግፍ ታሳሪዎቹን የአዲስ አበባ ወጣቶች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ
ባላደረጉት የአይደገምም የይቅርታ ቲሸርት ሳያስለብሱ አስገድደው ይቅርታ ሳያስጠይቁ ይፍቱ
አሁንም በድጋሚ
በህገወጥ መንገድ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በካምፕ በበሽታ እና ስለ በሰአብአዊ አሰራር እና አያያዝ ባልሰለጠኑ የጸጥታ ሃይሎች እያሰቃዩ ስልጠና እየወሰዱ ነው ብሎ ማለት ግፍን እና ህገወጥነትን ማንገስ ነው።
ስለ አፄ ኃይለ ስላሴ ክብር እና አወዳደቅ የተናገሩትን አይርሱ።
በአበባ ፋንታ ለአመታት ለወያኔ ስንቸረው የነበረውን የበሰበሰ እንቁላል እና የበሰበሰ ቲማምቲም
ለርሶም ለመቸር እንድንገደድ አያድርጉን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባጭሩ ጀርመን ላይ በጭብጨባ ፋንታ ጠንካራ ተቃውሞ እንደሚጠብቆት ይወቁት። የአዲስ አበባ ወጣቶችን ባስቸኳይ ይፍቱ!!!
የአለም አቀፍ የፍትግህ ግብረሃይል