የሆነውስ ሆነና ዐቢይ ትናንትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተብየው ላይ ሊገሉኝ ቤተመንግሥት ድረስ ሠራዊት ልከው የነበሩ ሰዎች ሴራቸው ከሽፎ ሊገሉኝ ባለመቻላቸው ተናደዋል ተበሳጭተዋል!” ያሏቸውን 240 የአግአዚ ሠራዊት ልከው ሊገሏቸው የሞከሩትን የወያኔ ወንጀለኛ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል ወይ???

መቸም የላኳቸው እነሱ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ወይም በቂ መረጃ ሳይኖራቸው እንደዚህ የዓለምአቀፍ የዜና አውታሮች ሳይቀር እየተቀባበሉ ያራገቡትን ክስ በማንሣት አይወነጅሏቸውም ብየ ነው፡፡ መረጃው ካላቸው ደግሞ በቁጥጥር ስር ማዋል አለባቸው፡፡ ጥያቄው እነኝህን ሊያስገድሏቸው የነበሩ ወንጀለኞች ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር አዋሏቸው ወይ ነው ጥያቄው??? ካላዋሏቸው ደግሞ ለምን??? እነኝህ ወንጀለኞች ማንነታቸው ሳይገለጥ ዘለዓለም በሽፍንፍን የሚገለጸውና ማንነታቸው በይፋ ለሕዝብ የማይገለጸውስ ለምንድን ነው???

ተዋናይ ዐቢይ እንዲህ ብለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተራገበ ክስ ካሰሙ በኋላ ዞር ብለው ደግሞ እዚያው ላይ ምን አሉ መሰላቹህ አነሣሥተው ካመጧቸው ከአንድ አምስቱ በስተቀር የተቀሩቱ ደሞዝ የሚጨመርላቸው መስሏቸው የመጡ ናቸው!” ይሉናል፡፡ ከአምስቱ በስተቀር የተቀሩት የመጡት ደሞዝ ይጨመርልን?” የሚል አቤቱታ ለማቅረብ ከሆነ የመጡትና የመንግሥት ግልበጣ የማድረግ ዝግጅትና ዓላማ ይዘው ካልመጡ እንዴት ሆኖ ነው ታዲያ እርስዎ የሚሉን እኔን ገለው ለውጡን ለማጨናገፍ ነበር የመጡት!” የሚለው ክስዎት እውነት ሊሆን የሚችለው ተዋናይ ዐቢይ??? እርስዎ እራስዎ መልሰው አፈረሱት እኮ???

በዚህ ቀሽም ወሬዎት ምድረ ነፈዝ ደጋፊዎት ይጃጃል እንጅ እኔን አምሳሉን በዚህ ሐሰትነቱ እዚያው ላይ በሚታወቀው ግልብና ቀሽም ወሬዎት አይደለም በምንም ሊያታልሉኝ ሊሸውዱኝ አይችሉም እሽ ተዋናዩ፣ ውሸታሙ፣ አስመሳዩ፣ ነውረኛው ጠቅላይ ሚንስትር???

ዐቢይን ምን ትሉልኝ መሰላቹህ ዐቢይሻ እባክሽን አሁን ተባኖብሻል የሕዝብን አንጀት ለመብላት ፈንጅ እያስፈነዳሽና የታጠቀ ሠራዊት ቤተመንግሥት ድረስ እያስመጣሽ የለውጥ አደናቃፊዎች እኔን ገለው ለውጡን ሊቀለብሱ!” ምንትስ ቅብርጥስ የምትይው የማጃጃያ ፈሊጥሽ ተባኖበታልና ደሞ ሌላ አዲስ የማጭበርበሪያ የማወናበጃ ፈሊጥ ፈልጊ በሉልኝ እባካቹህ???

ሕዝብ ከጎኔ ካልቆመ ሥልጣን እለቃለሁ!” የሚለው አባባልሽም ሕዝብ ማንነትሽን አውቆታልና የሚሠራልሽ እንዳይመስልሽ ወይ ደግሞ ያንች የማጃጃያ የማታለያ ካርድነት ተበልቶበት አልቆ ከሆነና ዞር ተደርገሽ ደሞ ሌላ ጠ/ሚ ሊሾም ከሆነም ግልጹን ንገሪን በሉልኝ እስኪ???

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com