ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው
ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን አቅም የሚያጎለብት ስልጠና በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተሰጠ ነው፡፡
አመራሩ ለውጡን ለማስቀጠል የማያቋርጥ የመማርና የማድረግ ሂደት ውስጥ መግባት እንዳለበት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስልጠናውን ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡
አመራሩ ለሚመራው ሰራተኛ፣ ህዝብ ምሳሌ መሆን እንዳለበት:- ሰዓት በማክበር: በትጋት በመስራት: ውጤታማ በመሆን እንዲሁም በሌሎች ህዝቡን በሚጠቅሙ መልካም ተግባራት ምሳሌ ሆኖ ማሳየት እንዳለበትም ጠ/ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡
እያንዳንዱ ሚኒስትር የመጀመሪያ 100 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ፈጣንና የህዝቡን ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ ለማምጣት እንዲረባረብም ዶ/ር ዐቢይ አሳስበዋል::
ስልጠናው ቁልፍ በሆኑ ርዕሶች: በተመረጡ የዘርፉ ምሁራን በመካሄድ ላይ ይገኛል::
ስልጠናው ለ2 ቀናት እንደሚቀጥል ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ልዮ ሀላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡