ዳኛ ፍሬሕይወት ሳሙኤል

የትላንቱን የዶ/ር አቢይን የፓርላማ ውሎ በጥሞና ተከታትዬ እነደተረዳሁት በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ ለተፈመው እስራት የተሰጠው መልስ አስደንግጦኛል፡፡ ወጣቶቹ ሣይፈረድባቸው ተራሚ ተብለው የቅጣት እርምት ጨርሰው አብዘኛቹ ወጥተዋል እየተባለ ነው፡፡ ሰው ሳይፈረድበት ታራሚ ይሆናል እንዴ? ማን ማንን ለማረም ከየት ስልጣን አገኘ? (ፖሊሶቹ እኮ ፍርድ ቤት እየሄድን ጊዜ አነጠፋም እያሉ ነው)፡፡ ወጣቶቹ ህግ ጥሰዋል አልጣሱም እያልኩ አየደለም፡፡ መጠስ አለመጣሳቸው በፍርድ ቤት መረጋገጥ አለበት፡፡ መንግስት ግን በጠራራ ፀሃይ ህግ ጥሷል፡፡ ያለፍርድ ቤት ሰዎች የሚያዙበት ሁኔታ እንዳለ አወቃለሁ፡፡ ግን የለፍርድ ግን ታረሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ኢህገመንግሰታዊ ስለሆነ መቆም አለበት፡፡ በለውጥ ማሳበብ አንችልም፡፡ ኢህአዴግ እንደመንግሰት ሰዎችን አፍሶ በመሰለው እያረምኩ ነኝ ማለት ማቆሚያው የቱ ጋ ነው ? በዚህ አይነት አገርቱን ለዝህ ውድቀትና የመበታተን አደጋ የጋራደው አብዘኛው የህዋሀት/ኢህአዴግ አመራር በሃገርቱ በሁሉም ክልሎች ለገደላቸውና ላስገደላቸው ቢሎም ለዘረፈው ሀብት (የልጅ ልጆቻችን ከፍለው የማይጨርሱት የህል ዕዳ አሳቅፎን ሲየበቃ)የለፍርድ እነዲታሰር እኮ አልጠየቅንም…… ከደሞዛቸው በላይ ሀብት አካብተው ያሚታዩ ባለስልጣናትን የለፍርርድ ቤት ይወረሱ አላልንም…… ለምን ቢባል ህገወጥነትን በህገወጥነት መግታት ማቆሚያና መቋጠሪያ ስለሌለው ፡፡ ዜጎችን ከማረሚያ ቤት አልፎ ቢሮና በግል ቤት ሲየስሩና ሲያሳሲሩ፤ ሲያኮለሹ፤ አካል ሲቆርጡ የነበሩ የኢህዴግ ባለስልጣናት መቼ ተከሰሱ መቼስ ታረሙና ነው …… ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊሲ የስራ ሀላፊ LTV

WORLD https://www.youtube.com/watch?v=ecvijAhDs5Q&feature=share ጋር ባደረጉት ውይይት ያሉዋቸው ነገሮች የሳስበናል፡፡ ከወጣቶቹ ጀርባ ሌላ ሀይል አለ ይላሉ፡፡ ይህ ከጀርባ ሆነው እንደ የመን/ሶሪያ ሊያደርጉ የሚለው ማንን ነው? ……. ምንም ጀርባና ፊት የለውም ፡፡ ማስረጃ ካለ መናገር ነው፡፡ “ከጀርባ የነበሩት” የት ሄዱ? ”ከፊት የሉት” ምስክኖች ተይዘው…… በእንድህ አይነት ”ከጀርባ ያለ” ”ከፊት ያለ” በሚባል ቅኔ ሰዎች ሲታሰሩ በማየታችን ያሳዝናለሁ፡፡ ከውጭ የገቡቱ እያመሱን ከሆነ በግልጽ በማስረጃ መያዝና ለህግ ማቅረብ፤ ከዚያ ውጭ ዜጎች በመላምትና በግምት እነእከሌ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል በጥርጣሬ ሰላማቸውን ማጣት የለባቸውም፡፡ መንግስት ሀሜት የሚያስፋፋ መሆን የለበትም፡፡ ወይ ግልፅ ማድረግ ወይ አለመናገር፡፡ አሁን ባለው የለውጥ ህደት መንግስት አውቆት ነው ያደረግነው ሲል ምን ማለቱ ነው? (27 MINUTE:14 SECOND ቀጥሎ)፡፡ የሚናምነው ሰው (ዎች) እንጂ የምናምነው ተቋም በሌለበት ሁኔታ ሁኔታዎች ከዚህም እንዳይከፉ ይስፈራል፡፡

አሁን ወጣቶቹ ደዴሳ ታሰሩ ይባላል፡፡ ደዴሳ የሚባል ቦታ እኮ በ1997 ቀንደኛ የቅንጅት አስታባባር የነበሩት ተብለው ወጣቶች ተገርፈዋል ከፍሎቹ ደግሞ ማታ ከእስር ቤት ተወስደው አልተመለሱም፡፡ አሁን ደግሞ ይህ እየተደገመ ያለው በለውጡ ጊዜ መሆኑ ያሳስበናል፡፡ የሆነ ሆኖ ለውጡ ያሳሳኛል ፤ማንም በአብይና በለማ የለውጥ ጥረት ላይ ባይመጣብኝ ያሰኘኛል፡፡ ብርቱ ደጋፊያቸው ነኝ፡፡ የለውጡን ሐይል መርዳት በሚቻልበት ሁሉ ለመርዳት በግልም ሆነ ከሌሎች ጋር በጋራ ከምጥሩት መሃል መሆኔ እነደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን በለውጡ ስም ተከልለው ድሮ ህወሃት/ኢህአዴግን ከነካችሁ፤ለመንካት ካሰባችሁ ፤ከገላመጣችሁ ‹‹ሀገር ይፈርሳል ዝም በሉ›› ሲባል እንደነበረው አይነት ለዉጡ እዝህ እንድንደርስ ስለታሰሩትና ሰለሞቱት ስለቆሰሉት በጨዋ ደንብ ተነጋግሮ ፍትህ መስጠቱ ወደኃላ ይጎትተናል፤ ስለሞቱት ስለታሰሩት መናገር ለውጡን ለሚያደናቅፉት ቤንዚን ማቀበል ነው የሚሉት ወገኖች ጠቃሚ አይመስሉኝም ….. ህሽ….ኡሽ… ዝምበሉ ከተናገራችሁ ለዉጡን ወደ ኋለ ይመልሳል እየተባልን ለውጡ እነዳይቀለበስብን ሰግተን በመንግስት ህግ ሲጣስ እያየን ዝም ማለት የሞራል ክሳራ ከመሆን አያልፍም ( በለውጡ ስም ተከልለው ተጠያቂነትን ለማምለጥ የምጥሩ የሚናውቀቸው ወንጀለኞች ዝም እንድንል ስመክሩን ደግሞ የበለጠ ያሰዝናል)፡፡ ሆኖም ግን ስነስርኣታዊና የአፈጻጸም ጉለቶች ላይ መንጠልጠል ከትልቁ የለዉጥ ጉዞ እንደሚጎትት ቢገባኝም የሰዎችን መሰረታው መብት የሚያሳጣ አሰራሪ መሰረታዊ ሲለሆነ ዝም ሊባል አይገባም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የአሁኖቹ ተሳሪዎችም ሆኑ የበፊቶቹ የደደዴሳ እስረኞች ፍትህ ይገባቸዋል፡፡ ይህችን ቃል ለፍትህ መናገራችን ለውጡን ወደኋላ ይጎትተው ይሁን? ይጎትተናል ከተባለ ከሰው ተፈጥሮ ውጭ ሁሉን ረስተን ወደፊት የሚታሰሩቱ ብቻ ፍትህ ይሰጣቸው አንበል ነገር፡፡ በዝህ አጋጣሚ በ1997 ዓ.ም. በእንደዝህ አይነት ሰበሰብና የፖለቲካ ሽፈን ከአዲስ አበባ ብቻ ከ50 000 (ሀምሳ ሺህ) በላይ ወጣቶች ተስረው ተገርፈው ተገድለው ሲያበቁ ባንክ ሊዘርፉ ነበር…. መሳሪያ ይዘው ነበር….. ወዘተ የሚል የውሸት ሪፖርት ተዘጋጅቶ ፓርላማ የቀረበበትን ሁኔታ መንግስት ስህተቱን ተቀብሎ ሪፖርቱን በእውነተኛው ሪፖርት እንድተካ እየጠየቅን መሆኑን ሳሳውቃችሁ መንግስት ከበፊቱ ውድቀቱ ተምሮ ወደፊት እነድህ አይነት ዜጎችን እያፈሱ ማሰርና ማሰቃየት እነዳይደገም በማድረግ ለውጡን ምሉእ እንዲያደርግ ለማገዝ ከመሆኑም በላይ ፍትህ ለሚገባው ፍትህ ለመስጠት ሞራል የሚጎለው የለዉጥ ሀይል አለመሆኑን መሪዎቹ እንዲየረጋግጡ እድል ለመሰጠትም ጭመር ነው፡፡

ፍሬህይወት ሳሙኤል