ባለፈው ሳምንት ለደመወዝና ለጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ-መንግሥት የሄዱት ወታደሮች “የለውጥ ሂደቱን የማደናቀፍ ዓላማ ባላቸው አካላት የተላኩ ነበሩ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልፀዋል።
የወታደሮቹ ሐሳብ ክፋት ይኑርበት አይኑረው ስላልታወቀም ብልሹ ሁኔታ ሳይፈጠር ሁኔታው በዘዴ መፈታቱን ተናግረዋል።
ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ካቢኔ ድረስ ያለው የተቋም ብቃት አነስተኛ መሆኑን በዛሬው ንግግራቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ “ችግር የፈጠረን ጭንቅላት – ችግር ፈቺ ማድረግ ቀላል አይደለም” ብለዋል።