ለአራት ዓይናዋ ፖለቲካኛ ለብርቱካን ሚደቅሳና ለጋዜጠኛ ቤተልሄም ታፈሰ መታወሻ ትሁን!!!
{1} የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ተመዝጋቢዎች 7 ዓመታት ጠብቀው፣ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2005 ዓ/ም ይፋ ባደረገው አራት የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች የ10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ አንድ ሚሊየን ነዋሪዎች ተመዝግበው ባንክ እየከፈሉ 7 አመታት አስቆጥረዋል፡፡ በ1996 ዓ/ም በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ እስከ 2010ዓ/ም ድረስ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ 175 ሽህ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ የ40/60 ቤቶች ጨምሮ ከ132 ሽህ በላይ ቤቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡ የ40/60 የመኖሪያ ቤት ፕሮግራም 164000 (መቶ ስልሳ አራት ሽህ ሰዎች ተመዝግበው 37000 (ሠላሳ ሰባት ሽህ) ከተመዝጋቢዎቹ 23 በመቶ፣ ዜጎች ተስፋ በመቁረጥ ውላቸውን አቆርጠዋል፣ በቀጣይነት ለ40000 (አርባ ሽህ ሰዎች)ቤት ለመስጠት እቅድ እንዳለ ጥቅምት 9 ቀን 2011 ዓ/ም በቴሌቪዥን ገልፀዋል፡፡ ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሦስትና አራት አመት ሠርተው እናስረክባለን ብለው የህዝብ ገንዘብ ሰብስበው በተግባር ቤቶቹን ሠርተው ባለማስረከባቸው ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡ በሃገሪቱ ህዝብ የገንዘብ ቁጠባ ባህልን ያጠፋት ሁለቱ ድርጅቶች ሥራቸውን በአግባቡ ስላልተወጡ ለህግ መቅረብና በሌሎች ብቃት ያላቸው ሙያተኞች መተካት ይኖርባቸዋል፡፡ ቤት ሰሪው ህብረተሰብም ለ7 ዓመታት በቤት ኪራይ እየተሰቃየ፣ ለተጨማሪ የቤት መሥሪያ ወጪ የዋጋ ግሽበት ተጠያቂ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ለፍርድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ባንኮች በየአመቱ ከ10 እስከ 14 ቢሊዮን ብር አተረፍን እያሉ የሚተርኩት የደሃውን ህብረተሰብ ተቀማጭ ገንዘብ እያበደሩ ባገኙት ትርፍ መሆኑ ይታወቃል ስለዚህ በህግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ካገኙት ትርፍ የእነዚህን ደሃ ህብረተሰብ ቤቶች መስሪያ የዋጋ ግሽበት ተጨማሪ መክፈል ይገባቸዋል፡፡ የዲያስፖራ ወገኖች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያዘጋጀውን‹የዲያስፖራ የሞርጌጅ ብድር አካውንት›በህግ ተዋውላችሁ፣ መብታችሁን አስከብራችሁ በሃገራችሁ ውስጥ ቤት ሠርቶ የመኖር ነፃነታችሁን ማስጠበቅና ሃገራችሁን መርዳት ይጠበቅባችሆል፡፡ ዲያስፖራዉ ወገናችን ቤት ለመገንባት ብለው በተለያዩ ሪል እስቴት ዲቨሎፕርስ ገንዘባቸውን ተዘርፈዋል ከጃክሮስ ኢትዮጵያ እስከ ካንትሪ ክለብ ከውል ውጪ የአምስት መቶ ሽህ ብር ጭማሪ እየተደረገባቸው ቤታቸውን አጥተዋል፣ በአክስስ ሪል ስቴት ገንዘባቸውን ያጡ ዜጎች ሊመለስላቸው ይገባል እንላለን፡፡
{2} የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን፤-የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከ18 በላይ ዞኖች ሲኖሩት የተወሰኑ ልዩ ዞኖችን በውስጡ ያካትታል፡፡ ከአዲስ አባባ ኩታ ገጠም የሆኑ የኦሮሚያ ግዛቶች በልዩ ዞንነት በ2008 ዓ/ም ተጠቃለሉ፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች 497,846 ሄክታር መሬት ያጠቃልላል፡፡ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ስድስት ወረዳዎች ማለትም አቃቂ፣ ባራክ፣ ሙሎ፣ ሱሉልታ፣ ሰበታ-ሃዋስ፣ እና ዋልመራ ያጠቃልላል፡፡ እንዲሁም ስምንት የገጠር ከተማ ማዘጋጃ ከተሞችን ማለትም ሰንዳፋ፣ ለጋጣፎ፣ ላገዳዲ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ፣ ዱከም፣ገላን፣እና ሰበታን ያካትታል፡፡ የአዲስአበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ስም ገበሬዎች መሬታቸውን በሪል ስቴት ልማት አልሚዎች ስም ከመሬታቸው ተነቅላዋል፡፡ የአንዱ ጥቃት የሁሉም ጥቃት ነው፡፡ ከዘርና ከማንነት ጥያቄ በላይ ስብዓዊነትና ለፍትህ ዘብ እንቁም፣ በአዲስ አባባ ኩታ ገጠም የተፈናቀሉ የኦሮሞ ገበሬዎች አዲስ አበባ ወጣቶች ድምፃቸውን ያሰሙ፡፡ በአዲስ አበባ ወጣቶች ያለፍርድ እስራት ነግ በኔ ስለሆነ የኦሮሞ ወጣቶችም ድምፃቸውን ያሰሙ እንላለን፡፡ፍቅርና ስብዓዊነት ያሸንፋል፡፡
የሪል ስቴት ባለኃብቶች፣አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ኃላፊዎችና ፊዴራል መንግስት ሹማምት መሬታቸውን በግፍ ለተነጠቁ ገበሬዎች ቤት ሠርቶ የመስጠትና የደሃውን እንባ ማበስ ማህበራዊ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባም እነዚህን የሪል ስቴት ልማት ሃገር በቀልና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች በተግባር ተፈናቃቹን እንዲረዱ ውይይት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ የሪል ስቴት ዲቨሎፕሮቹ የሃብት ምንጭ የገበሬዎቹ የተነጠቀው መሬት በመሆኑ የግሉ ዘርፍና መንግሥት ሊክሳቸው ይገባል፡፡
“Social responsibility is an ethical framework and suggests that an entity, be it an organization or individual, has an obligation to act for the benefit of society at large. Social responsibility is a duty every individual has to perform so as to maintain a balance between the economy and the ecosystems.”
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት በሪል ስቴት ልማት ስም የተላለፈላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዝርዝር (በ2002 የተደረገ ጥናት)
336,296 ሚሊዩን እስከ 57,679 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ (1) አያት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ የቦታው ስፋት 1,336,296 በካ.ሜ (2) ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ፣ የቦታው ስፋት 262,868 ካ.ሜ (3) ካራ ቆሬ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ የቦታው ስፋት 255,046 ካ.ሜ (4) ጊፍት ትሬዲንግ ሪ/ኃ/የተ/የግ/ማ ፣የቦታው ስፋት 162,997 ካ.ሜ (5) ሳትኮን ኮንስትራክሽን፣ የቦታው ስፋት 104,100 ካ.ሜ (6) ተ/ብርሃን አምባዬ ሪል እስቴት፣ የቦታው ስፋት 100,000በካ.ሜ (7) ዮሴፍ ተገኝ፣ የቦታው ስፋት 71,996 ካ.ሜ (8) Getty / ኖርዝ ጌት /LTD/፣ የቦታው ስፋት 68,700 ካ.ሜ (9) ቫርኔሮ፣ የቦታው ስፋት 67,500 ካ.ሜ (10) ሙሉነሽ ፍጥረት፣ የቦታው ስፋት 66,763 ካ.ሜ (11) ጌታቸው ወልዴ ሪል እስቴት፣ የቦታው ስፋት 57,679 ካ.ሜ
50,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን፣ ኤስ ኤን ቢ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ጋድ ኮንስትራክሽን፣ ጂ.ኤች ሲሚክስ፣ ከአጆ ኢንተርናሽናል፣ ኖብል ሪል እስቴት፣ አደይ አበባ ሪል እስቴት፣ ገ/ሚካኤል ማርቆስ፣ ፔትራም ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮቴክ ኮንስትራክሽን፣ ቢኒያም ጥላሁን /ማርብስ/፣ ካንትሪ ክለብ ደቤሎኘመንት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ያንኮማንድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ስታር ቢዝነስ ግሩኘ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፈሪስት ሪል እስቴት፣ እንይ ደነሪል ቢዝነስ፣ አካካስ ሪል እስቴት፣ አድሮም ጀኔራል ትሬዲንግ፣ ሉና ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ማጅኮን ጠ/ስ/ተቋራጭ፣ ደግነት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፖስራክሲንክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ
49,610-40,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ጋራድ ኃ/የተ/የግ/ማ፣በርታ ኮንስትራክሽን፣ጌት አስ ኢንተርናሽናል፣ ኃይሌና አለም ሪል እስቴት፣ አምባሳደር ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዶ/ር ቻርልስ ናቸው፡፡
39,216-30,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ብርሃን ጐህ/ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ኤን ኤም ቢ፣ አምድይሁን ጠቅላላ ንግድ፣ ጋን ችንግ ሪል እስቴት፣ አሴ ትሬዲንግ፣ ስርደንጂ ሃውሲንግ ፣ፓን አፍሪካ ሪል እስቴት ፣አሴ ትሬዲንግ ፣አሴር ሪል እስቴት ፣ተፈሪ ይርጋ፣ሮማናት ሪል እስቴት ፣ብስራት ፀጋ ሪል እስቴት ፣መሐመድ ሰብደን ፣ኢኬር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ደ.ኤምሴ ፣ኮሜቶ ትሬዲንግ ፣ይርጋ ሀይሌና ቤተሰብ ኃ/የተ/የግ/ማ ፣ካስትል ሪል እስቴት ፣ካንጋሮ ኘላስት ሪል እስቴት ናቸው፡፡
25,000-20,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ኒው ሆኘ ሪል እስቴት፣ ሰሙ ተክሌ፣ ሆም ስዊት ሆም ፣ሾላ አክስዮን ማህበር፣ ናሰው ሪል እስቴት፣ ፊባ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ሆስኢ ትሬዲንግ፣ ሚካኤል ቤቶች አካባቢ ማ፣ ካስማ ኢንጂነሪግ፣ ማረፊያ ሪል እስቴት፣ ክንድያ ሀጐስ ሪል አስቴት፣ ዜደ.ኤም፣ ሮማናት ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ
19,800-10,000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ሁሴን ሲራጅ ሪለ እስቴት፣ ቶኘ ላንድ ሪል እስቴት፣ ሲሳይ ደስታ፣ አል አድ አሳ ሪል አስቴት፣ ሀውስ ዊዝደም ሪ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ አቤንኮ ሪል እስቴት፣ ማይተባይ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዮሐንስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ፊሊክስ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ጉላጉል ትሬዲንግ ኃ/የት/የግ/ማ፣ ላዋራ ንግድና ኢንዱስትሪ፣ ወ/ሮ ይርጋለም አሰፋው፣ ስብሃቱና ልጆቹ፣ አዜብ ሃይሉ፣ ፍቃዱና ጓደኞቹ ሪለ እስቴት /የተ/የግ/ማ፣ ራጉኤል የቤቶች ግንባታ አ/ማ፣ ሰንሴት ሆምስ ሪል እስቴት፣ ቶፊቅ ሻሽ፣ አበው ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ዋይድ ኢንጂነሪንግ፣ ፍሬው ብርሃኔ ሪል እስቴት፣ መሠረት በትዛዙ ሪል እስቴት፣ መሃመድ አሊ ሪል ስቴት፣ ሉሲ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ወ/ሮ አልጋነሽ ሃይሉ ሪል እስቴት
6,940-1,072 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት የተረከቡ ሪል ስቴትስ አልሚዎች፣ ኤልያስ አባሚልኪ ፣ኤልያስ መሃመድ እና ኢብራሂም መሃመድ፣እስክንድር ካሳ፣አምሳለ ጌታቸው ፣ጀኖሪል አስቴት ፣ማይክሮ ጠ/ሥራ ተቋራጭ ፣ማደክ ካርጌት ኃ/የተ/የግ/ማ ፣ሜይ ሪል እስቴት፣አዱኛ እጅጉ፣ሳሙኤል አለማየሁ፣አቶ ሰለሞን ወርቁ፣ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ ፣ማቲያስ ኃ/የተ/የግ/ማ ፣አንቶኒዩ ካርናቪያክ ፣ኢምፓየር ሪል እስቴት፣ፋሪይም ኃየተ/የግ/ማ፣አቶ አስራት መኮንን አለም፣ ረዘነ ተፈራ፣ መልካም ራዕይ ሪል እስቴት፣ አበራ ቶላ፣ መክሊት ሪል እስቴት ናቸው፡፡ ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን ብትወጡ አዲሱን የዶክተር አብይ አህመድን መንግሥት የመደመርና በፍቅር አብሮ የመኖር ዘለቄታዊ ለውጥ በመደገፍ የኢኮኖሚ ብልፅግና ድህነት የመቅረፍ ቀጣይነት ያለው ራዕይ ተፈፃሚ ይሆናል እንላለን፡፡ ማህበራዊ ፍትህ በራስ ተነሳሽነት በማስፈን በባለኃብቱና በህዝቡ ውስጥ የተፈጠረውን የቂም በቀል በማጥፍት ቀጣዩ ትውልድ በፍቅር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ የመሬት ቅርምቱንና የሃብት ክፍፍሉን በመቃወም፣ ብዙ የድሃ ልጆች በህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ወድቀው የገማውን ኢፍትሃዊ አስተዳደር መንግለው የዛሬውን ለውጥ አስረክበውናል፡፡ የሞች ቤተሰቦች እንባቸው እንዲደርቅ፣ ለጦሪ ልጆቻቸው የደም ካሣ የሪል ስቴት ባለሃብቶችና መንግሥት ሊያደርግ ይገባል እንላለን፡፡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የኢትዮጵያ ወጣቶች በሰከነና በሰለጠነ የጠረጵዛ ዙሪያ የፖለቲካ ውይይት ችግራችሁን መፋታት ተማሩ፣ ፍቅራችሁ ይጠንክር!!! የነገ ተተኪ ትውልድ ወራሾች ናችሁና፡፡ “Social responsibility is an ethical framework and suggests that an entity, be it an organization or individual, has an obligation to act for the benefit of society at large. Social responsibility is a duty every individual has to perform so as to maintain a balance between the economy and the ecosystems. A trade-off may exist between economic development, in the material sense, and the welfare of the society and environment, though this has been challenged by many reports over the past decade. Social responsibility means sustaining the equilibrium between the two. It pertains not only to business organizations but also to everyone whose any action impacts the environment. This responsibility can be passive, by avoiding engaging in socially harmful acts, or active, by performing activities that directly advance social goals. Social responsibility responsibility must be intergenerational since the actions of one generation have consequences on those following.”
ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን ተወጡ!!!
ጭፍን ድጋፍና ጭፍን ጥላቻ የሃሳብ ወንዝ አያሻግርም!
የጥላቻ ፖለቲካ የዓይምሮ ድህነት ውጤት ነው!!!