አንቺ ኦሮሞ አትመስይም ይሉኛል ኦሮሞ ምን አይነት ነው? የምትለው የዛሬዋ እነ ጀዋርና ታከለ ኡማ የኦሮሞ ተወላጅን ብቻ የሆኑ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሰብስበው ስለዘረኝነትና ጥላቻ ቀስቃሽ ውይይት በአደረጉበት መድረክ ነው፡፡ ስሙት የዚህ ውይይት ዓላማው ምንድነው?
ልብ በሉ እነዚህ ወጣቶች ቢያንስ በአብዛኛው በአለፉት 27 ዓመት የተወለዱ ናቸው፡፡ እንግዲህ ለእነዚህ ወጣቶች በ”ቋንቋቸው” እንዳይናገሩ እንዳይማሩ ያደረጋቸው ማን ነው? አስተውሉ! ፊንፊኔን ብቻ ሳይሆን ሕዝባችንንም ተቀምተናል? ማን ነው የቀማቸው? ኧረ ለመሆኑ ምን እየተሰራ ነው? ተቀምተናል እያለ በዘረኝነትና ጥላቻ አእምሮው እየጠለሸ ያለ ትውልድ ስለሚናገርለት ማህበረሰብ ለማወቅ ባለመፈለግ ሌላን መሆን የመረጠ እንጂ ማንም የከለከለው የለም! ነፍጠኛ አገራችንን ባሕላችንን ምናችንን አጠፋ ምን አደረገ እያሉ ይሄው 50 ዓመት! በበቀልና ጥላቻ እየተመረዘ የሚሄድ ትውልድን እየኮተኮተ ያለ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ! ይህ ውይይት የተደረገው በኦኤም ኤን ቀራጭነት ነው ቢያንስ! ማን ነው የዚህን ውይይት የመራው?
ግልጽ እንነጋገር ከለማና አብይ ውጭ እስካሁን አንድም ሰው ፒዲኦ ብሎ ራሱን ከሰየመው ኦፒዲኦ ሌላውን በመጥላት ላይ በተመሠረተ የኦሮሞነት አበባዜ ነጻ ሆኖ ያገኘንው የለም! ሰሞኑን በአማራ ክልል የአብይን ፎቶ ማውረድ ተጀምሯል የሚል ሌላ የፌስቡክ ቅብብሎሽ አያለሁ! ከተጀመረስ ለምን? እርግጥ ነው ከኦሮሞ ይልቅ አማራን ጨምሮ ሌሎች በእነ አብይና ለማ ደስተኞች ናቸው! አሁን ነበሩ ወደሚለው እየተጓዙ ቢሆንም፡፡ አሁን ላይ ጥርጣሬው በአማራ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ማህበረሰብ እየጨመረ ነው፡፡ ለምን? በግልጽ እንምናየው የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት አራማጆች እንደፈለጋቸው እየፈነጩ ነው! ማንም እስካሁን በአብይ ላይ ተቃውሞ አላነሳም! ከኦሮሞ ውጭ! በበታችነት ስሜት ከመሠረቱ በጥላቻና ዘረኝነት ዓላማ ይዞ የተነሳ ፖለቲካ ለ50 ዓመት የተጠጋ እድሜ የዘራው ዘር ነው! እዬዬ ተበድያለሁ ይላል! መበደሌንም ሌሎችን በማጥፋት ነው ነጻ የምወጣው ብሎ ነው እንግዲህ የተነሳው! እስካሁን ብዙ ለማስታመም ተሞክሯል፡፡ አሁን ላይ የኦሮሞ ፖለቲካ ለሁሉ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ ኦሮም ጠቅላይ ሚኒሰቴር ሳይሆን እየተፈለገ ያለው ፍጹም ሌላውን የሚጠላ በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ በኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ የመረቀዘ አስተሳሰብ ያለው ነው እየተፈለገ ያለው፡፡ ባንዲራውም ዛፍ ከሌለበት ሊሆን አይችልም ይለናል፡፡ እንግዲህ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ በሚከተለው ሊንክ እንደምታዮት ነው ዓላማው! ከሚኒሊክ በፊት ሁሉም የየራሱ ባንዲራ ነበረው ይልሀል! የኢትዮጵያ ባንዲራ ኦዳ ሊኖርበት ይገባሀል ይላል፡፡ ለመሆኑ ኦዳ የምን ምልክት ነው! ሰውዬው እንግዲህ የሚያመልከውን ጥቁር አምላክ ምልክት ነው ሊያደርግልን የሚፈልገው! ጥቁር የአማላክ ምሳሌ ነው ይለናል፡፡ ከሱ ቀጥሎ የሚያወሩት ሶማሌ ናቸው አስተውሉ የሰውየውን ጥልቅ ንግግር፡፡ እሳቸው በጣም እያሳሰቡ የራሳቸውን የሰከነ ሀሳብ እየሰጡ ነው፡፡ አስተውሉ የሰውየው ንግግር ብዙ እንድናስተውል ነው የሚያስጠነቅቁት! ሰውየው ከእድሜያቸው ጋር የተስማሙ እውነቱን ይናገራሉ! ሐቅን እንፈልግ፣ ሐቅን እየቀበርን ነው! ውሸት እየነገሰች ነው ይሉናል! ሊንኩን ይመልከቱ፡፡
https://streamable.com/edit/ns6ch
ከዚህ በፊት የአሁኑ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙሰጠፋ ኡመር በኦኤምኤን በሚባለው የኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ማሰራጫ ሚዲያ ከኦሮሞ ጽንፈኞች ጋር ሲነጋገር ግልጽ የሆነ የአስተሳሰብ የበላይነቱን የሚያሳየውን ክርክር አጋርቻችሁ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግልጽ እየሆነልን የመጣው ነገር የኢትዮጵያ አደጋ የኦሮሞ የጥላቻና የዘረኝነት ፖለቲካ እንደሆነ ነው፡፡ ዛሬ የአማራ ዘረኞችን እየወለደልን ነው! በዚህ ከቀጠለ አብረን ላንኖር ነው፡፡ የኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ፖለቲካ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ ማውደም ነው! በጥላቻና ዘረኝነት በእምነትም በባህልም የማይመሳሰለው የዚሁ በሽታ ሰለባ የሆነ ኦሮሞ ሁሉ አንድ ነው! እስልምናም ሆን ክርስትና ከኢሬቻ ጋር አይገናኝም! አሁን እምነት ሁሉ ኢሬቻ እንዲሆን ዘመቻ ከፍተዋል! ገዳን ማንም አያከብርም ገዳን ዛሬ ድረስ እንዲደርስ ያደረጉት ሚኒሊክ ሆነው ሳለ ገዳን ሚኒሊክ አጠፋብን እያለ ያላዝንብሀል! እስኪ አሁንም የሚከተለውን ቪዲዮ ተመልከቱ! ገዳን ሚኒሊክ እንዴት ከመጥፋት እንደጠበቁት፡፡ እውነቱን ይሄ ነው! ቪዲዮውን ትንሽ ወደ ኋላ ጀምሬ ነው የቆረጥኩት በትግስት አድምጡት፡፡ ተናጋሪው የገዳ ስርዓት አጥኚ አስመሮም ለገሰ ናቸው ጠያቂው የፊንፊኔ ራዲዮ የተባለ ነው፡፡ ሊንኩን ይመልከቱ
አስተውሉ የኦሮሞ የጥላቻና የዘረኝነት የጥፋት ዘመቻ ምን እንደሆን ታሪክ ማውድም ሕዝብን እሴቶቹን በማውድም ምልክት የሌለው ማድረግ ነው! ዛሬ በሰፊው ዘመቻ ከፍተውብናል! በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልልቅ ድርሻ የነበራቸው የኦሮሞ አባቶች በፍጹም በዚህ በበታችነት ሥሜት የጥላቻና ዘረኝነት የተለከፈው ቡድን ሥማቻው አይነሳም፡፡ ኢትዮጵያ ግን ልጆቿን ታከብራለች! የኦሮሞ አባቶችን ጀግኖች ኢትዮጵያ ትዘክራለች፡፡ የኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ የበታችነት ስሜት የደቀቃቸው እነዚህን አባቶች የሚጠሉት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች ስለሆኑ ነው! አዝናለሁ! አብይንም የሚጠሉት የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጅ መሆኑ ነው!
እንግዲህ ሠላም ለአገራችን ከአልን ከዚህ በኋላ ለእነዚህ የሕዝብና አገር ጠላቶች ምንም አይነት እድል መስጠት አያስፈልግም፡፡ ከእነሱ ጋር በድርድር አይሆንም! የቡድኑ ዋና መሪዎች ኑሮአቸውን የመሠረቱት ሕዝብን ከሕዝብ በማጣላት ሕዝብን የንግድ እቃ በማድረግ ነው፡፡ እንግዲህ እላለሁ! ኦሮሞም ሁሉ ሊያስተውል ይገባል! ኦሮሞነት ከሌላው የተለየ አደልም! ምስራቅ አፍሪካን እንመራለን ይሉሀል! የኢትዮጵያዊውን አብይ ቃል ቀምተው! ኢትዮጵያ ሲሏቸው ግን ይደነብራሉ! እንዲህ በአለ ሥሜት ነው ሕዝቡን የሚያውኩት! ኦሮሞ ብዥታ ውስጥ ነው! ሊነቃ ይገባል! የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ቡድን አካሄድን የተመለከቱ ብዙዎች ሁኔታውን እየታዘቡ ነው፡፡ በዚሁ ምክነያት የአብይ አስተዳደርም ጥርጣሬ ውስጥ እየገባ ነው! በግልጽ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጣሉ አስተሳሰቦችን እያስፋፋ ያለው የኦሮሞ አክራሪ ቡድን በየቦታው ሴራውን እንዲነዛ የአብይ አስተዳደር እድል ሰጥቶታል ብቻም ሳይሆን በመንግስት ገንዘብ እየታገዘ በመንግስት መዋቅር በአሉ ትልልቅ ባለስልጣናት እየተደገፈ ነው፡፡ ለአብይና ለማ ብዙ እምነትና ዜማም ተዜሟል! ሕዝብ ያየው የአስተሳሰብ ደህንነታቸውን እንጂ ዘራቸውን አደልም! የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄ ነው! ሆኖም ግን አሁን ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፍተኛ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ እያደረገው ያሉ ነገሮች እየበዙ ነው! የአዲስ አበባ ከንቲባ የተባለው ሰውዬ የአዲስ አበባ ኦሮሞ ወጣቶችን ብቻ ከላይ ያያችሁትን አይነት ዘረኝነት አልሰበከም የጠላት ወሬ ነው ይሉናል፡፡ ግለሰቡን እኮ በግልጽ የኦነግ አቀባበል የተደረገ እለት ሰምተንዋል! በአደባባይ የሰማንውንም ሊክዱን ይችላሉ! ታዬ ደንደዓ የኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ቡድን እንዳይነቀፍ በመንግስት መዋቅር ዋና ጠበቃ ሆኗል! አዝናለሁ! ውስጡ የተቀበረው የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ ሊቆጣጠረው አልቻለም! እንደ እውነቱ ይህ አስተሳሰብ ከቤተሰብ የመጣ እንዳይመስላችሁ! የአስተሳሰቡ ዋና ትምህርት ቤት የከፍተኛ ትምርት ተቋማት ናቸው! በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ያለፈ ኦሮሞ ከዚህ አስተሳሰብ ነጻ የሆነ ምን ያህል እንዳለ አላውቅም! ግን ይህ የጥላቻና ዘረኝነት አስተሳሰብ ከሁሉም ይልቅ በከፍተኛ ተቋም ያለፈውን አጥቅቶታል፡፡ ማወቅ ስለቻለ እንዳይመስላችሁ! እውነታው እንደ እምነት አንዲቀበለው ስለተመረዘ ነው! ኢንዶክትሪኔትድ!
አብይ ለማ ሆይ የፈጠራችሁት አገራዊ መግባባት በፍጥነት እየተሸረሸረ እንደሆነ አስተውሉ! ኦሮሞን ለማሳመን ኢትዮጵያን መጥላት የሆነ እስኪመስል ነው ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ ነን የሚለው የአብይ ንግግር ኦሮሞን ያስደነበረው! ወደነበርንበት የኢትዮጵያዊነት ማንነት እንመለሳለን የሚለው የአብይ ንግግር እብድ ነው ያደረጋቸው!
ልዑል አግዝአብሔር ኢትጵያንና ሕዝቧን ከክፉዎች ይጠብቅ! ሠላምና ፍቅርን ይስጥ! አሜን!
ሰርፀ ደስታ