ለበርካታ አስርት ዓመታት በፖለቲካ ምስቅልቅል ውስጥ የከረመው የምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ ቀጠና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እየታዩበት ስለመሆኑ ብዙዎች ይመስክራሉ። በተለይም የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እያደረጉት ያለው የሦስትዮሽ ውይይት ለቀጠናው ሰላም መጠናከር እንደመልካም ጅማሮ ተወስዷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ።
04:08

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የሶስትዮሽ ውይይት
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የሶስትዮሽ ውይይት

https://www.dw.com/overlay/media/am/የኢትዮጵያ-የኤርትራ-እና-የሶማሊያ-የሶስትዮሽ-ውይይት/45961870/45963477

የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከወራት በፊት በአስመራ ተገናኝተው ነበር። ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ጥቅምት ሰባትም ተመሳሳይ ውይይት በሶማሊያ ሞቅዲሹ አድርገዋል። በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የተገኙ ሲሆን የኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳለህም አብረዋቸው ነበሩ።
ውይይቱን ያስተናገደችው የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ኢሴ አዋድ ከሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር በቀጠናዊ ጉዳዩች ላይ መክረዋል። ለቀጠናው ሰላም መጠናከር እንደመልካም ጅማሮ የተወሰደው የሦስትዮሽ ውይይቱ በተለይ በሀገራቱ መካከል ስላለው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጸጥታ ትብብሮች ሰፊ ትኩረት መስጠቱ ተነግሯል። DW ያነጋገገራቸው የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን የሀገራቱ የሦስትዮሽ ውይይት የህዝቦቻቸውን መሰረታዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ነው የተናገሩት።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ተስፋለም ወልደየስ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic